ግብፅ ጦር ብትሰብቅ ብዬ ስጋት አይገባኝም!

0
249

ግብፅ ጦር ብትሰብቅ ብዬ ስጋት የለኝም! እንደውም ብትሰብቅ ምን አለበትም እላለሁ! ምክኒያቱም በራስህ ጉያ ስር ባለ ወገን ከመገደል አንድ ፊቱን የሩቁ ጠላት ጦር ቢሰብቅ ይሻላል! ግድቡ ለምን ይገደባል? መብራት ለእኛ ምን ይሰራልናል! እንኳን በብርሃን ተጥለቅልቆ በጨለማውም ከዘር ፍጅት ማምለጥ አልቻልንም! እንኳን መብራት ተጨምሮ በጨለማም አልተሰወርናቸውም! መብራት እኮ ለሚያለማ ለሚሰራ ማህበረሰብ እንጂ ቀኑን ሁሉ እንደ ሙጃ ተኝቶ ውሎ ከሰአቱን በጫት ነሁልሎ በእኩለ ሌሊት ከተማን በእሳት ለሚያነድ government-sponsor በሚያደርገው ቄሮ ቴረሪዝም ባለበት አገር መብራት ምን ይሰራል?

ምናል ባንመቀኝ እና በምትደርሳቸው ትርፍራፊ ውሃ ከመቶ አመት በላይ ዝናን ያተረፈ የጥጥ ምርትን ለአለም በግንባር ቀደምትነት ለምታቀርበዋ ግብፅ ብንተውላት?! ጀርመን በመኪና ጣሊያን በኦሊቭ ዘይት የምትታወቁትን ያህል ግብፅ ለራሷ በጥጥ ምርቷ ዝናን አትርፋለች! ገና ጥጥ ስትል ግብፅ ነው የሚልህ ፈረንጄው! እኛ አባይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል ብቻ ከአርባ በላይ የውሃ ምንጭ (water resource) እያለን በተደረገብን ያላሰለሰ ፀረ- አማራዊ አገር በቀል ሽብር በተለይም ከ66ቱ አቢዮት ፍንዳታ በኃላ “መሬት ላራሹ” በሚል አይን ያወጣ ዘረፋን አስታክኮ አንዱንም ተፈጥሮ የቸረንን የአምላክ ልግስናውን ሳንጠቀምበት ይኸው ዛሬ በዘረኞች ቀመር እየተንከላወስን አሁን ደግሞ ጭራሹን በውጭ ጠላቶች ሊያሰልፉብን ብለው እነ መለስ ዜናዊ ነቀርሳ አባይ ላይ ለጥፈው ሄደዋል! የግድቡ በአጠያያቂ ሁኔታ መተለቅ ምክኒያቱ ግልፅ ሊሆን ይገባል! ግብፅ ትንፍሽ ባትል እንኳን ተሰርቶ ተጨርሶም menatinanceሱን ማን ይችለዋል? ሌላው ቢቀር It’s a very expensive project to ever posses as the poorest country of the world! Who is going to fund it when maintenance is deemed? እንደተለመደው የአንድ ወር ደሞዝ እየሰረቅን ከህዝብ ልናድሰው?

መጠነኛ ትልቀት ያለው ግድብ ቢሆን ኖሮ ማለቴ በአፍሪካ ትልቅ ሚባል አወዛጋቢ ባናደርገውና sizable ቢሆን ኖሮ humongous በመሆን ፈንታ ዛሬ ግድቡ አልቆ immediate effect በአካባቢው ባሉ ክልላት (አገራት)ሳይቀር በማስመዝገብ የልፋታችንን ውጤት ባጣጣምነው ነበር:: We must critically question as to why the Abay/Nile dam is bloated out of proportion while we have many other water sources to utilize? Is it out of sheer ambition of Meles Zenawi to benefit Ethiopia or to feign the Amhara region in a difficult position with our neighbors? Make no mistake, the Gred Dam is bloated to provoke our neighbors and to purposely pose the Amhara region in a risky spot for generations to come! Keep in mind that the dam is deliberately overblown to make the Amhara region the next Gaza strip. So, get ready for high tech war with Egypt. ልዮ ሃይልህ ቄሮን እንኳ tame ማድረግ አልቻለም እንኳን ግብፅን ሊመክት! ጠቅላይህ እንኳን ኢትዮጵያን ከግብፅ ሊያስጥል በአገር ውስጥ ላሉ ተራ የኮዶሚኒየም ጉዳያትን እንኳ የመሪነት ብቃት ማሳየት አቅቶት Camouflage ቲሸርት እየቀያየረ ሊያስፈራራ የሚጥር በራሱ አለም ስኳር ቅሞ የናወዘ ህፃን ልጅ ነው:: በጨበጣ አገር ለመምራት እየሞከረ ያለ አስቂኝና አስጨናቂ ሰው!

እንግዲህ ግብፅ ጠጥታም የምታድረው ይህንኑ ውሃ ነው:: ዘጠና በመቶ ህዝቧ በዚህ ውሃ ላይ ተንጠልጥሎ ይኖራል! ታዲያ እዚህ አገር እነ ባሮ ፥ እነ አዋሽ ፥ እነ ሸበሌ ፥ እነ ገናሌ ፥ እነተከዜ ፥ እነ ቦርከና ፥ እነጣና እነ ኦሞ ወዘተ ወዘተ ወዘተረፈ እያለ አባይ ላይ ምን ይሄንን ሁሉ የሰው ኃይልና የሌለንን ገንዘብ ማባከን አስፈለገ? ግልፅ ነው አባይ ለአማራ ችግር ከፍ ሲልም ኢትዮጱያን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች መጫረቻ ነው::

ሌላው ትልቁ አባይ ግድብ ሴራ መንፈሳዊ ስሌት ያለው ነው:: የአማራውን ክልል እስከ ላይ ኤርትሪያ ድረስ በድህነት አረንቋ ደቁሶ geographical locationኑ በታላቁ አርማጌዶን ጦርነት በደብረዘይት ተራራ የሚገለጠውን ጌታችን የሱስን የእባቡ ልጆች ሊገጥሙት ፈልገው ያሸንፉ መስሏቸው በልባቸው መታለል አግብቷልና ደብረሲናን መክበባቸው መሆኑ ነው! የማይሞትን ሊገሉ ብለው የማይረታውን ሊታገሉ ለዚሁ ጥፋት ተመድበዋልና በአፉ እስትንፋስ እስኪጠፉ ድረስ ይታትራሉ! ኢትዮጵያ ከማንም አገር ተሽላና ተቀድሳ ሳይሆን መልክአ ምድር አቀማመጧ ነው አይን ያስገባት ልክ እንደ የመን እንደ ኢራቅ እንደሶሪያ ሁሉ ማለት ነው::የግብፅንና የኢትዮጵያን ጉዳይ አካርረው እነዚህ ኃይላት military baseዛቸውን ማስገባት ይጀምራሉ ማለት ነው! ህገወጡ የስራኤል መንግስት ምስረታም በዚሁ መልክ ነው የተተገበረው:: በ6 ቀን ጦርነት ተደርጎ Arab- Israeli war ተብሎ ሁለቱም አንድ ዝርያ የሆኑ ሰዎች (Ashkenazi) እስራኤል የሚባልን ህዝብ identity ሰርቀው በዚህ ስፍራ ተደባድበውበት ሲካፈሉት ዋናዎቹ ባለቤቶች ተረሱ ማለት ነው:: አሪፍ ቆረጣ! ሰው ሰራሽ Suez canal ሰርተውም መካከለኛው ምስራቅ የሚል funny ሎኬሽን ፈጥረው እስራኤልን ከአፍሪካ የገነጠሉበት የታሪክ አጋጣሚ ነው:: ወደ ምስራቅ ሊያስገቡ መካከለኛ አሉትና ሁሉን እኛ ካላቦካነው ኩፍ አይልም አሉ አለምንም መበጥበጡን ተያያዙት! የኛም ጉዳይ ይህንኑ መሳይ ነው!

ግብፅ ግን ትቀጣ ዘንድ ቀጠሮ አለና ሸብረቡ ተጀምሯል! በትንቢት ቃል እንደሚል ግብፅን ጌታ የሚያንበረክካት አባይን አድርቆ መሆኑን በህዝቂኤልና ኢስያስ ትንቢት ላይ ተቀምጧል! ጣና ሲደርቅ ስታዮ ምክኒያቱ ይግባችሁ! አባይ ግድብ መሙላት የተፈለገውም ይህ ቁጣ ቀን ከመቃርቡ በፊት ለግብፅ መከራ ቀን reservoir እየተጠራቀመ ነው እንጂ አንተን በመብራት ብርሃን የሚያንቀለቅልልህ ማንም የልም! አትሞኝ! ቢሆን ኖሮ እነዚህን የትየለሌ ወንዞችህን እየተጠቀመ በትንንሽ ወዲያው ተፅእኖ ማምጣ በሚችል የጎጆ ኢንደስትሪዎች (small business small projects) አገር ተጠቅማ በበራራች ነበር:: small projects are effective brings immediate effect. Gigantic projects are ላም አለኝ በሰማይ ነው! በተለይ ታዳጊ አገር በትልቅ ፕሮጄክት ንድፍ እንድትያዝ የሚደረገው በዚሁ ላም አለኝ በሰማይ ህሳቤ ነው!

ኢሳያስ 19:5-13 “ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብፅም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም:: ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ። ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች።
የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቍርና ሆነች። ፈርዖንን- እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ? አሁንሳ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ያሰበውን ይወቁ። የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብፅን አሳቱ።”

ይኼው ነው!

Stop Amhara Genocide!

Stop Amhara Genocide!