Unpardonable Sin

0
175

ጥያቄ:- “በ1ኛ ዮሐ 1:7 የልጁ የየሱስ ክርስቶስ ደም ከሀጢያት ሁሉ ያነፃል ይላል:: “ከሀጢያት ሁሉ” የሚለውን እንዳትዘነጊብኝ:: በሌላ ስፍራ ደግሞ “በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብን ቃል የተናገረ ሃጢአቱ አይሰረይለትም ይላል:: ማቴዎስ 12:31

መንፈስ ቅዱስን መሳደብ የሚለው ሀጢያት ሁሉ በሚለው ስር ስርየትን አያገኝም ወይ?

መልስ:- በመጀመሪያ የመፅሃፉን አውድ በጥንቃቄ ስናጤን ጌታችን የሱስ ክርስቶስ እውርና ዲዳ እስኪያደርገው ጋኔን የያዘውን ሰው አይኖቹና ጆሮውን የደፈነው ጋኔኑን አውጥቶ ሰውዬውም ነፃ በመውጣቱ፤ ሰውዬውም እያየና እየሰማ ካጋንንት እስራት ነፃ በመውጣቱ በህዝቡ መካከል “እንጃ ይህ መሲሁ ይሆንንን” የሚልን ነገር በማስነሳቱ ፈሪሳዊያኑ ፈጥነው ክስን በጌታ ላይ በመመስረት “በቡኤልዜቡል የአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም፡” በማለታቸው ነው:: ይህም የሚጠቁመው የራሳቸው ድብቅ የሆነ ባቢሎናዊ ልምምድን ነው:: የነያኔስና ጀምሬስን ስራ በጥበብ መልክ ይዘዋልና:: አመሳስሎ መስራትን::

እነርሱ በአጋንንት አለቃ በቡኤልዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም ይሉ ዘንድ ያነሳሳቸው በቡኤልዜቡል የነጀምሬስና የያኔስ አይነት ስራ የሚሰሩት ነበር ማለት ነው:: ካልሆነስ እንዲህ ይሉ ዘንድ ባልተነሱ ነበር! ይህንን ሊሉ ያስቻላቸው እራሳቸው ይለማመዱት የነበረ ስራ እንደሆን ጥቋሚ ነው:: ምክኒያቱን ስንመረምር:- አንድም በአጋንንት አለቃ spirit taming ይሰሩ እንደነበር የራሳቸውን ገበና ሲገልጥ፤ ዛሬ ግዜ ድረስ በክርስቶስ የሱስ ስም ሳይሆን በተለያየ ልምምዶች አጋንንት እናወጣለን እንደሚሉ አይነት፤ በክርስትና ሽፋን ውስጥ ያሉ ልምምዶችን የመጡበትን ምንጭ ይገልፃል::ለምሳሌ በመቁጠሪያ ጀርባ መደብደብ ፥ (በቡዲስት እስልምና በአንዳንድ ኦርቶዶሳዊ ልምምዶች) በውሃ ውስጥ መዝፈቅ ፥ በተለያዮ ቅዱሳን በሚደርጉ ሰዎችና መላእክት ስም ሰይጣኑን ለመገዘትና ድርድር ማድረግ፤ ሰውዬውን ነፃ ሳያወጡ በስምምነት የአንድን ሰው ህይወት በተለየ መልክ ላጋንንት ተገዢነቱ እደቀጠለ ግን የእርኩስ መንፈሱን ጭቆና አይነት ገፀ-ባህርዮን እንዲለውጥ ማድረግ ነው:: መፅሃፍ ቅዱስ በማያወላዳ ሁኔታ ሰይጣን በክርስቶስ ስም ብቻ እንደሚንቀጠቀጥና ታዝዞ እንደሚወጣ ያስተምረናል:: ፈሪሳዊያኑ ይህንን የመሳሰሉ ልምምዶች ነበር ጌታችንንም ይከሱበት ዘንድ የጀመሩት:: “ጥበብ” በሚል ስም ዛሬ የምናያቸውን አይነቶች የተለያዮ ቅጠል በመበጠስ፥ የአንድ ገዳም አመድ ነው ብሎ በመቀባት፥ ቃልን ድግምትን ደግሞ አሸንክታብ በአንገት ላይ በማሰር ፥ ከክፉ አይን (ቡዳ አጋንንት ስራ) እናስጥላለን እንደሚሉት ያለ መሆኑ ነው:: እነዚህ ልምምዶችን እስራኤል ወደ ባቢሎን ተግዞ ሰባ አመት ሲኖር ለምዶት የመጣ ከባቢሎን የታልሙዳዊያን ካባላ ሚስትሲዝም ነው:: ግብፃዊያኑም የሚሰሩት የ wizardry ስራዬ ነው::

አጋንንት በአጋንንት አይወጣም! የአጋንንቱን ጭቆና አይነቱን መቀየርና የወጣ ማስመሰል ግን ይቻላል ይሆናል:: ለግዜው! ለምሳሌ:- አጋንንት ያስጓራው ከነበረ እዛው እንዳለ አጋንንቱን ሌላ ገፀ ባህሪይ እንዲላበስና ምናልባትም ሰውዬውን ማስጮህ ትቶ፤ ሰዬውን ሳይዋጁና ነፃ ሳያወጡ መልኩን ለቀየረ አጋንንታዊ ሌላ አሰራር ተጠቂ ሆኖ እንዲቀጥል ይሆናል ማለት ነው:: ምናልባት ከቤት ደግሞ አላስወጣ ይለው ይሆናል:: የእንቅልፍን መንፈስ ሆኖ ይላክበታልና! እውነተኛ deliverance እና redemption በጌታ በየሱስ ስምና ደም ብቻ ነው! አራት ነጥብ!

እናም ይህንን ቃል በአውዱ ስናጤነው ጌታ ሁለት ነገርን ያሳያቸዋል deception ሲገልጥባቸው:: ሌላው ደግሞ ይህን የሚያድነውን መንፈስ መግፋታቸው ለጨርሶ ጥፋታቸው መሆኑን ያመለክታል! እነርሱ አጋንንት አወጣን ባሉ ግዜ በቡኤልዜቡል አጋንንቱን እንደማያወጡት፥ ይልቁንም ሌላ ገፀ ባህርይ ተላብሶ እንዲሰራ legalityን የሚሰጡ የእፉኝት ልጆችነታቸው እንጂ ነፃ አውጪዎች ሆነው እንዳልነበር ይናገራል:: ለጥቆም በእውነት ግን እርሱ የዚያን ሰው አይኑን እስኪያበራ ጆሮውን እስኪከፈት አድርጎ ነፃ ያወጣው እንደሆነ መንግስት እንደቀረበችባቸውና እርሱም የዳቢሎስን ስራ ሊገልጥ መገለጡን እናያለን! እርሱ በእግዚአብሄር መንፈስ በሆነ ስራ ሰውዬውን ነፃ በማውጣቱ ምክኒያት መንግስት እደቀረበች እነርሱም ከእግዚአብሄር መንግስት ያለመሆናቸውን “የእፉኝት የእባብ ልጆች” ሲል ግብራቸው የአባታቸው የሰይጣንን ልጆች መሆናቸውን በስራቸው ገልጦ ይነግራቸዋል::

ሌላው የእግዚአብሄር ቃል እንደሚለው እርግጥም የሆነ ኪዳን እንደሚያስረግጥልን የክርስቶስ የሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ እንደሚያነፃ ነው! ሆኖም በክርስቶስ ያለውን ድነት እናገኝ ዘንድ አለምን ስለኃጢያት የሚወቅስና ወደ ንስሃ የሚያደርሰን ግን መንፈስ ቅዱስ ነው:: ሰው ከታሰረበት ነገር ተላቆ ወደ ድነት እንዲመጣ የሚያደርገውን ያንን መንፈስ ግን የሰደበ ማለትም reject ካደረገ ያ ሰው irredeemable, unsalvageable, unforgettable, irreparable, hopeless ሆኗል ማለት ነው:: ይህ unforgivable የሚለው ቃል unjustifiable, unpardonable, inexcusable, Indefensible የሚል ትርጓሜን ይሰጣል:: ይቅር እንዳይባል የሆነ፥ ሊከላከሉለት እንዳይችሉ የሆነ፥ ለምህረት እንዳይበቃ የሆነ የሚል ፍቺ ጋር ያመጣናል:: የአንድን ሰው አመፀኛ belligerent stance ያሳያል:: There’s nothing done or said that can’t be forgiven. But if you deliberately persist in your slanders against God’s Spirit, you are repudiating the very One who forgives. The Holy Spirit is the only one who can forgive, but when we reject the Holy Spirit, we’re sawing off the branch on which we’re sitting, severing by our own perversity all connection with the One who forgives

ከዚያ በተነሳ አንድ ሰው ቅዱሱን መንፈሱን ሲሰድብ እንዳይድን እንዳይፈወስ መንፈስ ቁዱስ ወቅሶ ለእርማት ንስሃ ያመጣው ዘንድ እንዳይችል የእውነትን መንፈስ በማክፋፋቱ ምክኒያት ድነት ማግኘት እንዳይችል ይሆናል:: የክርስቶስ ደም ከኃጢያት የሚያነፃን ደግሞ በንስሃ መንፈስ ቅዱስ መርቶን ወቅሶን ሲያመጣን ብቻ ነው:: እውነተኛ ንስሃ ከጌታ መንፈስ በተነሳ የሚደረግ ነውና:: ማንንም በራሱ ተነሳሺነት ንስሃ አይገባምና:: መንፈስ ቅዱስ ካሳሰበው በቀር:: ለፍሬ የማይበቃ ካለንበት አመፃ መንገድ ፈቅ የማያደርግ ያፍ “ማረኝ ማረኝ” ንስሃ አይደለምና:: ለዚህ ነው መጥምቁ ዮሃንስ ህዝቡ ግልብጥ ብሎ ሊጠመቅ ብሎ ሲመጣ አይቶ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤” ማቴዎስ 3:7-8 ያላቸው:: በራሳቸው አመላካችነት አልነበረምና የወጡት አለምን ስለኃጢያት በሚወቅስ በእርሱ በእውነቱ ቅዱስ መንፈስ እንጂ!

”እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤ ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።” ዮሃንስ 16:8-11

በዚሁም ምክኒያት አማኞች የሆንን እንኳ አብዝተን ድምፁን መስማት ሲሳነን ለንስኃ ያለውን ወቀሳ መተላለፍ ስናበዛ እንደ ቀድሞ ወራት እንደዳንንበት ግዜ ያለውን ከመንፈስ ቅዱስን መስማት ቃሉንም መረዳት እየከበደን የሚሄደው:: ስለፅድቅ እኛንም ዘወትር በመምከር ፍሬ ባለው በተለወጠ መንገዱን በቀየሰ ለአብ በክርስቶስ የሱስ በመንፈሱ ምክር የታዘዝን እንድንሆን በእኛ እንደፍቃድ ፍፁማን ሊያደርገን ይሰራልና:: ድምፁን እንስማ! ንስኃ ከለታት አንድ ቀን ጌታን ስናገኝ ብቻ አይደለም:: በለየለት ኃጢያት ስንወድቅ ብቻ ሳይሆን እለት እለት እራሳችንን ማሳያ ዘመም ከሚያደርገን አካኼድ መጠበቂያ ነው:: በምህረቱ በሚታመኑት ደስ ይለዋልና:: ምህረቱ ደግሞ በንስኃ የሚገኝ ነው:: ንስኃ ደግሞ ከክፉ ስራና መንገድ ተመልሶ በፅድቅ መቆም ነው::

ስለዚህ በክርስቶስ በደሙ ያለውን መዋጀትና ድነት ለማግኘት ንስሃ ይቀድማል:: ወደ ንስሃ የሚያደርሰን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ወቅሶን ነው:: ይህንን መንፈስ ካክፋፋን ከናቅን ማለት ከሰደብን መዳኛችንን መንገድ በመዝጋት ለኃጢያታችን ስርየት የሚያስገኘውን የደሙን ኪዳን እንዳይዋጀን ኃጢያታችን እንዳይሰረይልን ይሆንብናል ማለት ነው::

ዛሬ ተብሎ ድምፁን ስትሰሙ እና ለዚህ መንፈስ ብትታዘዙ በደሙ የሆነ የኃርጢያትን ስርየት ታገኛላችሁ:: መንፈስ ለአብያተ ክርሲቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ!

Side Note:- የሚቀጥለው ጥያቄ መልስ የምሰጥበት ደግሞ ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው የሰውን ልጅ ስጋውን ካልበላችው ደሙንም ካልጠጣችው በራሳችው ህይወት የላችውም የሚለው ቃል ላይ ማብራሪያ ይሆናል::

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ሊዲያ ዘውዱ