አገረ መንግስቱ ፈርሷል

0
1171

ስለ አማራ ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ አገሩ ሙላውን ተኝተህ ሳለ የዛሬ ሰባት አመት ጀምሮ ስጮህ ነኝ! ያኔም አልተነሳህ ዛሬ ደግሞ በቅጥ ሳይገባህና ሳትደራጅ ሆን ተብሎ ንቃትህን ለማጥፋት በተፋፋመ እሳት ውስጥ እንድትገባ በትኩስ ብሄርተኝነት ስሜትህ ላይ ሲጫወቱ “በህልውና አደጋ” ስም የማንም ፈረስ ሆነህ ጦርነት እየተማገድህ ይብሱን በፈቃድኝነት የህልውናህን አደጋ ጎትተህ በራስህ ላይ ጋርጠኻል::

  • ችግሩን ከስሩ ማወቅ:- የህልውናችን ዋነኛ አደጋ ጋሬጣ ብአዴን የተባለው እንከፍ የቤት ባሮች ስብስብ ነው:: በመለስ ፍርፋሪ ያደገ ድርጅት የራሱን ገበታ ማሰናዳት የማይችል ለመሆኑ ግልጥ ነው:: ዛሬም በአማች ፖለቲካ ስም የአማራን ጥቅም አዲስ አበባን ተፈራርሞ ከመስጠት ጀምሮ እነ አሳምነው ፅጌን በማስገደል እየተውደለድለ ያለው የአገኘሁ ደቡብ ጎንደር clan ነው:: እነሱም ልክ እንደ “አድዋው” የትግሬ clan በትግሬ ላይ እንደሰለጠነ ሁሉ በእኛ ላይ አድዋኛ እየተጫወቱ ሊሰለጥኑብን ወደው መሰል አገኘሁ ቅርሻቱን ሲያቀረሽ ለአንድ እስክስትኛ በተጋለጠ ቅጂ የሰማነው ነው:: ድፍን ጎጃም ወሎንና ሸዋን በፈሪነትና ሽንታምነት ሲከስና ሲያሳቅል ሰምተናል:: በዚህ አለመቆጣታችንና በነጋታው ከስራው አለማባረራችን ለጠላቶች የሚሰደው መልእክት አማራ ፈዛዛና ንቃቱ ገና መሆኑን ነው:: ፈዛዛ ሆንንም አልሆንም መልእክቱ ግን ነን የሚል ነው! አገኘሁ በነጋው ተነስቶ ቢሆን ግን it would have sent a strong message for both our enemies and Abiy that we are intolerant when it comes to our nationality- Amhara. However, now our enemies laugh at us, for we are people who are vilified and demoralized by our own so-called leaders. If we don’t start cleaning from within, no one will ever fear us! Agegnehu Teshager and the likes are their allies anyways.

አሁን አማራ በመደራጀትና ብአዴንን በማውረድ ላይ ቢያተኩር ይሻለዋል:: ይህንንም ጦርነት በሸፍጥ እንደ ደርጉ ዘመን ጦርነት ከውስጥ በሚባክን ሚስጥርና በ”ስልታዊማፈግፈግ” ስም ወደ መሸነፍ ያመጡታል::

በዚህ ጦርነት የበላይነቱን ህውሃት አግኝታለች ማለት አንደኛ አሁን የምታሽሞነሙናትን ክልል ይነጥቅሃል:: ጎንደርን ግማሹን ለቅማንት ይሰጣል:: ወሎን ገሚሱን ለራሱ ቀሪውን ደግሞ ለኦሮሞ ያደርጋል:: ጎጃም ለሁለት ወይን ለሶስት ይሰነጥቁታል:: ክልል አልባ ጂብሲ ያደርጉሃል! ቃራሚ ሆነህ ትቀራለህ! አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ሲያንዘርጥ የነበረው በመረሸን ነው የሚያፀዱት:: ሃይለኛ የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ሂሳብ የማወራረድ ስራ ይሰራሉ:: ያውም አማራን ጠራርጎ ከአዲሳባ በማውጣት ይሆናል::

ሌላው በጦርነት በመሸነፍ እነራያ ወልቃይት መተከል ሄደዋል ማለት ነገሩ በብረት ችንካር ተዘግቷል ማለት ነው:: የወልቃይት ኮሚቴ ሆነህ ትቀራለህ ማለት ነው!

ኢትዮጵያ እናቴ አክስቴ ቀሚስሽ ስር ልግባ ልደበቅ አለቅም ገለመሌ እያልክ የመሃይም ተረትና ዘፈን አታሳልጥ:: ኢትዮጵያ የወል ስም ነው:: ኢትዮጵያ በስምምነት ከሰማኒያ ሶስት ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለ የጋብቻ ሰነድ ነው:: ጋብቻው ካልጣመህ በራስህ ማንነት አገርህን የመመስረቱን ምርጫ ሰነዱ እራሱ በአንቀፅ 39 ይፈቅድልሃል:: ይህ የጋብቻ ውል ደግሞ በሁሉም አካላት ዘንድ ቅራኔ ያለውና dysfunctional marriage, ከሆነ ሰንብቶ dysfunctional kids ፈልፍሎ አሁን dysfunctional household ሆኗል:: Its better to have many functional houses instead of one big dysfunctional home. አዎ ኢትዮጵያዊነትን ስትፈልግ የምታወልቀው ሹራብ ነው:: ሙቀት ከጨመረ ላብ ከበዛ ሹራብ ይወልቃል:: ሻወርም ያስፈልጋል:: ስለዚህ አማራውን ከበሰበሰው ከኢትዮጵያዊነት ህሳቤ deprogram ማድረግና ሻወር መስጠት ቀጣይ ተግባር ይሆናል:: ባንዲራውን እራሱን ልንለውጥ እንችላለን:: we must embrace change. አሮጌው አቁማዳ የገባው አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳውን በማፈነዳዳት ላይ ይገኛልና! አዲስ አቁማዳ አዲስ ወይን ጠጅ ይገባል ሁለቱም ይጠባበቃሉ እንዳለ ጌታችን እንዲሁ ነው!

መስማት ከፈለግህ ስማ! አሁን ከማንም በላይ የህልውና አደጋ ያለበት አብይ እና መንግስቱ ነው:: አብይ እና ግብረ አበሮች የትም አገር እንዳይሄዱ ማእቀብ መደረጉን አትርሱ:: አሁን ይህ ጦርነት እንደሚገባ ተይዞ ካልተቋጨ አብይ በተያያዘው የበሸሻኛ አራድነት ጨዋታ ከቀጠለ ህዝብ ቀቅሎ የሚበላው እሱን ይሆናል:: የህልውና አደጋ ላይ ያለው ከአማራ ይልቅ ፒፒውና አዴፓ የባሮቹ ስብስብ ቤት ላይ ነው::

አማራ ባስቸኳይ አዲስ አመራር በማዋቀር አዴፓን አውርዶ ከውስጥ ማጥራት ስራ በመጀመር አለበት:: Immediately ceasefire መጥራት ያለበት አማራ እራሱ ነው:: ለውጭ አገራትና አካላት አማራዊ መንግስት ማቋቋሙን ገልፆ አብይና ደብረፂሆን የከፈቱትን የእብሪት ጦርነት ተቃውሞ የህዝብን ማረጋጋትና መልሶ የመገንባት አላማውን ለአለም ይፋ ማድረግ ያሻል:: we need to work with the West on the need to establish Amhara state as we face an imminent existential threat from all groups surrounding us; thus similar attention and identical statement as Balfour Declaration should be formulated concerning us.

ጥራዞችን ቶሎ በማሰናዳት አሳቡን በተወረሩ ቦታዎች ላይ ግልፅ በማድረግ ጠላት አፈግፍጎ እንዲወጣ ጥሪውን አክሎ በአለም ማስተጋባትና ብሎም ታዛቢዎችንም ቢሆን በፍላጎቱ እንደምያስተናግድ ማስታወቅ ይጠበቅበታል:: ታሪካዊ ሰነዶችን በተጠንቀቅ በማሰናዳት ታሪክ ሙሁራንን በተጠንቀቅ ማሰለፍ ይገባል:: ይህንን የታሪክ ሰነድ በማጣቀስ መሞገት የሚችሉ እሳት የላሱ ፖለቲከኞችን ደግሞ ማደራጀት ዋና ስራ መሆን አለበት:: ከኢጎ የፀዱ ሰዎችን ለማዘጋጀት ፕሮግራሚንግ አሁን ያስፈልጋል:: የጋራ ጥቅም ላይ የሚያተኩር አካላትን ማጎልበት ያስፈላል::

አሁን አቅም ያላቸው አማሮች ተሰባስበን አማራ ኔሽን መፍጠር ታሪካዊው አጋጣሚ ግድ ይላል::

▫️ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈርሳለች!

▫️ሰራዊቱ አገር አይደለም መንደር የመጠበቅ ቁመና የለውም::

▫️ህልውናችን ይልቁን አደጋ ጋርጦበታል:: በሰው ጎርፍ ሚሊሻ በሚል አሳቻ ስም ውስጡን በመጠቅጠቅ አማራውን ታታሪ ገበሬውን ለሞት ዳርገው እነርሱ እየሸሹ ነው::

ከዚህም ቀደም በፅሁፌ አበክሬአለሁ፤ አማራ ሁሉም የራሱን ነፃነት አውጆ አገር መሆኑን በአመቱ በጡሩንባ ሰምቶ በድንጋጤ የሚሞት አይነት ህዝብ ነው:: በግዜውም ያለግዜውም ዝግጁነት ያስፈልግል:: ነገ ሊዲያ ምን አለች በሉ ኦሮሚያ ነፃነቱን አወጀን ሳይውል ሳያድር ትሰማላችሁ:: ትግራይ ያው አውጇል:: እና አማራ ምንድር ነው የሚጠብቀው?

🟥 ባስቸኳይ ግዜአዊ መንግስት ልንመሰርትና ድንበራችንን claim ልናደርግ ይገባናል::

ግንዛቤ የሚያስፈልገው ጉዳይ:-

▫️አገረ መንግስቱ ፈርሷል:: አብይና ግብረአበሮቹ የመጨረሻ ሩጫ ላይ ናቸው:: የሚገቡበትን ኤምባሲ እያሰቡም እየለመኑም ይሆናል ማን ያውቃል::

▫️ስጋቴ ካደለን አገራችን ወደ South Africa አይነት ቀውስ ከክፋብን ዮጎዝላቪያን እንዳትሆን ነው::

▫️ወጠጤው አብይ አገር አጥፍቷል:: ከሱ የማይሻሉት እነ ደብረፂሆንም አንድ በሽተኛ ሰውዬ ተከትለው አገርን ቀውስ ውስጥ ከተዋል:: በአለም አቀፍ ጦር ፍርድ ቤት ሊከሰሱ ይገባል::

ይህንን ፅሁፍ በሶሻል ሚዲያ አስራጩ! ላልስሙ አሰሙ! አጉል በጥላቻና ቅንአት ተጀቡናችሁ ባላየ አትለፉ የራሳችሁ አገርና ቤተሰብ ነውና አደጋ ላይ ያለው::

ሊዲያ ዘውዱ!