“ይህ የመንግስት ወንጌል”

0
264

” ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” ማቴዎስ 24:14

ይህን ቃል ስናነብ የምናሰምርበት ዋናው ሃረግ “ይህ የመንግስት ወንጌል” የሚለው ላይ ነው:: ጌታችንና መድኃኒታችን ቤዛ ክርስቶስ የሱስ ይህንን ይህ የመንግስት ወንጌል በአለም ሲሰበክ ፍፃሜው እንደሚሆን ነግሮናል:: ይህ የመንግስት ወንጌል ማለት የትኛው ነው? ዛሬ እንደተደረገው ለአንዳንዶች motivational speakerነት ስራ መስክ ሆኗል ፥ ለአዳንዶች ለክፋት መሸፈኛ ማጣቀሻ ብቻ ሆኖ “በእኔ በልጥ እኔ እበልጥ” ጥንታዊነት ተላብሶ ትክክል ሊደረግ የሚፈለግበት ፥ ለገሚሶች የመበልፀጊያ መንገድ ፥ ለከፊሎች ትንንሽ አምላክነት (ግብብዲያም ነንና ትልቅ አማልክት በሉን ያሉም አልጠፉም) ለቀረው መንፈስነት ፥ ከአብ እኩልነት ፥ ከክርስቶስ ጋር እተካከላለሁ እያሉ ግብዝነትና የያዛቸውን የሃሳዊው ኢየሱስ መንፈስ መገለጫ ቢሆንም ቅሉ የጌታችን ወንጌል ቃሉ ግን ስለ መሲሁ ብቸኛ አዳኝነት የሚተርክ ነው:: ለሰው ልጆች ቤዛነትን የሰጠበትን የማዳን ስራ የሚተርክ ነው:: ይህ የመንግስት ወንጌል የተባለው ጳውሎስ በሮሜ ምእራፍ አንድ በማያወላዳ መልኩ እንደፃፈው ወንጌል ማለት:-

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤”

ይሄ ነው:: ስለየሽዋ/የሱስ ቅድመ አለም በፊት ልጅ በሆነ ወልድ ፥ በስጋ ከዳዊት ዘር ከድንግል መወለድ፥ በቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሳት፥ በኃይል የአብ ልጅ ሆኖ ስለተገለጠ ነው:: ከዚህ ውጪ መፅሃፉን ከፍቶ ባንዳንዶች ዘንድ ልማድ እንደሆነ ሲላቸው የተዋጣለት ትዳር መኖሪያ ማኑዋል አድርገውታል! Sex education ሁሉሊሰጡበት የሚደፍሩ ኤልዛቤላዊያንም አሉ:: አንዳንዶችም እጅግ ሲረክሱ ሳያፍሩ እዚሁ በፌስቡክ መንደር እንኳን የምናያቸው በጌታችን ቅዱስ ወንጌል ላይ ስለተራ የሴትና የወንድ ወሬ ማውሪያ የሚያደርጉ “የወንጌል ተጧርዎች” እንዳለው ዘማሪ ደረጀ ከበደ በዮትዮብ ገንዘብ ለመቸርቸር ቃሉን እያጣመሙና አጉል controversial በመሆን ህዝበ አዳሙን እግዚኦ ሲያሰኙት ይውላሉ! ህዝበ አዳሙን ነው ያልኩት ቅዱሳንን አላልኩም! ያዳም ፍጥረት ሁሉ ሃይማኖት እንኳ የሌለው ሁሉ ሲያፍርባቸው ሲስቅባቸው ይውላል:: ለሰማይ ምድር ፈጣሪ ግንዛቢያቸው ከገንዘብ ባርኮት ፥ ከሴሰኝነት፥ ከሆድ አምላኩነት እንዳላወጣቸው አይተዋልና! አለምን እንዳልናቋት ግን በአለም እርከን ደረጃ ሊይዙ የሚሟሟቱ ሆነው በቁስ የሚለኩ ስለሆኑ ነው:: የጌታችን ወንጌል የተከደነባቸው የአምልኮ መልክ ያላቸው ኃይሉን ግን የካዱ ሆነው የክርስቶስን የምስራች ቃል ወንጌሉን ያሰድባሉ :: እንዲህ ያሉት አስተምሮዎች ይህ የመንግስት ወንጌል ሳይሆኑ የመንደር ዲስኩሮች ናቸው! አያሻግሩም!

አምላክ ነን ሲሉ ለብሰው ወጥተው በሁለት እርምጃ ጉዞ የሚያልባቸው ሆነው ሳሉ ፥ በተዋረደው ስጋ ገና እያሉ በልተው ወደ መፀዳጃ ቤት መሮጥ እያለ፥ ዝለው እንቅልፍ እሚያዳብታችው እያሉ ፥ አልፎም ቀኑ ሲደርስ እነኩላሊትና ጉበት ቻው ብለው እነ ልብ ደክመው ፀጥ ሲል ከባዱን እንቅልፍ ሞት ተብዬው የሚያስተኛቸው ሁሉ እንዲህ እየሆኑም አምላክነትን ሽተው በስም እንደ ሹመት ሊወስዱት ሲላላጡ ያሳዝኑኛል:: ልኡልም አይቶ ይስቅባቸዋል ይስለቅባቸዋል!

ቃሉን ማሰራት ነው:: ቃሉን በእምነት በመናገር እንፈጥራለን የሚሉት ሰው በሰራው መኪና ውስጥ ቁጭ ብለውና ሰው በሰራው ቴክኖሎጂ በፌስቡክ መስኮት የሚሉ ሁሉ ተፈትሮ ያለቀባቸው ተፈጣሪዎች አምላክነታቸው እንጦሮጦስ ይግባ! “እናንተ አማልክት ናችሁ አልሁ” የምትል አንድ ሃረግ መዘው ሲያናፍሱ ቀጥሎ ያለውን ሃረግ እንዳያነቡ አይናቸውን የዚህ አለም ገዢ አጨልሞት እንጂ “እንደ ሰው ግን ትሞታላችሁ” ማለቱን ስተው ነው:: “እኔ ግን፡— አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤ ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ አልሁ።” ይህ ቃል የተነገረበት አውድ ለመዘርዘር ምናልባት በሚቀጥለው እመለስበታለሁ:: በቅጡ ሰው በሆንን መጀመሪያ! ሰው ሁን በተባለው ልክ እንኳ ሳንገን በዙፋኑ ካለው ከእስትንፋሳችን ባለቤት ጋር መተካከልን መመኘት ዳቢሎሳዊ ነው to say the least!

ዛሬ አምልኮ ማለት በተለያዮ የዲስኮ መብራቶች ተገብዞ entertainment ሆኗል:: አምልኮ ሳይሆን የሚቀርበው እራስን ማቅረብና performance ማሳያ ሆኗል:: ግን ምን አውታር ምንገዘግዝ ፥ ምን ዝማሬያችን የጨካኝ ዝማሬ ብትሆን ከመዋረድ አታመልጥም! የጨካኞች ዝማሬ ትዋረዳለ. ይላልና ቃሉ! Be reminded brethren’s that entertainment will never be worship. Hype will never level to the anointing. Religious rhetoric will never ever be an exposition of Gods word. Clairvoyance will never ever be a prophecy, it’ll always be lowkey voodoo.

እናም ይህ የመንግስት ወንጌል የተባለው ጌታችን በቅድመ አለም ወልድነቱን የሚታመን፥ ከድንግል መወለዱን ፥ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክነቱን የማይክድ! በስጋ የእኛን ሃጢያት ተሸክሞ ስለእኛ በእንጨት ከሰፈር ወጥቶ መስዋእት ሆኖ መሰቀሉን፥ መሞቱን ፥ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን መነሳቱን ፥ ስጋን በትንሳኤ አንስቶ ከፍ ከፍ ማለት ማረጉን ፥ በሰው እጅ ወዳልተሰራች ሰማያዊቷ መቅደስ የገባ ፥ በራሱ ደም ቤዛነት ሲያስገኝልን ለዘላለም ካህን ሆኖ በእግዚአብሄር ፊት ስለእኛ የሚታይ የዘላለም ሹመት ያለው ሊቀካህናት እንደሆና ብሎም በሰውና በአብ መካከል ያለው መካከለኛው አማላጅ (የእግዚአብሄር በግ ነውና) …ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንደሄደ ሰማያትን ሰንጥቆ ደግሞ እንዲሁ ተመልሶ እንደሚመጣ የማይታመንንና ይህን የማይሰብክ ሌላ ጭማሪ የሚደርብ በሙሉ “ይህ የመንግስት ወንጌል” የሚለው ወንጌል እንዳልሆነ አውቀና እንንቃ! ወንጌል ስለክርስቶስ የሱስ/የሽዋ አዳኝነትና ቤዛነቱን የሚናገር ብቻና ብቻ ነው! አማላጅነቱ ክህነት ሹመቱ የዘላለም በመደረጉ ያለ የሊቀካህናት ክህነት ሹመት ስራው duty ነው! አማላጅነቱ በኮርማ ደም ለምኖ ሳይሆን በገዛ ደሙ በማቅረብ ቀድሶን ነው:: አማላጅነቱ ስለነፍስ መዳን የሆነ ነው:: አማላጅነቱ እግዚስብሄር ሲያየው ሰን በፍፁምነት ፊቱ ማሳያ ሆኖ በኩር ሆኖ በወንድሞቹ መካከል አልፎ የገባ ይለፋችን ነው እርሱ! የጌታችን ሞት የሰማእት ሞት አይደለም! አናሳንሰው! የጌታችን ሞትና ትንሳኤ መስዋእትነት ነው:: ለዘላለም
በዚህ ምስል ሊገኝ መተካከልን እንደመቀማት አልቆጠረምና! በቀኜ ተቀመጥ ብሎ ይርምስጋዘድን የጫነለት እርሱ የእኛን መልክና ዘር እንጂ የመላእክትን ዘር አልያዘምና!

ሲኦል ወረደ እያሉ ሰየጠነ የሚሉ የባታቸው የሰይጣንን ድምፅ አልባ ፍከራ የሚያስተጋቡለት ይገሰፁ! ክርስቶስ የሱስን ለማውረድ የዘላለም ክህነቱን የሚክዱ ይረገሙ! Let them be anathema! እራሳቸውን ከክርስቶስ ሊያስተካክሉ የቅሚያ መንፈስ ያረፈባቸው እራሱን በአንድ ኮከብ ላይ ከፍ ሊያደርግ እንደ እግዚአብሄር ብሆን ሲል በአመድ ላይ እንደተጣለ ብርሃንን ከውስጡ እንዳወጣበት ክብሩን ገፍፎ ድዳ እንዳደርገው እንደሰይጣን እነርሱም ብርሃናቸው ጨልሞ ወደ ሌላ ብርሃን ሲዞሩ የብርሃን መላእክ መስሎ እራሱን በሚገልጥ በአስመሳይ መንፈስ ተነድፈው አእምሯቸው የጨለመባቸው ትእቢተኞች ሆነው ጨለማን ተገን የሚያደርጉ ተኩላዎች ሲደረጉ ነው! የክብርን መንፈስ ማክፋፋት ደሙን መርገጥ መጨረሻው ጥርስ ማፏጨትና ዋይታ ነውና ጤና ከጎደለው ትምህርት እንራቅ! በመፍራት መዳናችንን እንፈፅም!

ሌላ ላለማወቅ ወስነን ክርስቶስ የሱስን ብቻ እንማረው! የማይጠገብ ረቂቅነቱ የማይመረመር ድንቅ መካር የዘላለም አባትነቱን ፥ ፍለጋ የሌለውን ባለጠግነቱን ልንረዳ በኃይሉ ችሎት እንበርታ! ወደ እርሱ እንቅረብ ያበራልናልና! እንቅረብ ወደ ፀጋው ዙፋን እንቅረብ በመከራው ቀንም የሚረዳንን ፀጋ እንድንቀበል ዛሬ! እንቅረብ! ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል!

የሱስ ክርስቶስ ያድናል ስንል ከንዳኞች መካከል እርሱም ያድናል እያልን አይደለም! እርሱ ብቸኛው አዳኝ የሰው ልጆች ቤዛ ነው እያልን መሆኑን በደማቅ ይሰመርበት!

ለእርሱ ላዳነን በደሙ ላጠበን ለመንግስቱም ወራሽ ላደረገን እንዲው ስለመውደዱ ይክብር ክብር ይግባው! ምስጋና ይጨመርለት! ብቻውን አምላክ የሆነው ከፍ ከፍ ይበል!

ወደ መንግስቱ ግዜው ሳይመሽ ኑ! የሱስ ያድናል! ይሁን ይሁን ይሁን!

ንስሃ እንግባ መንግስት ቀርባለችና!