0
96

እንግዲ ከዚህ በኋላ ነገሮች ይበልጡን እየተወሳሰቡ እንደሚሄዱ እወቁ! በአንዱ ችግር ሌላ እየተጨመረና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነ ፥ በጣም ውስብስብ ያለና እጅግ አዳጋች የሆነ ግዜ ከፊት አለ:: አወዛጋቢው ግዜ የመታለል መንፈስ የሚሰራበት ነው:: “የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው” 2 ተሰሎንቄ 2:9 እንደ ምትሃት ያለ አሰራርነው:: በአይናችን ፊት እንኳን አሳቻ የሆኑ ማመሳከሪያዎችን እያቀረበ እውነትነት እንደሌለው ለማመሳከር ቴክኖሎጂው እራሱ deceptive ሆኖ በብዙዎቻችን አቅም መፈታት የማይችል ይሆናል:: በተለይም ዛሬ በጠበቀ የቃል መሰረት ላይ ላልታነፀ ሰው እንደ ደራሽ ውሃ ይዞ የሚሄደው ማእበል ሲመጣ ብዙ ጌታን እናውቃለን እያልን ጠንካራ የቃል መሰረት በሌለን ላይ ጭምር አሰራሩ ይሰለጥናል:: ሰልጥኗልም! ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን የዋጀ መልእክት የላትም! ቀኖናዋ በሩቅ ምስራቅ ቡድሃዊ POSITIVE THINKING አስትምሮ የተቀረፀ ነው:: ሌላውም hyper Calvinism አስተምሮ የነጎደ ሲሆን በዚያም ወገን ያለውደግሞ Baal priesthood መንበርዋን በመንግስት መቀመጫ አድርጋ በብዙ ውሃዎች ላይ የምትቀመጠው መንፈስ ተማራኪዎች ናቸው:: ለአብይ እኩይ ስራ ጠበቃ የሚቆሙ ጴንጦችና ኦርቶዶክሶች ኢማሞች ሁሉንም ይጨምራል! ዳሩ የኔ ትኩረት እነርሱ ባይሆኑም! ሌሎችም Sadducees priesthoodን የተቀበሉ ሲሆኑ እዚሁ በዚሁ ነው ሁሉም ብለው ትንሳኤ ሙታንን ክደው ይገኛሉ እንኳን ዳግም ምፅአቱን ሊያወሩ! ቤተክርስቲያን ለአለም ስትፀልይ በፅድቅ መሰደድን በቃኝ ብላ ዘመኑን ሳትዋጅ ነገር ግን አለምን መጥና ልትገኝ ወዳ ነገረ ስራዋ ሁሉ አለም አለም የሚሸት ይልቁንም የመታለሉ መንፈስ እዚህ ጠፍንጎ ይዞ የሚያሰራ መሆኑን እናያለን! በእርግጥ ቅሬታዎች አሉ እንደ ኤልያስ በረሃ የገቡ! ለአክአብና ለመንበሩ እንቢ ያለ:: እሱም ብቻዬን ነኝ እንዳይል አምላካዊ ስራ መልሱ ዛሬም አሉ ለባኦል ያልሰገዱ የተሸሸጉ! ይገለጡ ዘንድም ግዜ አላቸው::

ከዚህ በመቀጠል ማወቅ ያለብንና በጥንቃቄ ልንገነዘብ ያለው ነገር ቢኖር በአገራችን ከቤተ ክርስቲያን ጀምሮ እስከ መንግስት ድረስና ብሎም እስከ ተራው ሰው ያልተገቡና ከጌታ ባልሆነ መንፈስ የሚሰሩ መንፈሳዊ ጉዳዮች በማህበረሰብ ላይ የሚያመጣው ጠንቅ እንዳለ ነው ነው::

የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ አሳቾች

  1. መንክራት ባህታዊያን በሚል ስም ግልፅ የሆነ የጥንቆላና የሟርት የድግምት አዚም መናፍስትን እንቅስቃሴ በግልፅ በክርስትና ሽፋን ወደ ተለቀቀ አየር በማምጣት ምስኪን ምእመኖችን የተለያዮ የእርኩሳን መናፍስት ወረራ እንዲካሄድበት እየተደረገ ነው:: ቃል የማያውቀው ምእመን እንደእግዚአብሄር ቃል ያለውን አምልኮ ባለማወቁ ምክኒያት ለነዚህ የበለአምን መንገድ ለተከተሉ በደሞዝ ለተታለሉ ግለሰቦች መጫወቻ ሆነዋል:: ”ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ” ራእይ 2:14 ሃሳዊ ነብያት*
  2. የጌታን ቃል እንኳን ሊማሩ ግዜ ያሆነላቸው:: አዳራሽን ሞልተው ፓስተሮችና ሃዋሪያት ነን ብለው በኪቦርድና ታንቡር ጋጋታ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉ ምትሃታዊ ስራቸውን ሲሰሩ እንደነዛኞቹ በለአማዊያን እንኳን የተስማሙት መንፈስ ባይኖርም በብላኔ ህዝቡን ያጥቡታል:: በአሳቻ መንገድ ቃል እየመዘዙ የመዳንን መንገድ የሚያሰናክሉ ደሞዝተኞችና ባለሙያዎች የሆኑ ስጋዊያን ሲሆኑ እዚህም ቃሉን ቸል ያለ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ሆነው ምልክትን ሽተው አልፈው ለውሬው አሰራር የተሰጡ በመስኮት በገቡ እረኞች የተበዘበዙ ሲሆኑ ተኩላ ሲያዮ ለተኩላ እያስረከቧቸው የሚሮጡ ነብይ ተብዬዎች ናቸው:: በጠራራ ፀሃይ የስንቱን ሃብት ንብረት ዘርፈው ወደ ድህነት አረንቋ ሲከቱ እነርሱ በበጎች ደምና ላብ ሱፍ እየቀያየሩ በቴሌቪዥን ቻናሎቻቸው አገር ያምስሉ:: መንግስትም ፈቃድ ሰጥቶ ህዝቡን ያስበረብረዋል! “ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ” ራእይ 2:20

* ወገኛዋ

  1. ለብ ብለው ያሉ ወይ የማይዋጡ ወይ የማይተፉ ድንዙዝ እንቅልፋሟ ቤተክርስቲያን ነች! አይሞቃትም አይበርዳትም! “እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው” ራእይ 3:16 ያው ወግና ስርአቷን መባዋን እስከሰበሰበች “አየሩ ላይ ምን አለ?” “ሰማያት ምንን ያመላክታሉ” ብላ ወቅቱ ዘመኑን አትመረምርም:: ሁሌ የራሷ ምኞት አጀንዳ አላት:: ከምኞቷ የሚከለክላት ደግሞ ምንም ነገር የለም:: እንደ ሜዳ አህያ ነች! ብዙ ነገር ሽታና አልማ መንፈሳዊ ፍትወት ወራቷ እንደደረሰ አህያ ያሮጣታል:: ምን ሳሙና ብታበዛ ላትጠራ ድከሚ ያላት ሆና! ምንም ነገር ፈቅ የማያደርግ የማያስደነግጣት ነች:: በጎቿን ድምፅ አታለማምምድም ስለዚህ ባለሙያተኞችና ሃሳዊ ነብያት መጥተው ከጋጥ በጎቿን በሚያባብል ቃል አስኮብልለውባታል! የተበዘበዘች ነች! አሁንም ምርኮዋን እንዳታስመልስ እሷም ሲሻት ያው የምትቃወመውን ቅርፁን የቀየረ ባላቅን ያስተማርውን በልአማዊ መንገድ ትሄደዋለች! የራሷን ቨርዥን ሰጥታ ጉዳዮን ታመናፍሰዋለች! “አንቺስ፡— አልረከስሁም በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? በቈላ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ያደረግሽውንም እወቂ፤ በመንገድም ላይ እንደ ተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል፤ በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፤ ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል” ኤርሚያስ 2:23-24 …አይደክማትም ዛሬም ለንስኋ አትጣራም! የበደልነውን ጌታ በእንባ አታስፈልገንም! እሷም ለlowkey በልአማዊ ምትሃት ስትገበዝ ከወዲሁ መነቃቃት ሪቫቫል ይሆናል በሚል ምእመኑን የራሷን ተስፋ ታጠግባለች! መንግስት ቀርባለች ፥ አውሬው ሊፈታ ነው ፥ ጌታ ሊመጣ ነው የሚለውን ርእስ ከሰይጣን በላይ እሷ ፈርታዋለች! አክአባዊ መንግስት
  2. መንግስታዊ ምትሃተኝነት
    ይህ ቡድን ደግሞ በአለም ላይ ካሉ ዋና ከሚባሉት ሃይማኖት ተቋማት ከወጡ ቤተሰብ ተወልጄአለሁ በሚል ሃሳዊ ለምድ ለባሽ ወንጌላዊ ካባ በለበሰ አምበል መሪነት ዲን ማእረግ የታጀቡ occultistቶች ናቸው:: ጣኦስን አቁመው በጥንታዊ መፅሃፍ ስም ክርስቲያናዊና አገራዊ ሊያደርጉት ሲባዝኑ መሆኑ ነው:: ይህ መንግስት sponsor የሚያደርገው የጥልቁ ቡድን አንድ ክንፍ ይዞ ሲያማትር እስከ አደባባዮች ድረስ የወጣ ዛሬ አርትፊሻል ሃይቅ ሁሉ ይሰራለታል የሚባለው የባህር አጋንንት አምልኮ በባህላዊነት ስም ይፋ ወጥቶ ባደባባይ ሲዘከር አይተናል::

ለጥፋት ቀን የተቀጠሩ

  1. ሌላኛው ደግሞ ማህበረሰባዊ መንፈሳዊ ኪሳራ ላይ በመሆናችን ምክኒያት ዛሬ በአንድ ጀምበር ለመናጠጥ ሲሉ ነፍሳቸውን ለሰይጣን ለመሸጥ ሰልፍ የያዙ መበራከታቸው ሌላው የዘመናችን ትልቁ አሳፋሪው ጠንቅ ሆኗል::

የነዚህ ሁሉ ድምር ለመናፍስትና ለጨለማው ስልጣናት open season ፈጥሯል:: በመንፈሳዊ አለም ለሚራኮተው ለክፋት መናፍስት ለአየሩ ገዢ በር ከፋቾች በመንክራት፥ ዲኖች: ሃሳዊ ነቢያት ፥ ለምድ ለባሽ ፓስተሮች አጋንንታዊ አሰራርን ቃሉ የሚቃረነውን ስራ ከአውድ ውጭ ቃልን በመመዝበር መክንዮ እየሰጡ ህጋዊነትን የሚያላብሱና ደም እየገበሩ ዛሬ የጣኦቶቻቸውን ምልክቶች እንኳን በግልፅ እያቆሙ ኢትዮጵያን ወደ ጠለቀ የጨለማና የጥልቁ መናኸሪያ አድርገዋታል:: ኢትዮጵያ ድሮ ንፁህ ነበረች ማለቴ ሳይሆን ገደብና ልክ ግን ነበረው:: እንዲህ እንደ አሁን ግዜ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ነፍሱን ለመሸጥ ሰው ተደራጅቶ አያውቅም! ለቅስናቸውም ሆነ ለፕስትርናቸው ምንም ትምህርት የሌላቸው ግለሰቦች ከተማ ገብተው ሰው በመቁጠሪያና በጧፍ እየደበደቡና እያቃጠሉ የሰሩበት ግዜ ብሎም በካራቴና በስልክ መናፍስት እናውጣ የተባለበት ዘመን አልነበረም:: ምንም ቢሆን ይብዛም ይነስም በግብረገቡ የተሻለ ትውልድ ለየሃይማኖቱ ለእምነቱ ቀኖና የሚቀና በገባው ልክ የሚታመን ትውልዶች ነበሩና!

በተለይም በተለያየ ሽፋን የሚደረጉ ጥንታዊ የሆኑ የማያድኑ ከጥልቅ ለሚጎተቱ አማልክቶች በተለያተ ሽፋን እየተሰጠ ወደ ግላጭ በመንግስት ደረጃ ሳይቀር የሚደረግ አጋንንታዊ ስራ በማህበረሰቡ ላይ ሊያመጣበት የሚችለውን ጣጣ በትዊተር ገፄ ላይ በግዜው አስፍሬ ነበር:: ምንድር ነው እርሱ:- እንዲህ ያሉ በመንግስት ደረጃ ስልጣንን consolidated ለማድረግ ህግን ተከትለውና ተመርጠው ሳይሆን በአፍዝ አደንግዝ የታጀበ አሰራር ግልፅ ሲወጣ የሚያመጣው consequence አለ!

በግለሰቦች ደረጃ ደግሞ ባንድ ጀምበር ለመክበር ሲሉ እንደ ማህበረሰብ ደግሞ ግዜውን ለራሳቸው ለማስዋጀት ከጥልቁ power solicit ማድረግ መበራከቱ ብዙ ምርምር አያሻውም! ይሄ ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል! በወቅቱ እንደፃፍኩት በተለያየ “በአል” እያሳበብን በባህላዊነት ስም እያስደገፍን የምንከፍተው የመናፍስቱን ሰማይ በግላጭ በከተማዎቻችን እንዲራመዱ ያደርጋል:: access ይሰጣል! effectቱ ምንድን ነው? ድንገት ጤነኛና ደስተኛ ሰዎች ያብዳሉ! ድንገት ልጆች ተነስተው እራሳቸውን ያጠፋሉ:: ወይን ቤተሰቦቻቸውን ይገድላሉ:: ጠዋት አብረው ስቀው ቁርስ በልተው አባት ተነስቶ ልጆቹን ሚስቱን ይፈጃል:: ዛሬ እንደምታወሩት ያለ የሚቀፍ ነገር በቤተሰብ መካከል ይከሰታል! ይሄ የሚያመላክተው ሰማዮ በመናፍስት መበከሉንና ሰዎች እንደ እንሰሳ እየተመሩ እንደሆን ነው:: ይህ በአውሮጳና አሜሪካን የሆነ ነገር ነው:: በተለይሜሪካን በ60ዎቹ መናፍስት በግላጭ በከተማዎቻቸው ታይተዋል! ሰዎችን በሌሊት በየቤቶቻቸው ጎስት መናፍስት አራውጠዋል!

እና ሱባኤና ፆም ፀሎት በንስኋና በመንፈሳዊ ውጊያ መንፈሳዊ ጦር እቃዎቻችንን ማንሳት ግድ ይላል:: በመንፈሳዊ ቅኔና ዜማ አምልኮን እያደረጉ ሳይዘናጉ በእግሩ ስር ቁጭ ማለት ከዚህ ሁሉ ክፋት ያድናል! አማኞች አይኖቻችንን እንክፈት! እንፀልይ! መንፈሳዊውን ውጊያ እንዋጋ! “እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ” እራይ 3:11

ከእግዚአብሄር ቤት ጀምሮ ያለው የመናፍስት አሰራር ለሃሳዊው ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ ሆኖ ይስተዋላልና እንንቃ::

“እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።” ራእይ 2:16

ሊዲያ ዘውዱ

ንቁ