እንግዳው እሳት

0
184

”እንዲህም አላቸው፡— ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ማርቆስ 16:15

ወደ አለም ሂዱ እንጂ ወደ አለም ግቡ አልተባልንም! እኔ ከአለም እንዳይደለሁ እናንተም ከአለም አይደላችሁም!

“ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።” ዮሃንስ 17:15-16

ዘመነኛው ዘማዊው ጴንጤው ታዲያ በተቃራኒው በዘመን ማብቂያ ላይ ሆኖ “እንዝፈን አንዝፈን ብንዘፍን ምን ችግር አለ” … ” አይ አገሬ የምኖርባት ዘግነቴ” …. ” ኪዳና አላት አገሬ ግብፅ ግን የላትም” የሚል ኢ -መፅሃፍ ቅዱሳዊ ወደሆነ ጉንጭ አልፋ ዘበዘቡን ተያይዞታል:: በቅጡ በዘመራችሁ ለመዝፈን ከመገበዝ በፊት! አለም ላይ እኮ በዘፋኝነት የሚሰማችሁ አይኖርም ነበር ጌታ ባይሆን ኖሮ መራጩ:: ጌታ ያው አለምን በተናቀው ነገር ማሳፈር ስለፈለገ ነፍናፋና ምንም የሙዚቃ ስልት የማናውቀውን እያነሳ አዘመረን እንጂ ቅባትና ፀጋውን ለሰከንድ ብድግ ቢያደርገው እኮ አብዛኞች የቆርቆሮ ጩኸት ነው ድምፃችን! እረ እንፈር?! የተመረጥሽና የተቀባሽው በተናቅሽ ባንቺ አለም ሊያሳፍር እንጂ የረባ ድምፅ ስለያዝሽ አይደለም! ተው!

ዳሩ መዝሙሩን ከደነስንበትና ከጨፈርንበት ቆይተናል! አሁን እንዝፈን ወይ ጋር ያደረሰንም እርሱ ነው! ዛሬ ዛሬ ደግሞ የክለብ መብራቶችን በመፅሃፍ ቅዱስ ቋንቋ “እንግዳን እሳት” (strange fire) ይዘን መጥተናል::

” የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። ”

እንግዳ እሳት አስገብተን የጌታን ፀጋ በሚለወጥና በሚጠፋው መስለን ጣኦታችንን አለምን ግቢልን ብለን አምጥተናታል እደጁ ድረስ:: ዳሩ ወደ አለም ሂዱ ብንባል እኛ ይዘናት ልንመጣ ገና ግዜ የሆነልን ምስኪንና ጎስቋላ ፥ ባለጠጋ ነን ስንል የደኸየን ሆነናል! አርትፊሻል ጭስ ( fog smoke machines) ከማምጣት ለምን አንድ ፊቱን ከርቤና ሉባንጃውን አታጥኑም? ቡናውንና ረከቦቱንም ፥ ሌላም ሌላውንስ የተዋችሁ ማንን ፈርታችሁ ነው? ጭሱ ካማራችሁ ምን ሰው ሰራሹ ጋር ወሰዳችሁ?? የፊቱ ብርሃን ስላልበቃን ይሆን በdisco light የታጀብነው? ፀጋው ብቻውን አልሰራ አለ? ቅባቱ ድጋፍ ፈለገ? ታዲያ ዘፈኑን በመዝሙር ከዘፈንን ቆይተን ሳለ ዛሬ “መዝፈን ሃጢያት ነው ወይ አይደለም? ” የሚባልበት ክርክር ድፍረትና ምፀት ምን ሊገርም?! ምን ይደንቃል?!

ወደ አለም ሂዱ ሲለን ገብተንባትና ገብታብን ይዘንለት መጥተናል! ብልጢቱም ባቢሎን ስርአቴን ወስዳችኋል ስለዚህ እንደውም መዝሙሩን ተውና በዚሁ መቅደስ ዝፈኑ እያለችው ነው:: Like Antiochus erected Zeus in the temple and defiled it sacrificing a pig, the same anti-Christ spirit is doing the same thing, in a different light.

በምናለበት ምፀት ፥ በአናካብደው ቅለት፤ ተይዘን መልእክት አድርሱ ተብለን መልእክት ይዘንለት ለጌታ የመጣን ብኩኖች! ዴማስ አለም ስትጣፍጠው በቃ ተለየ እንጂ እንጂ የወደዳትን አለም ቤተክርስቲያን ግድ ትምጣልኝ ብሎ ጳውሎስን ግድ አላለም! አንዳንዴም ለመመለስም ለንስሃም ስፍራ እንዳይጠፋ ትንሽ ክፍተት መተው ጥሩ ነው:: ድፍረት በዛ!

ባቢሎን ቤተክርስቲያን ገብታ አስተምራና አጥምቃ እያዘፈነችው ትውልድ “መዝፈን ሃጢያት ነው አይደለም?” የሚል ዘማዊ እሰጣ እገባ ገብቶ ከወዴት እንደወደቀ እንኳን የማያውቅን ትውልድ ሆኗል! የወደቀ እኮ ይነሳል! ይሄ ቤት ኗሪው በፀጋው ቸርቻሪው መውደቁን ያላወቀው ግን በቃ ወለሉ ተመችቶታል! ከቤት ሳይወጡ መውደቅ ፥ በቤት ሳሉ በለብታ ለዘብታ መውደቅ አደገኝነቱ ሲነገረው ሲመከር “አታመናፍስ” “አጉል መንፈሳዊ አንሁን” ይላል ስለሰማይ ሲወራለት! ሁሉን በአመክንዮ ካልሞገትኩኝ ይላል:: የማይታይን አምላክ በእምነት መታመኑን ረስቶ Reason and Logic ይዞ ይዘበዝባል! “አታመናፍስ” ይላል እሱ ሰይጣን እያመናፈሰ እያበጠረው:: ፀልዮ!

ቤተ ክርስቲያን መነጋገር የነበረባት ዘፈን ሃጢያት መሆኑን እርግጡን ነገር ሳይሆን፤ በተወሰኑ የሙዚቃ ስልትና ሪትም እንኳ ከቤቷ እንዳይገባ ትከላከለው ዘንድ ታጤነው ዘንድ ይገባ ነበር::

Certain rhythms are instrumental in evoking and conjuring spirits. መችም ይሄ አዲስ የሚሆነው ለሚዘፍነው ዘማሪ ነው እንጂ መንፈሳዊውን አለም ግራ ቀኝ ለቃኜ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው! ለምሳሌ- ዲቤ ይደበደባል:: ያ የተደጋገመ specific አመታት መናፍስትን ይጠራል:: እንዲሁም Rock and Roll (the devil’s music) በመባል የሚታወቀው ሙዚቃዊ ስልት የሚያዳምጡ ወጣቶች አሜሪካኖች አገር በቤተክርስቲያን ሲፀለይ ሰይጣን ሲወጣላቸው ታይቷል! The spirit revealed itself that it possessed the teenager through the music he listens to which is Rock and Roll. ሰፊ ሃሳብ ነው:: እንዳስፈላጊነቱ በሰፊው ላትትበት የሚችል ጉዳይ ነው:: ብዙ ማሳያዎችን ማምጣት ይቻላል የተወሰኑ ምቶችና ስልቶች መናፍስትን መጎተቻና መጥሪያ ነው! እነ መንዙማ አይነት የዜማ ስልቶች spiritual assistance ስላላቸው ነው:: ሰይጣን በሙዚቃ መልክ እየሚቀርብን አምልኮ ይፈልጋል ይደረግለታልም! ነገረ ስራው ሁሉ በልኡሉ ለመመሰል መጣጣር ነውና! እናም የእርሱን ስልት ስናመጣና በእርሱ የዳንኪራ ቤቶች መመለኪያ አፀዶቹ fog machineryዎቹን disco club lightቶቹን ስናመጣና አልባሌ ሙዚቃ ስልቶችን እርኩሱን ካልረከሰው መለየት ሲሳነንwe give the devil legality to operate through the church. I have seen ”worship leaders” gone wild and smegung ungodly manifested in them, in an instant. They may not be possessed, but another spirit may have summoned them up for a short while leading the sheep astray.

የአምልኮው ስፍራ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው:: ከወዴት እንደሆን ሳያውቁ መውደቅ አለና! “የቆምክበት ምድር የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ”እንዲል ቃሉ ልብ ይሏል! አምልኮ ውስጥ በጥሪ ካልሆነ መግባትም አደገኛ ነው! ጥሪው ስለሌለ እንግዳ እሳት ማምጣቱ እና ችግሩን የመረዳት አቅም ውስንነትና እምቢተኝነትን ስለሚሞላን! ቅባቱ ከሌለ አምልኮ ዘፈን አይደለም ባለድምፅ ሁሉ እየተነሳ የሚዘፍነው! እግዚአብሄር ደስ አስኝቶት ከልቡ ምስጋናን ያፈለቀበትና በምስጋናው መጎናፀፊያ የወደቀበት “ደስ ያለው ይዘምር” ነውና ቃሉ! በልባችን ገና ሳይሞላና ደስም ሳይለን አንዘምር! ሳንቀባ አንዝፈን በእግዚአብሄር ህዝብ ላይ!

አሳፍን ”ዜማ አዋቂው” ይለዋል ይለዋል መፅሃፍ ቅዱስ! ዜማን ይለይ ነበር! ያልተቀደሰና ያልተገባውን ያውቅ ነበር ማለት ነው! በrhythmሙ ይለየዋል:: “የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።” 1ኛ ዜና መዋልእ 25:6

የቆሬን ልጆችና የአሳፍ ልጆችን ዘማሪያኑን ዳዊት በቤተ መቅደስ ላይ ሲሾማቸው ዜማን የሚያውቁ ብቻ ሳይሆኑ ዝማሬዎቻቸው ትንቢታዊ የሆኑ ናቸው:: Their musical service could be called “prophesying” 1 Chronicles 25:1-7. Descendants of Asaph delivered prophetic messages under God’s Spirit 2 Chronicles 20:14-19. Later generations sang the songs of Asaph “the seer” እስራኤላዊያን በዘመናት መካከል የሚዘምሯቸው መዝሙሮች ናቸው! መዝሙሮቹ እስከ መሲሁ ዳግም ምፅአትና ስለ አንድ ሺው አመት ንግስናው ድረስ የሚተነብዮ ናቸውና! መዝሙራቱም እንደየ አውዳመቶቹ የሚዘመሩበት ግዜ ይለያያል! ለዳስ አውዳመት ( Sukkot) የሚዘመረው ለማለፍ አምልኮ (Passover) ከሚዘመረውየተለየ ነው:: Day of atonement ላይ የሚዘመረው Day of trumpet lay ከሚዘመረው የተለዬ ነው:: የጠዋት ፥ የቀትር ፥ የማታ ፥ የዘወትር ፥ ለጦርነት ግዜ ፥ የድል ዜማ ወዘተ የሚሉ መዝሙራትን መዝሙረ ዳዊትን ስናነብ በትንሹ የተፃፉ ርእሶች ከምእራፉ ቁጥር ስር አሉ:: ሁሉም በምክኒያት ተፅፏል! ታሪካዊ ዳራውን ፥ የተዘመረበትን ምክኒያቱን ወዘተ ማጤን ለመዘምራን ትልቅ አስተዋፅዋ ያደርጋል:: ለምሳሌ “ውብ እና ድንቅ አድርገህ ፈጥረኸኛል” የሚለውን ዜማ በዘመናችን ከተዘመረበት ሃሳብ የጠለቀ ነው! ስለ ውብ ስለሆነ መልከ መልካም ስለሆነ ሰው አይደለም ስፍራው የሚያትተው:: ረቂቅ ስለሆነው ስለ ሰው ልጅ ፍጥረትና ከአፈር መበጀቱ በፊት እግዚአብሄር ያንን ሰው ስለማወቁ:: ገና አዳምን ሳይሰራው ወደ መሆን ሳንመጣ ፍጥረቱን ሁሉ እንደ አወቀው እያሰበ ዳዊት “እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ” መዝ 139:15 እያለ ስለ ሰው ረቂቅነት ደግሞም ሙትነት ፥ ገናም ደግሞ ከእርሱ ጋር መሆኑን፤ ይሄንን ሆኖ የተፈጠረበት መሆን ፥ ገና አፍርነቱ ደግሞም እንደገና መንፈሱ ሲኖርበት ሲመለከትና እስከባህር ቢሄድ ላይሰወር፥ ጨለማም እንዳይሸፍነው እያየ አምላኩን የሚጠይቅበትና ረቂቅና ድንቅ ውብ ስራውን ለእግዚአብሄር እየነገረ የሚያወሳበት ነው:: እንጂ አፍንጫዬ ሰልካካ ነው፥ ወይን ደግሞ ገፅታዬ ምንም ፉንጋ ቢሆን ጌታ ግን ይወደዋል የሚል ልል አይደለም ሃሳቡ!

የዳዊት መዝሙር በተለምዶ የምንለው የብዙ ዘማሪያን ዝማሬ ጥርቅም ነው በአንድነት ሆኖ የተጠረዘው! የዳዊት አለ ፥ የሙሴ ፥ የቆሬ ልጆች ፥ የአሳፍ ፥ የመዘምራን አለቃ ወዘተ. የማኃልዬ መኃልይም ዝማሬ እንዲሁ የቆሬ ልጆችም በትንቢታዊ ዝማሬ ድርሻ እንዳለበት የሚያትቱ ፅሁፎች አሉ:: ከሰለሞንና ከሳባ በዜማ ምልልስ ባሻገር!

እና እንዝፈን ወይ? ወይንም ዝማሬን ጌታን ከማወደስ ፥ ስራውን ከማውሳት፥ ድንቁን ከማወጅ ወጥቶ ስለሃገር ፥ ፍትህ፥ ስለ አለመግባባት …..ባጠቃላይ ፓለቲካዊ ቅርፅ እንስጠው ማለት ያው ዳንኪራ ካልደነከርኩ ማለት ነው! እርሱን ደግሞ በቦታው ቢደረግ ለምህረትም ግዜ ይገኝ ይሆናል! ወደ ነፍሳችን መለስ ያልን ግዜ ጥጋባችን ሲበርድ እንዳናፍር:: ጌታም ይህንን ሰምቶ የለ? ታዲያ እርሱ እኮ አሁን ሰዎች ቀብቆ በቅባት እየታሹ ነው:: “ታሽቶሎጂ” እንለው ነበር አለ ወንጌላዊ ያሬድ 🤣 እየታሹ አሉ! አሉ የባኦልን ዝማሬ በዝማሬያቸው ከመቅደስ የሚያባርርባቸው! ምንም እንኳ አሁን ሳኦል ቢሆንም የተሰየመው ቅሉ:: የተቀባው ባለ በገና ሲመጣ ይህንን የመስንቆ ጫጫታ ያረግብና ከሰማይ በተሰማ ዜና ፥ ከጌታ ከልቡ ትርታ ዘመኑን ለምን እንዳቀረበው የሚናገሩ ዘማሪያን ይነሳሉ:: እነዘፍሙር ይረሳሉ! ዳሩ እየረሳናቸው በላይ በላይ እየደራረቡብን እንጂ ሳምንትም አይቆይ የዛሬ ዝማሬ:: እንዲህ ባለ ሞቲቭ ተዘምሮ ድሮ ምን ይጠበቃል?!

ብዙ ቃላት ቢደረደርና ብናፈላስፈው ክርስትናም ሆነ ዝማሬ ፍልስፍና አይደለም:: የቃል ወተት ነው! የሚያዳብር:: አጥንት ነው የሚያሳድግ! ማርና ወተት ነው የሚጣፍጥ! በቀላል ቋንቋና ዘዬ ተነግሮ ግን ልብ የሚያቃጥል! አንዳንድ ዝማሬዎች “እስትንፋሴ” ብለው ከጀመሩ ሲያፈላስፉትና durationኑን ሲያራዝሙት ከሳንባ ይጀምራሉ:: ከዛ “ኦክሲጅን ነህ” ብለውም “አፈነኝ አልተነፍስም” “ወዬው” ምናምን የሚሉ መንፈሳዊ ውበትና reverence ያጡ ይልቁን erotic የሆነ ድባብ ያላቸው እየሆኑ መጥተዋል:: እረ ቀስ! Brah, God is not oxygen! He is your creator, be content with that! ስለዚሁም ምክኒያት መዝሙሮቹ የመሰማት አቅም አጥተዋል!

ቃሉን አስተምርና ስበክ ፥ ዘምርም! ጭማሪ አይፈልግም ወንጌል! ቃለ አጋኖ አያሻውም ቃሉ! አምልኮ ሰውን በሙዚቃ ሰመመን ውስጥ መክተትም አይደለም! Mesmerize almost ወደ Hypnosis የተጠጋ new age movement ነው የማየው ከየመድረኩ እድሜ ለዮቲዮብ! አንዱን አምልኮ እንኳ ሰምቶ መጨረስ አልችልም! ምክኒያትጅም the attempt is not to lead in worship, but to hypnotize the congregation by repeating one chorus over and over again. That’s a method of hypnotism.

Worship is in spirit and truth connecting to our creator without the need to evoke Him with a way of music. Like an evil spirit, Abba Yah doesn’t need to be evoked. He doesn’t want us to alert our mind as the mind is not as vital at the time of worship but our spirit. It surpasses our minds. The mind knows but doesn’t play the role, it’s our spirit that instantly connects to our Father, Abba Yah!

የክርስቶስ የሱስ ፃጋና ሰላም ይብዛላችሁ!

ሊዲያ ዘውዱ!

ብዙ ቃላት ቢደረደርና ብናፈላስፈው ክርስትናም ሆነ ዝማሬ ፍልስፍና አይደለም:: የቃል ወተት ነው! የሚያዳብር:: አጥንት ነው የሚያሳድግ! ማርና ወተት ነው የሚጣፍጥ! በቀላል ቋንቋና ዘዬ ተነግሮ ግን ልብ የሚያቃጥል! አንዳንድ ዝማሬዎች “እስትንፋሴ” ብለው ከጀመሩ ሲያፈላስፉትና coverageጁን ሲያራዝሙት ከሳንባ ይጀምራሉ:: ከዛ “ኦክሲጅን ነህ” ብለውም “አፈነኝ አልተነፍስም” “ወዬው” ምናምን የሚሉ መንፈሳዊ ውበትና reverence ያጡ ይልቁን erotic የሆነ ድባብ ያላቸው እየሆኑ መጥተዋል:: God is not oxygen bro! He is your creator be content with that! ስለዚሁም ምክኒያት የመሰማት አቅም አጥተዋል!

ቃሉን አስተምርና ስበክ ፥ ዘምርም! ጭማሪ አይፈልግም ወንጌል! ቃለ አጋኖ አያሻውም ቃሉ! አምልኮ ሰውን በሙዚቃ ሰመመን ውስጥ መክተትም አይደለም! Mesmerize almost ወደ Hypnosis የተጠጋ new age movement ነው የማየው ከየመድረኩ እድሜ ለዮቲዮብ! አንዱን አምልኮ እንኳ ሰምቶ መጨረስ አልችልም! ምክኒያትጅም the attempt is not to lead in worship, but to hypnotize the congregation by repeating one chorus over and over again. That’s a method of hypnotism.

Worship is in spirit and truth connecting to our creator without the need to evoke Him with a way of music. Like an evil spirit, Abba Yah doesn’t need to be evoked. He doesn’t want us to alert our mind as the mind is not as vital at the time of worship but our spirit. It surpasses our minds. The mind knows but doesn’t play the role, it’s our spirit that instantly connects to our Father, Abba Yah!

የክርስቶስ የሱስ ፃጋና ሰላም ይብዛላችሁ!

ሊዲያ ዘውዱ!