ለየሱስ? …Nah ah ላንቺ ነው!

0
252

“ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን፡— እኔ ታላቅ ነኝ፥ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ።

ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፡— ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው፥ እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።

ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር።

ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።

ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና፡— እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ፡ አለ።” ሃዋሪያት ስራ 8:18

ሲሞን ፕሮፌሽን ነበረው:: ፕሮፌሽኑ እንደ ዛሬ ግዜ በድብቅ የሚደረግ አልነበረም! ገና የወንጌል ብርሃን እንደጮራ መፈናጠቅ በጀመረ ማግስት፥ ብርሃኑም እንደ ንጋት ጮራ እስኪጠባ ዛሬ ፀያፍ የምንልበትን ብቃት ሳናገኝ፤ የወንጌል ብርሃኑ እስኪያጠራና የንጋት ኮከብ በልባችን እስኪጠባ፤ እነዛ ዘመናት ወደ ጣኦት አምልኮ እንደሚታረዱ በጎች የምንጎተትበት ነበር!

የሃዋሪያት ዘመን በግልፅ ይሰሩ የነበሩ ሃጢያቶች እንደ ዛሬ ሰው አይሸማቀቅባቸውም ነበር:: Their moral compass was upside down. The time was between post-Babylonian captivity, Roman captivity, and Assyrian, the temple’s defilement by Antiochus. As so often happens, Babylon’s wealth and glory were accompanied by moral decay, wickedness, and iniquity. እና ብዙ ብዙ የአህዛብ ልምምዶች ሰርፀውባቸው ነበር!

ፍልስፍና ተብሎ የዚህች አለም ጥበብ የትምህርት ክፍል ተይዞለት፤ አደባባይ ተሰይሞለት፥ ግሪክ መድረኩ ሆና ማናቸውንም ነገሮች የእምነትም ጉዳይ ቢሆን ለጥያቄ መቅረብ ይችላል በሚል ድፍረት ገባ! የማይነካ የእግዚአብሄር ቃል ለሙግት እየቀረበ እይታዎች እንደየሰው እንዲዳብሩ የሚደረግበት ሂደት ተፈጠረ::

ለምሳሌ:- “እውነት ምንድን ነው” ብሎ ጲላጦስ ጌታችንን የጠየቀውን ጥያቄ ለፍልስፍና መንደርደሪያነት አለም እንደተጠቀመችበት የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው:: በተለይም እውቁን የጀርመኑን ፈላስፋ ፍሬደሪክ ነትሼ who shaped modern intellectualism…. “ what’s truth and the lies in the nonmoral sense” አስደግፎ በመጡ ምክኒያታዊነት እውነት ክርስቶስ ማለትም ቃሉ መሆኑን ቀርቶ እውነትን አንፃራዊ (relative) በማድረግ ስሁት ትምህርት ቀጠለ!

እውነት ቃል ነው! አንፃራዊ የምባል እውነት የለም! እውነት ፍፁም ነውና! Truth is absolute! እና “ቃልህ እውነት ነው ህግህም ፍፁም ነው” እንደሚለን ቃሉ አለማትም የተሰሩበት እውነት የተጋጠሙበትም፥ ሆነው እየሆኑም ፥ ማጠቃለያውም በቃሉ እውነት ተጠብቃ እንዳለች አይናችንን ላበራልን ግልፅ ነው! ይህ የምናየው ገሃዳዊ አለም በቃሉ ተደግፎ አለና! አለማትን ሁሉ “ይሁን”የሚል ቃል ደግፏቸው አሉ! እንዲሁ ደግሞ እውነት የሆነ ቃሉ እንደሚል ለእሳትም ተቀጥረው አሉ:: ስለሆነም እውነት ቃሉ ነው:: ቃል እግዚአብሄር ነው:: ፀጋና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ- ክርስቶስ የሱስ ከሙታን በኃይል የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ የተነሳበት ያንኑ መንፈስ ተቀብለናል እውነት ህይወትም መንገድም ሆኖልናል! ብንሞት እንኳን ህያዋን ነንና! እውነት ይኸው ነው! እንደነ ኒትሼ በቃላት ሰደቃ ስንሰበቅ ግን ኃላ ምን እንደሆነ እናውቃለን:: የፃፋቸውን እንኳ ግርፎች እህቱ ያሳተመችቸው ሲሆኑ እርሱ ግን አእምሮውን ተቀምቶ በአእምሮ ህመምተኛ ሆኖ ለሞት መብቃቱን እናውቃለን! እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት!

እናም የጥንት ባቢሎኒያንም ሆኑ አሲሪያንስ ብሎም ግሪካዊያኑ አንዳንዴ እኛ እንደምናስበው ኋላ ቀር ምንም የማያውቁና አሁን ካለነው ሰዎች በእጅግ ያነሱ ይመስለን ይሆናል ግን አይደለም!

ፍልስፍና (የአለም ጥበብ) በራሱ ህሳቤ ነው ያለውን ነው ሊል እውነትን አንፃራዊ ያደርግ ዘንድ deceptionኑን አሾልኮ አገባ!

ለምሳሌ:- ፆታዊ ግንኝነትን ብንወስድ እግዚአብሄር ለተቀደሰ አላማ ለሰው ልጆችም ጥቅም ቢፈጥረው ቅሉ ፍልስፍና የሚል የሳይንስ ዘርፍ እውነት ከተባለው ውሸት ትርክት ሊፈጥር ሲጠነሰስ ግን sexን ወደ art በማሳነስ ምንም እንኳ እንዳሳደጉት ሁሉ መስሎ ቢታይም ይህንን ለቅዱስ አላማ የተሰራን ጉዳይ በማፈላሰፍ “love is love” እንደምልባለው ዛሬ፤ ሴሰኝነት ፍትወታዊነትንና ልቅ የሆነን ዘማዊነት ፍቅር በሚል ቃላትን አጅቦ ደበሎ አልብሶ እርክሰት ሰተት ብሎ በትምህርት መልክ ሲመጣ ዛሬ አዲሱ አይደለም! የሴክስ ቴምፕሎች እስከመስራት የደረሱ አቴናዊያን ጣኦታትን ሰይመው ዛሬ የፍቅር ቀን ( Valentino) ፥ የጌይ ፓሬድ ፥ ኢሮስ (Eros) ለተባሉ የፍትወት “ፍቅር” አማልክት ቤት እየሰሩ ወደ እዚያ እየሄዱ እንዳይሆኑ መሆንን የጀመሩት ጥንት ነው! መውለድ ሲፈልጉም የfertility diety በመሰየምም ወንዱ ከሴቱ ሲራከስ ፥ በፍትወት አማልክት ፊት ወንድ ከወንድ ሲዋደቅና ያልተገባውን ነገር ሲያደርጉ ፍልስፍና ዋናው ፈረስ ነበር:: አመክንዮ መስጠት! አመክንዮ ካገኘ በቃ ትክክል ነው ተባለ! ፍልስፍና አንድን ነገር ካየንበት በተለይም በዚያን ዘመን ሁሉ ነገር በእግዚአብሄር ቃል ይዳኝና ልክነቱ ይመሳከርበት የነበረውን የአይሁድን ልማድ የተፃረረ ነበር:: ሆኖም አይሁድም በባቢሎን በአሲሪያ በግሪክና በሮማዊያን መገዛት ቆይታ ብዙ ድብልቅ ባህሎችን በማዳበር ቶራዉን ሳይቀር ተራማጅ ሊያደርጉ የሚታትሩ the unlawful Pharisees and Sadducees priesthood by forming their own schooling system called synagogues they start to dilute and create new meaning and translation to the word of Yahweh. ከተሰራበት አላማ ውጭ ነገሮችን መውሰድና ማየትን ብቃት በሚል በአእምሮ ባህር መጥፋት ሆን- ፍልስፍና! Philosophers hold your breath 🙂 I am not exempt from tending to think in that fashion.

ይህ ሂደት የፈጠረው ሰውዬው “ባየበት መንገድ በተረዳው” በሚባል የአእምሮ ሰለባነት በራስ መረዳት ነገሮችን መዳኘት እንጂ እግዚአብሄር በወሰነለት ተፈጥሮአዊውን አካሄድ በተከተለ አይደለም:: እርሱም ለገዛ የማይረባ አእምሯቸው ትቷቸዋልና የማይገባውን እያደረጉ ክቡር ሳሉ እንስሳ እየመሰሉ ሄዱ!

እግዚአብሄር በቃሉ ገልጦ ካስቀመጠው ውጭ ለማንም መረዳት ሲል የሚያጥፈው ቃል የለውም! “እኔ እንደተረዳሁት” የሚል አሳቻ አጉል ምፀት አእምሮን ከጌታ በላይ ማግዘፍ ነው! መጨረሻውም እንደነዚህ ጥንታዊ ግሪክ ሰዎች አልፎ በዚህች አለም ጥበብ እግዚስብሄር ከንቱ ላለው ነገር ታሳሪ ከመሆን በቀር ከፀሃይ በታች ምንም የምናመጣውና የምናስደምምበት አዲስ ነገር የለም አይኖርምም!

በራሱ ለጥቅማችን የተሰራ ምንም ቢሆን እንኳ አግባቡን ሲስት ግን ምንም ነገር ቢሆን ለመጥፋታችን ጠንቅ ይሆናል!

እንደዚሁ ሁሉ ስነፍጥረትንም ወስደው ጴጥሮስም ሲያስረዳ እንዳለ “ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውኃ ተጋጥማ በውኃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤ በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤” 2ኛ ጴጥሮስ 3:5

እነዚህ ጥንታዊ በፍልስፍናና Artcraft እስካሁን አለምን ያስደመሙ ቀደምት ትውልደ ትውልድ መረዳታቸው እንደ እግዚአብሄር ቃል ቢሆን ኖሮ ኖህ የውሃ ጥፋት ይሆናል ሲል ለማመን ባልተቸገሩ ነበር:: They were devoid of the knowledge of the primordial waters. They willingly become ignorant of, that by the word of God, the heavens were of old, and the earth standing out of the water and in the water. They were foolish to understand the truth of God and how he formed the earth, and so it was absurd to them to think water at the magnitude Noah was alleging to come and smite the entire world.

እናም ሲሞን ስራዬ ብሎ በአደባባይ ምትሃትንና ጥንቆላን ሲያደርግ “አንቺ እዛ ጋር ከፈለግሽ የአያትሽ ስም ልጥራልሽ” ከሚሉ የዛሬዎቹ ቁጭ ይበሉ ቦዘኔ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጠንቋዮች አይነት ብላኔ አልነበረም! በደንብ accuracy ባለው መንገድ መፃኢ እንድል ፈንታቸውን destinyያቸውን ወደ ፈለጉት አቅጣጫ direct በማድረግ መሬት ጠብ ሳይል ነበር:: ሰዎች ይህ የእግዚአብሄር እጅ ነው እስከሚሉት ድረስ አስደማሚ ነበር:: (ለበለጠ ግንዛቤ ሃዋሪያት ስራ ምእራፍ 7ን አንብቡ)

ሲሞን እነ ጳውሎስን ባየ ግዜ ጌታ እየሱስን ከነዛ በገፍ ከተመረቱ አማልክቶች አንዱ አድርጎ አስቦ መሰል እነጴጥሮስን ገንዘብ ሰጥቶ “በሉ እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ እንዲወርድበት እችል ዘንድ ብልሃቱን አስተምሩኝ አለ” ለእርሱ ይሄም የምትሃት ብልሃት መስሎት ነበር:: ጴጥሮስን አስቆጥቶ መራራ መርዝ በውስጥህ አያለሁ ቶሎ ንስሃ ግባ ትተርፍ እንደሆን የእግዚአብሄርን ነገር በገንዘብ ሽተሃል እና አለው::

ዛሬም በቤትክርስቲያ አንዳንድ ለጠላት በር መክፈቻ ሆነው በገቡ ቋንቋዎች “ don’t be religious” በምትል ልቅ ቋንቋ ቤተክርስቲያን ወጓንና ስርአቷን አሳጥቷታል! “አጉል አታመነፍስ” እየተባለ ሰዎች “እኔ የተረዳሁት” በሚል ምፀት ውስጥ መንገድ ተላላፊዎች ሆነዋል! እኛ በተረዳነው ሳይሆን ከስሜትም ከፍልስፍናም ከእውቀትም ሁሉ በላይ የሆነውን ቃሉን እንደ ቃሉ መቀበል ግድ ይላል:: አንሳት እግዚአብሄር ከልባችን በላይ ትልቅ ነው! እርሱን ለማወቅ ለመረዳት ከመሻት ይልቅ አእምሮችንን አናግዝፍ! በአእምሮ ላይ ከፍ የሚል ሃሳብ ሁሉ ለእርሱ ልናስገዛ ግድ ነውና! ማስገዛት ብቻ አይደለም ልናዋርደው ሁሉ ይገባል! አታመናፍስ እየተባሉ ነፍሶ መቅረት አለና! ይመናፈስ ለምን አይመናፈስም! ሃይማኖታዊ ያልሆንኩኝ ታዲያ አለማዊ አልሆን መቼም! ሃይማኖተኛ ማለት እምነታዊ ማለት ነው! አዎ ሃይማኖተኛ ነኝ! በትምህርት ንፋስ ሁሉ ልጎተት በንፋስ ልገፋ በአእምሮ ልጠፋ የማልሰጥለት ነገር ቢኖር የራሴውን አእምሮ ነው:: ተፈላሳፊነት ጥንት ጀምሮ ከልጅነት incline ያደረግሁበት ስለሆነ አሁን በእግዚአብሄር ሃሳብ ላይ ከፍ ሊል ሲወድ የማዋርደው እኔው እራሴው ነኝ! ቃሉ simple ነው! ቃሉን በሞኝነት እንጂ ባፈላሰፍኩት ቁጥር ከሌላ የእግዚአብሄር ሃሳብ ጋር ሲጣረስ ስለማገኘው ነው! ፍልስፍና ካለህ እዛው ካጥር ውጭ እንጂ በእምነት ነገር ካገባኸው ያጠፋል! ባለአእምሮ ብቻ ያደርጋል! እሱ ደግሞ ለገዛ አእምሮ መሰጠት ያመጣል!

እናም የእግዚአብሄር ቤት ስርአት አላት! ጳውሎስ እንዳለ:-

“ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።

“እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዓት አልሄድንምና፤” 2 ተሰሎንቄ 3:6

ሃዋሪያት እንኳ ያለወግና ስርአቷ አልሄዱም! በቤተክርስቲያን ወግና ስርአት በላይ በምንም አካኄድ በምንም ዘመን አመጣሽ አጓጉል ፍልስፍና ሊኬድ አይችልም!

የዛሬ አመት “አዝማሪ ነኝ” ያለችን ልጅ ቀደም ብላም ብቻውን የሆነውን ቅዱስ የእግዚአብሄን ልጅ መድሃኒታችን የሱስ ክርስቶስን ዘፈን ይወዳል በማለት ባለማወቅና በድፍረት ኃጢያት ተጠፍንጋ ያለችን ዘሪቱ ዛሬ ደግሞ እሷም እንደሲሞን እንዴት እንደሚዘመር አሳዮኝና እኔ በተሻለ በዘፈኔ ምትሃት ላስደምማችሁ ብላ ለራሷ የሆነ ለኢየሱስ ነው የሚል በድፍረት የሆነ ዜማ አስደመጠችን! ቤት መግባቱም ፥ መገዛቱም፥ በቀጭን በር ማለፉም፥ ሁሉን መተውንም ፥ መስቀል መሸከምም ፥ ለክርስቶስ መቀደስ (መለየት) የምትሉት ጋጋታ ሳይበዛ እንደ ድሮዬ በአዝማሪ ነኝ በፕሮፌሽኔ ” ለኢ-የሲስ ነው) ብዬ አሳያችኋለሁ ብላ ህዝበ ክርስቲያን በጎች ሳይቀሩ በፍየሎች ማእድ ሊበሉ ቅዱሱን ከርኩሱ ሳይለዮ በart ፍልስፍና ተጠምደው ነጎዱ! ያለ ወግና ስርአት ሄደው ከእሪያ ጋር ተሰማሩ!

እንዲህ እንደ ዛሬ እንደነ ዘሪቱ የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። መንፈስ ቅዱስን በሌላ እሳት offend አደረጉ እሱም እሳት አውጥቶ እዛው በመቅደስ በላቸው:: ከዚያ መቅደስ ተጎትቶ የወጣው እሬሳ የከሰሉ ሰዎች ሬሳ ነበር::(ዘለዋዊያን 10:1-4)

እኔ በዘሪቱ አልፈርድባትም! ይሄንን ሁሉ ስህተት ያመጣው እኛ አማኞች ነን! በተለይ ታዋቂ ሰው ነው ሲባል ወደ ክርስቶስ ለማምጣት በሚል ተራ ዝና ፈላጊነት ጠባቧን ደጅ ሰፋ ትደረግ የምንልበት ኑፋቄ ነው! ልክ ዘፋኝ ለእግዚአብሄር ትልቅ ሰው የሆነ ይመስል! መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ የሚለምነውና ዘሪቱ መኃል በጌታ አይን ምንም ልዮነት የለም! ሁለቱም ነፍስ ናቸው! ሁለቱም በሃምሳሉ የተሰሩ ሰዎች ናቸው! እና ዘሪቱን የልብ ሸለፈቷን ገርዘው፥ በውሃ አጥበው ፥ በደም አስቀድሰው ፥ ከሰፈር የሚያስወጣ ወንጌል ያላደረሱላት ጠማማ ክርስቲያኖች ስተው የሚያስቱ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ በገንዘብ አቀረቡላት! ከርሷ ይልቅ ለእነርሱ ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም! ክብራቸው በነውራቸው ይሆናልና! እሷንም ከእሳት ጋር ጨዋታ አያዋጣሽም የሚሉ ደፋር ወንጌላዊያን ከፊት ይልቅ ያቀኗት እንደሁ ቢመክሯት ጥሩ ነው! የያዘችው እንግዳ እሳት ሌላ የሚባላ እሳት እሷ የያዘችውን እሳት ጭምር የሚያከስል እሳት ይጠራልና!

በሁለት ሃሳብ ከሆነች እስኪረጋላት ድረስ ትቆይ! አይ ለይቻለው ካሉ በውጪ የሚቀርብ ምግብ የለንም! ቤት ገብትሽ መማር ፥ ጎራን መለየት ፥ እርሱ ስጋውን ይዞ ከሰፈር እንደውጣ ከሰፈር መውጣት ነው:: ብዙ ሃብት ነበረውና ሁሉን ትተህ ና ሲባል እየተከዘ እንደሄደው ሰው ትካዜ እንዳይሆንብሽ እቱ!

እናም ዘሪቱ የዘፈንሽው ለራስሽ ነው! ገቢውም ላንቺ ነው! እየሱስ ክርስቶስ በእውነት ሲነካሽ ትህትና ዝቅ ታደርግሻለች እንጂ አታሽቀረቅርም! የምትዋቢው ለወንጌል በመሰደድ እንጂ ባጉል ትህትና ባሉት በአፍ ቃል ጎሽታ እንትናዬ በሚል አይደለም!

የምገባው ለማነው ላልሽው? የምትገቢው ላስከተትሽለት ነው! እርሱ አዝማሪነት! የለም ለክርስቶስ ነው ካልሽ እንደ እነ ተፈራ ነጋሽ ማስመስከር ነው! ሳንቲም ሳይገደው ልጆቼ ሚስቴ ሳይል ዝናን ሁሉን እንደተወው! በግዜው ከፍ ሊያደርገው ጌታ ሰው እየተርገፈገፈ ከሚሰማው መድረክ ወርዶ መሪ ጨብጦ የሃቅ እንጀራውን በፅድቅ የሚበላ የተነካ ሰው ይልሻል እንዲያ ነው! አልጋ ባልጋ ክርስትና የለም! ዝቅ ማለት ግድ ነው! በሰው ሁሉ ፊት አለምንም ሆነ አዝማሪነቱ (ደሞ Ethiowood, Hollywoodንም የተው አሉ) በሰው ፊት ክደሽ እርሱ በአምላኩና በአባቱ ፊት ቢመሰክርልሽ ይሻልሻል! ዛሬ ለፅድቅ ተሰድደሽ ከእርሱ ጋር በኃላ በመንግስቱ መንገስ ይበልጣል እቴዋ! ለዚህ እንደ እንፋሎት ታይቶ ለምጠፋ ህይወት አትወዛገቢ! አለምን ድፈሪና ገደል ግቢ በያት! Trust me, ታተርፊያለሽ እንጂ አታጎይም! በሁለት ሃሳብ መኃል አታነክሺ! እየሱስን ያዢና ይልቅ እንደሰንደቅ ሆነሽ ብትቆሚ ይሻላል! ባንቺ ዘፈን መዝርሙር ባልሽው መንፈስ ቅዱስ አይከብርም! እርሱ ንፁህ መስዋእት ይገባዋልና! እሱን በድምፅ መስረቅረቅና በሙዚቃ ርቀት አይታለልም:: በዲቤ የሚጎተት አጋንንት መንፈስ እንጂ የጌታ አይደለም! በከበሮሽ ጋጋታ በስንድ ግጥም መንፈስ ቅዱስ አይመጣም! ንፁህ የማያነክስ መስዋእት ካልያዝሽ! እርሱም የበጎ ህሊና መማፀኛ የተሰበረ ልብ እና በተቀጠቀጠ መንፈስ ከሰፈር ከወጣሽ ብቻ ነው! ጊታርና ግጥም እንዳይመስልሽ አምልኮ!

ይህንን ካልኩኝ ለዚህ ሁሉ ስህተትሽ ዋና እኛ ኖረን ያልኖርን የወንጌሉን ቃል በጥንቃቄ ያላቀረብን ደቀመዛሙርት የተባልን አምኖ አደራ የሰጠንን ቃሉን አደራ የበላን ነን እና ይቅርታ ልልሽ እወዳለሁ! በጥፋት መንገድ ላይ አቁመው ድነሻል ዘምሪ ይሉሻልና! ለነፍስሽስ ቢገዳቸው ካለሽበት ከፍየሎች ጎራ በለዮሽ ነበር! ተለይ! ሁሉን ተይ! ሁሉን ትተሽ የሰማይን የምድርን ፈጣሪ ሃብትሽ አድርጊ! ያኔ የእውነትን መባረክ እየባረከ ይባርክሻል! የእውነትም መነካት መዳሰስ ይሆንልሻል! ምን አገኛት የሚያስብለው መለወጥ በመንፈሱ ይሆንልሻል!

ለምን እንወሻሻለን ማኔጅ የሚያደርጉሽ ሰዎች ለnew age ትምህርት አጋልጠው በእምነት ነገር አጥፍተው የነማንን አርማ እያስለበሱና እንደ ነማ እያስመሰሉሽ እንዳለ እኮ ግልፅ ነው!

“ውሸታም አንቺ ውሸታም” እያልሽ በቅኔ ትተሽ ያልተውሻትን አለም ቅኝት መቀኘቱን ትተሽ ገደል ግቢ በያት!

ዘፈኑ ግን ላንቺ ነው!