ኢ-ካቦድ

0
459

Firstly, I want to thank comedian Eshetu for making a clear distinction between the true church of Christ and with these spiritual bandits and occultists! What these false prophets are doing is not the true picture of the actual evangelical teaching of our church. Certainly, what these guys are doing is called clairvoyance, not prophesy!

ነብይ ነን ባዮች እነሃዋሪያ ቁጭ ይበሉዎች! ጥንቁልና ያልተማሩ ጠንቋዮች በቁጭ ይበሉ ስልት ህዝብን ሲዘርፉ የሚውሉ መንፈሳዊ ዱርዬዎች ናቸው!

እግዚአብሄር ፍርዱ አትቸኩልም! እርሱ ለቁጣ የዘገየ ነው! ባህርዮ እንዲህ ነው! ሰው ይመለስ እንደሆን በቂ ግዜ ይሰጣል ፃድቅ ነውና! ትእግስቱን ሰው የሚፈታተንበት አይደለም! He is usually slow to anger; however, once he deemed for time to be up, no amount of prayer and pleading will avert his decision.

እስራኤልም እንዲሁ አንድ ኤሊ የሚሉት ካህን ነበረው! ካህኑም አርጅቶ ጃጀ! ልጆቹ ደግሞ መረን የወጡ ነበሩ! የእግዚአብሄር ቃል “እግዚአብሄርን አያውቁም ነበር:: ምናምንቴዎች ነበሩ” ይላቸዋል! በእግዚአብሄር ቤት ሊሰራ ያልተገባውን ሲሰሩ ብዙ ዘመን አለፈ! እነ አፍኒንና ፊንሃስ ለእግዚአብሄር የሚቀርበውን መስዋእት ከመቅረቡ በፊት በጉጠት ስጋውን እያወጡ እፍታ ይበሉ ነበር:: የእግዚአብሄርን ቤት ወግና ስርአቱን ሲያፈርሱ ያለስርአት ይሄዱ ነበር:: እግዚአብሄርም ዝም ያለ ይመስል ነበር:: ኤሊ ሽማግሌው ካህን ምልጃን ከስካር እስኪምታታበት አይኖቹ ብቻ ሳይሆኑ መንፈሳዊ እይታው ሁሉ ፈዝዞ ነበርና::

እናም ዘመናት ይቆጠራሉ በመገናኛው ድንኳኑ በተቀደሰው ስፍራ የኤሊ ልጆች እነ ፊንሃስ በመገናኛውም ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር ተኙ:: እግዚአብሄር አሁንም ዝም ያለ ይመስላል:: ቀጠለ እንዲህ እንዲህ እያለ…

እዲሁ ማይክ ይዘው ያሻቸውን እያሉ እፍታውን እየበሉ፥ በአስራት እየተምነሸነሹ ይኖሩ የነበሩ እነ ፊንሃስና አፍኒን “ጌታ ይናገረኛል አንቺ እዛ ጋር” እያሉ የሚጠነቁሉ ነበሩ! እንደዛሬው እንደ እኛ ዘመን! “ጌታ ይህንን ፕሮጀክት ስራ ብሎኛል “ብለው ደሃ ሳያበሉበት ወንግጌሉን ለገዛ ለስማቸው ዝና ህንፃ አቁሙልን የሚሉ ነበሩ:: ህንፆቹም ይሰሩ ነበር:: እነእርሱም “የግዛቤር ሶ” እየተባሉ ይኮፈሱ ነበር::

እንደለመዱት መስሏቸው እነፊንሃስ ታቦት አስመጡ ፍልስጤም ጦር ሰብቋልና! እነፊንሃስም ዝም ያለው እግዚአብሄር ደስ ቢሰኝብን ነው ስላሉ ጦር ሊገጥሙ ፊቱ ሲባልጉበትና ሲያስቆጡት የነበረውን ታቦት ለጦርነት ይዘውት ወጡ:: ታቦቱ ተማረከ! ከእስራኤል ክብር ለቀቀ ኢ-ካቦድ ተባለ!

ዛሬም ቤተክርስቲያን ላይ ነብይና ሃዋሪያት ተብዬዎች ሲፋንኑና እንዳሻቸው ሲሆኑ እግዚአብሄር ዝም ያለ የመሰላቸው ሰዎች ታቦት መማረክ እንደጀመረ ሲያዮ denial ውስጥ ገብተው ዘራፍ ሊሉ ለራሳቸው ሊከላከሉ እግዚአብሄር እንደተነካ ሁሉ ይህ “ፕሮቴስታንት እምነት ላይ ዘመቻ ነው” ብለው ነውራቸው ሲጋለጥ ያዙኝ ልቀቁኙን በጋሻ ጃግሬዎቻቸው በመልስ ምት ፅሁፎች ጩኸት እየተበራከተ ነው! በእግዚአብሄር ስም ና ቃል ላይ ለንግድ ሸቀጥ ሊሸቀጥ ስትዘምቱ ያኔ ምነው የቤተክርስቲያኗ ስም አላሳሰባችሁ?!

ኮሜዲያኑ የምትሰሩትን ነው ቁጭ ያደረገው! እሱንም አሰናክላችሁ ለወረፋ አስነስታችሁት ሲያበቃ ልምጯ ስታምማችሁ ለምን ተወረፍን ብትሉ አይሰራም! ኮመዲያኑ እንደውም ጨዋ ነው! ለይቶ ለመናገር ጥረት አድርጓል! ይህ የኑፋቄ ችግር ግን ቤተክርስቲያን ጥሩ ትምህርትና ቀኖና ያላቸውን ሳይቀር እንደ ወረርሽኝ እየተጋባ ያለ አደገኛ መንፈሳዊ ቫይረስ ነው!! ይህ የመጀመሪያ ነው! ገና ዶክመንተሪዎች ይሰራባችኋል! It’s in the works. እንኳን አጅሬው ይህንን ግድፈት አግኝቶ ንፅህት ቤተክርስቲያንን ሊያሳድፍ ሲሰራ በዘመናት መካከል እረፍት ወስዶ አያውቅም! በአልልታና በሆታ ታቦት ይዘው በወጡ በፊንሃስና አፍንኒን ድል አይመጣም! ጠላትም የእውነቱን እልልታና የጌታን አብሮነት ለይቶ ያውቃል! ባለጋራችን እንደው ክፉ ነው ተብሎ ተፅፎልናል! እራስህን አታስት አማኝ የተባክ! ቶሎ ከኤሊ ከአረጀ ካፈጀ አስተሳሰብ፥ ከነፊንሃስና አፍኒን ምናምንቴአዊ ቁጭ ይበሉ ስራ ተለይ! በገስት ሃውስ ስምና በፈውስ ስም የተመዘበረበትን የረከሰበቱ ስሙን ክብር ሳያስመልስ ዝም ላይል እግዚአብሄር “ክብሬን ለሌላ መስጠት አይሆንልኝም” ብሏልና! በእናንተ ምናምንቴዎች ላይ ቃሉ ከመሆን አይሻርም:: “ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፥ በፊቱም ሰግዶ፡— ቍራሽ እንጀራ እበላ ዘንድ ከካህናት ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ አንድ ብር አንድ እንጀራም ይለምናል።” 1ኛ ሳሙኤል 2:36

እናም ፍልስጤም ታቦቱን እንዲማርክ አሳልፎ የሰጠ እግዚአብሄር እራሱ ነው! እርግጥ ለማራኪዎቹም አይቀናላቸውም! ኮሜዲያኑ ለኮሜዲ ፍጆታ ይህንን ጉዳይ አንስቶታል:: ሆኖም “ቃል መጥቷል” እያለ ሲቀልድ እኔ ለርሱም ብርክ ያዘኝ! ቃል ክርስቶስ ነው! ቃል መጀመሪያ የነበረ ነው! ቃልም እግዚአብሄር ነው! በክርስቶስ ይቀለድም! ይህንን ሳይረዳ እርሱም አሳሳቾችን እወርፋለሁ ብሎ ስቶ ተሳሳተ! ንስሃ ግባ ወንድሜ! ዳጎን ፊት ቢያስገቡት ታቦቱን ዳጎንም አይቆምምና! ላንተም ስብራት ይሆናል! ቶሎ እባጩም ንክሻውም ሳይመጣ እግዚአብሄርን ማረኝ በል! ቸርችን አላልኩም! ዳጎን ሊቆም አይችልም ተሰባብሮ ይወድቃል! የእግዚአብሄር ክብር በማንም አይነካም!

ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ክብር ለቆባት ይሆናል ግን ምንም ቢሆን የበጉ ሙሽራ መሆኗን አትርሱ! ምናምንቴ የሆኑ ሰዎች በመድረኳ ቆመው ስላሰደቧት እናንተ በውጭ ያላችሁ ሰዎች አትሳለቁባት! ጌታዋ አንድ ቀን ይጎበኛታል:: በዚያን ግዜ ግን ይላልና በቃሉ “እናልፍ ዘንድ ዝቅ በይ ያሉሽን እበቀላለሁ” ብሎ ይናገራል! አምላኳ እንዳዘነባት አይታችሁ ተባብራችሁ አታስጨንቋት! እዘኑላት ወስላታነቷ ያመጣባት ጣጣ ነውና! ሁለተኛ ግዜ በድንጋይ ላይ የልቧን ሸለፈት ይገርዛል! ያን ግዜ በንፁህ ውሃ እንደገና ትታጠባለች! ቤተክርስቲያን ተስፋ ቃል አላት! ያለፊት መጨማደድ ያለግድፈት ትሆን ዘንድ ደሙን ያፈሰሰላት ውድ አላት!

ታቦቱ ወደ አሚናዳብ ቤት ይግባ በቂርያትይዓሪም ይቀመጥ! አንተ ግን ተለይ ከኤሊያዊ ክህነት! ሂድና ሽሽ የእግዙአብሄር ቅሬታ ሆይ!

“የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፥ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው” ኢሳያስ 34:8

ሊዲያ ዘውዱ!