0
103

*** አስቸኳይ የተግባር እርምጃ ጥሪ በ OMN ላይ !!! ***


/ይህንን መልዕክት በማጋራትና የዚህ እርምጃ አካል በመሆን ወገናዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ!!!/
/ዴቭ ዳዊት/

በተለምዶ አቶ ጃዋር መሐመድ በባለቤትነት ይዘውረዋል የሚባለው OMN የተሰኘው የጥላቻ፣ የዘር ፍጅት ቀስቃሽና የሞት አዋጅ ነጋሪ የሆነው ሚዲያ በአሜሪካ ሀገር በሚኒሶታ ግዛት በአቶ ግርማ ቲ. ታደሰ ስም የተመዘገበና ነዋሪነቱ በካናዳ ቫርንኩቨር ብሪቲሽ ኮሎምቢያ በሆነው ዶክተር አህመድ ገልቹ ፕሬዝደንትነት የሚመራ ነው።

ከሰሞኑ እንኳን ይህ ሚዲያ ከፍተኛ የሆነ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲፈፀም በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ እየቀሰቀሰ የሚገኝ ሲሆን የአብዛኛው ቅስቀሳ መረጃዎች በእጃችን ይገኛሉ።

አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ግን ህዝባዊ ተሳትፎን የሚጠይቁ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል። ይህም የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማስቻሉም በላይ በዚህ ሚዲያ ላይ ህጋዊ እርምጃ ለማስወሰድ የሚደረገው እንቅስቃሴ የብዙሃን ድጋፍ ያለው ለመሆኑ ማሳያ ይሆናል።

፩. ለሚኒሶታ ገዢ ስቲቭ ሳይመን ቢሮ /OFFICE OF THE MINNESOTA SECRETARY OF STATE STEVE SIMON/

  • OMN ፈቃድ ያገኘው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በዲሴምበር 17, 2013 ዓ.ም ከዚህ ቢሮ ሲሆን ፈቃዱ የሚታደሰውም በዚሁ ዓመት በዲሴምበር መጨረሻ ነው። በመሆኑም በዚህ መስሪያ ቤት ለሚገኙ ሁለት አካላት ከዚህ በታች በተቀመጡት የኢሜል አድራሻዎች OMN የተባለው ሚዲያ በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት አዋጅና ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑን እናሳውቅ፡-

ሀ. ለሚኒሶታ ግዛት ሀገረ-ገዢ ስቲቭ ሳይመን

Email: secretary.state@state.mn.us
Phone: (651) 201-1324
Fax: (651) 296-9073

ለ. ለ OMN ፈቃድ ለሰጠው፥ በሀገረ-ገዢው ቢሮ የቢዝነስ ሰርቪስ አገልግሎት ክፍል፡-

Email: business.services@state.mn.usus

፪. ለአሜሪካ የፓተንትና የንግድ ምልክት ምዝገባ ቢሮ /United States Patent and Trademark Office /USPTO/

  • OMN የአርማ ምልክቱን ያስመዘገበውና እውቅና ያገኘው ከዚህ መስሪያ ቤት ነው። በመሆኑም ይህ የዘር ፍጅት አዋጅ ነጋሪና ቀስቃሽ ሚዲያ የተመዘገበበት የንግድ ምልክት እንዲሰረዝ በሚከተሉት የኢሜል አድራሻዎች ሪፖርት እናድርግ፡-

ሀ. በአሜሪካ የፓተንትና የንግድ ምልክት ምዝገባ ቢሮ ዋና የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት/Office of the Chief Communications Officer/

Email: OCCOfeedback@uspto.govgov

ለ. በአሜሪካ የፓተንትና የንግድ ምልክት ምዝገባ ቢሮ የንግድ ምልክት አጣሪና ይግባኝ ሰሚ ቦርድ /Trademark Trial and Appeal Board/

Email: TTABInfo@uspto.gov

፫. በካናዳ ለምትኖሩ አማራዊያን:-

OMN የተሰኘውን የጥላቻ ሚዲያ በፕሬዝደንትነት የሚመራው አህመድ ገልቹ /ዶክተር/ ሲሆን መኖሪያውም በካናዳ፣ቫንኩቨር ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ነው። ይህ ግለሰብ በሀገረ ካናዳ ታዋቂ በሆነው BC Hydro በተባለው መስሪያ ቤት የሚሰራ ሲሆን የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ የሚከተለው ነው፡-

BC Hydro, Corporate head office
333 Dunsmuir St.
Vancouver, B.C.
V6B 5R3

በመሆኑም በመላው ካናዳ የምትገኙ አማራዊያን በሙሉ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ BC Hydro በተባለው መስሪያ ቤት ፊት ለፊት፣ በስራ ቀንና ሰዓት፣ የአህመድ ገልቹን ፎቶ እንዲሁም በ OMN የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ምክንያት የጭካኔ ግድያ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ምስል በመያዝ መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ እንድታደርጉ፣ አህመድ ገልቹ ለሚሰራበት መስሪያ ቤት የሚሰጥ በጥልቀት እና በስፋት የተዘጋጀ ደብዳቤ እንዲሁም ይህ ሚዲያ በአህመድ ገልቹ ፕሬዝደንትነት የሚመራ መሆኑን የሚያሳየውን ከዚህ ጽሁፍ ጋር የተያያዘውን ምስል በማያያዝ ለ BC Hydro ዋና መስሪያ ቤት ገቢ እንድታደርጉ፣ እንዲሁም በካናዳ ጋዜጦች ላይ ስለ አህመድ ገልቹ እና እሱ በፕሬዝደንትነት የሚመራው ሚዲያ እየፈፀሙት ስላለው የዘር ፍጅት እንድትጽፉ አደራ ለማለት እንወድዳለን።

የእርስዎ በንቃት መሳተፍ፥በጅምላ የሚጨፈጨፉ ግፉዓንን ህይወት ከሞት የመታደግ አቅም አለው!!!

በሠላም በሰለጠነ ሀገር እየኖሩ፥ በደሃ ሃገር የሚኖርን ህዝብ ማስጨፍጨፍ እንዲገታ ተባባሪ ይሁኑ!!!

ዴቭ ዳዊት።