ኪዳነ ምህረት አባቴ

0
259

ኪዳነ ምህረት

በብዙ ማቃተት

በመከራ ስደት

ከዙፋኑ መሬት

ሳይመስለው መቀማት

ፈቅዶ ባዶነት

የፍጥረት ሙልአት

ሞቱ ለህይወት

በግ ሆኖ መስዋእት

አምላክ ሰውነት

የፍጥረታት አባት

አጥቶ ደም ግባት

ጥጉ የውበት

ተንቆ ክብረት

ታሞ መዳኒት

ዝቅ ብሎ መላቅ

እግር አጥቦ መርቀቅ

ትሁት ሆኖ ትልቅ

ምድርን ተጫማት

ራሱ ሰርቷት

የሌለው መግቢያ ቤት

የሁሉ ባለቤት

በኪሩቤል ልልታ ቅዱስ የሚሉት

እንዳያዮት ፊት የሚሸፍኑለት

በባሪያ መልክ ሆኖ ሞገሳምነት

እርግማን ተብሎ ያረገን በረከት

ደዌን ተመቶለት የሆነን መዳኒት

አለቅነት ሁሉ የአለሙ ሙላት

መሲህ አዳኝ የሱስ ኪዳነ ምህረት

ስለ የሱስ ፍቅር ፥ ስለ የሱስ ምህረት ፥ ስለአባ አባት!

ሊዲያ ዘውዱ