ትውልድህን በደሉ

0
388

አንዱ በእሳት ሆኖ በምስል ተመስሎ
እንጨቱን ግማዱን ጭራሮ ቆልሎ
በቱባው ባህሉ አፍዞ አነኋሎ
ይሄ ደግሞ መጣ ከውሃ ላውጣ ብሎ
ሁለቱም አምልኮ ጣኦቱን ገብሮ
በፈጣሪ ፈንታ ግኡዙን ገትሮ
የኔ ካንተ ይበልጣል ብሎ ተፎካክሮ
በቄጤማው እንጨት ከዛፉ አመሳክሮ
የኔ ነው ጥንታዊ የኔ ነው የድሮ
ብሎ ተወራርዶ እንጨቱ ቆስቁሶ እሳቱን አንድዶ
ጨፌውን ጎዝጉዞ ማዶ እወንዙ ወርዶ
ሁሉም ለከንቱ ከንቱ ተሰልፎ ነፋስ ተከትሎ
በምኞቱ ፈረስ በጭፍን ቼ ብሎ
ትውልዱን ሲነዳ በባህል አመካኝቶ
የቀደመው እባብ ተንኮሉን ተክኖ
ያው የድሮው ውሸት አዲስ መስሎ መጥቶ
የክፋትን ፍሬ አብልቶ እያጠጣ ግቶ
እውቀት በማጣቱ አንድ ፊቱን ጠፍቶ
“የኔ ይለያል” ይላል ሁሉ ቃልኪዳኑን ከሲኦል ተጋብቶ

ሰሜኑን ደቡቡን ምድር ሞላዋን
የሰማይ ክዋክብትን ጨረቃና ፀሃይን
ቀኑንም ሌቱንም አየሩን ንፋሱን
ደመናን ዝናቡ የሚንጠባጠበውን
ለሰው ልጆች ጥቅም ሁሉን ሚያበቅለውን
ፈጥነው ረሱና ሁሉ እንደሆነ የርሱ እጅ ስራ
ለፀሃይ ጨረቃ ደርሰው ጎንበስ ቀና
ኮከብን ቆጠራ ምን ይሆናል ገና
ለእንጨት ለዛፉ ለእሳትና ለውሃ
እጁን የሚስመው በድፍን ጨረቃ
ትውልዱን ሲበድል በመርገም ሲጠቃ
በህያው አምላክ ፈንታ ግኡዙን ጥበቃ
የነፍሳቸው መሻት ክብራቸውን ለውጣ ስትሰራላቸው ጥጃን አቀላልጣ
የፊት ፊቱን ሽቶ የኋሊት ሽምጠጣ

ከጥንት ከነበሩ እስኪ ይንገሩና
እንዴትና እንዴት ሰማይን ዘረጋ
ምድርንስ በውሃ እንደምን አፀና
ይናገር ደግሞ ይነሳና ይጥራ
ምን ይሆናል እስኪ እኛም እናድምጣ
እዘዘው ፀሃይን እስኪ በደቡብ ይምጣ
ቀይረው በጋውን በክረምት ለውጣ
የቀኑን ስርአት ከቻልክ ልታዛባ
ዘመኑን ልትለውጥ ልብህ ከተነሳ
ብረትና ሸክላና አብረህ ላትፀና
ልብህ ሲኮራብህ ደርሶ ታበየና
በንስር ክንፍ ሆነህ በኮከብ ልትወጣ
በአመድ ስትጣል ብርሃንህን ሲያወጣ
በሌሊቱ ድቅድቅ በዚያ የሚወርዱ
ጨለማውን ተገን አርገው የሚማማሉ
እነዚህ የሰው ልጆች ምንኛ በደሉ
ዛሬ ድረስ አሉ በጥልቅ የሚሄዱ በአታክልቱ ስፍራ ገብተው የሚሰው
ዛፉን ”አንተ አምላኬ” ብለው የሚቀቡ
በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር ሚቀልቡ
ዘይት ቅቤአቸውን የሚለቀልቁ
በኮረብታው ወጥተው እጣን የሚያጨሱ
በጥልቁም ውስጥ ወርደው ደምን የሚያፈሱ
ልጆቻቸውንም በእሳትና በውሃ ውስጥ የሚያሳለፉ
ትውልዶችህ ዛሬም ተላለፈው ነጎዱ
የፈሰሰውን ደም አክፋፍተውት ሄዱ
ከባህሌ ጣኦት ተደረብ እያሉ
የክብርን ጌታ ባፋቸው በደሉ
እርሱም እንደ ‘ነእርሱ ‘ዲሆን ጠረጠሩ

ይህች ወጥመዳቸው መያዣቸው ነች
በጆሮው እንደ ሰማ ነገር ትሆናለች
እርግማን በምክኒያት ሆና እንደ ጨረባ ትደርስበታለች ክንፎቿን አርብባ
ባህል ሲላት መጥታ ልትቀር ተጣብታ
ታሳቅለው ነፍሱን ሲኦል ልታገባ

“የምስጋና ቀን ነው” እያልክ በሽንገላ ዲስኩር አትቀባባ
ሲሻ ነው ምስጋና ድሮውንም በጥልቅ ተወርውሮ የገባ

ሊዲያ ዘውዱ!