የበጫጫው ተዋናይ አብይ

0
388

ድራማው ከጅማኛ ወደ በጫጫኛ ወርዷል!

የ”ተማሪዎች እገታ” አብይና ለማን ጥግ ላይ አስፈንጥሮ ይሆነናል የሚሉትን የኦሮሞ ህዝብ ድጋፍ ከስራቸው የተቀመጡበትን ስጋጃ ምንጣፍ ስቦ የወሰደባቸው የቄሮና ጀዋር ጥምር ቅንብር ተጀምሮ በኦፌኮ መቧደን አንድም የኦሮሞ ድጋፍ ሳይቀርላቸው እርቃናቸውን መሬት ላይ ማስቀመጡን ፀሃይ ሳይወጣ በፊት አዲስ ድራማ ትወና መጀመረው “አማራ ልጆች ታግተዋል” የሚል ሰስፔንስ ፊልማቸው ግልጥ አድርጎ ያሳያል::

አብይና ኦዴፓን ከስራ ውጭ የሚያደርጋቸው ኦፌኮአዊ ማእበል እየመጣ ስለሆነ ኦዴፓን የቀረች ኃሏን አሰባስባ ባለቀ ጉልበት ተጠቅመው “የአማራን ልጆች አግደዋል”:: የታገዱት ልጆች መካከል አምልጣ መጣች የተባለችው ልጅ የሚፈልጉትን በጓደኛዋ ቴክስት አላካ ከተፃፈላት አንፃር ስትገልፀው “አማራው ህዝብ ለአመፅ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ይፈልጋሉ” ብላለች:: አማራው እንዲያምፅ የሚፈለልገው ማንም ሳይሆን የአብይ በጨጫዊ ቡድን ነው:: አማራው ጉምጉም ካለ እዚህ ጋር ያለውን የአክራሪ ኦሮሞ ትኩሳት አሰተነፍሳለሁ ብሎም ትኩረትም ወደ እኔና ምርጫዬ ላይ ሳይሆን ከወደ አማራ ክልል ሊነሳ በሚችል ሃይለኛ ግለት ላይ ይሆንልኛል እናም በዚህ አጋጣሚ የኦሮሞን ልብ አንጠልጥሎ ለውጡ ሊደናቀፍ ነው ብዬ አማራውን ጠፍሬ እይዝላችሃለሁ በሚል ማባበያ ልብ ሊሰርቅ ጥሎሹን ደግሞ ባመፀው አማራ ላይ ጁላን አሰልፎ ጥይት በማዝነብ ይሆናል ማለት ነው:: ከዛ ካርድ በሙሉ በአብይ ሳጥን ልትገባለት ማለት ነው::

በኦሮሞ ክልል ያለውን ባንክ ከማዘረፍ ጀምሮ ጋጥ የወጣ ስራ የሚሰራው አብይና ቡድኑ ነው:: ገንዘቡን ቶሎ ወደ ራሳቸው ኪስ ያስገቡበት ምክኒያ ደሞዝተኛውን ኦዴፓንም ሆነ “ኦሮሞ” ክልልን የሱ ተመፅዋች በማድርግ ለማንበርከክ ነው::

ለመሆኑ የታገቱት የአማራ ልጆች ቤተሰቦች የት አሉ? ሚዲያ ቢያጡ ቢያጡ ፌስቡክ ላይ በአንድ ሰው ዜናውን የልጆቻቸውን ስምና የተሰወሩበትን ቀን ቆጥረው ማስለቀቅ እንዴት ከበዳቸው? ይህ ነገር እውነትስ ከሆነ የአማራ ህዝብ ልጆቹን እንኳ ሲነጠቅ ሰልፍ የማይሰለፈው ምን ያህል ቢደነዝዝና ጨካኝ ቢሆን ነው? ተው እንጂ!

ሲለጥቅ እንዴት ለዚህ ጉዳይ አንዲት ልጅ ብቻ የሁሉም የዜና አውታር ምንጭ (source) ልትሆን ቻለች? ይህ ባጋጣሚ ወይንስ በተቀነባበረ ሴራ? እንድታመልጥ ወይንም (አስመልጠው ልበል)ሆነ ተብሎ የተሰራ ነገር ያለ ይመስላል:: ልጅቱ ቪክትም አይደለችም ማለት ሳይሆን ከቪክትምነትም ባሻገር የተሰራባትን ድራማ የመገንዘብ የብቃቱ ስለማይኖራት የድራማው ሰለባም ነች ብዬ ለማከል ነው::

ስልጣን ከእጁ እያመለጠው ያለው ፌኩ ጠሚዶኮ አብይ ሳር ውሃ በማጠጣትና ጎዳና ተዳዳሪ ለአንድ ቀን ምግብ በካሜራ ማጉረስ የትኩረት መሳቢያዎቹ እጅ እጅ ከማለት አልፎ እግር እግር እስኪለን ችኮ ጋንዲያዊ ድራማ እራሱን እንደ የዋህና ጅል አስመስሎ በመሳል እንዲህ ያለ ፀያፍ ድራማዎችን የማይሰራ ለምንም የማይበቃ mumbo-jumbo ሲያስመስል ነው:: በህዝቡ ስነልቦና ላይ ጨዋታ የያዘ ይመስላል::

በዚህ በኩል ደግሞ አዴፓንና ተስፈኛ አክትቪስቶቹን ይዞ ላቀ ሟሸ እያስባለ እራሱ በሾማቸው ሰዎች ጀምሮት የነበረውን የጎጥ ስንጥቅ እያሰፋ ይገኛል:: ከአዴፓ ስር ፍርፋሪ ሊለቅም ተስፈኛ ሆኖ የተሰለፈው አክትቪስት ከአዴፓ መኃል ቆንጆ እየመራረጠ ይገኛል:: ከአጋንንት መኃል ጥሩ መላክ ለማውጣት መላላጥ አይነት ነገር…አይ አለማፈር! አዴፓ በድንገተኛ አጋጣሚ አንድ ሰው አግኝታ ነበር:: በተቀናበረ ሴራም አስወግዳዋለች! ወሬ የሚያወራ ሳይሆን መድፍ አገላባጭ ነበር አስከብበው ሊያሲዙ ሲድበሰበሱ የራሳቸውንም ግንባር አስበሱ!

አሳምነው የኛ ካሲም ሱሌይማኒ ነበር:: ግን የእኛም ቤት ረዛ እና ሮሃኒዎች በሽ ናቸው:: የፖለቲካ ቀሽሞች ሲያጨማልቁት ገብተው አዴፓ በሂደት ይሻሻላል የሚል የደንቆሮ ዘዬ ይዘይራሉ! “ለኦሮሞ ጥቅም እንሰራለን” የሚሉ አዴፓዎች ምን አለባቸው የህዝባቸውን ድንቁርና የእነርሱ ከፍታ ነውና ክልሉን አደጋ ላይ ጥለው በምክኒያት የለሽ ድህነት አረንቋ ውስጥ ዘፍቀውታል:: እነርሱ በአሜሪካንና አውሮጳ እየዞሩ እርጥባን ይለምናሉ:: በልተው የማይጠረቁ ተቀብተው የማይወዙ መጋዣዎች!

አዴፓም ይህንን በጨጫኛ ጠለፋ ድራማው ላይ ከውን ቢባል ቀሚሱን ለብሶ ለመተወን የለመደው የተካነበት ጉዳይ ነውና ከተወና ውጭ ነው ማለት ይከብዳል!

አዴፓን እንደ እንቅርት እራስህ ላይ ለጥፈህ የምትኖር ህዝብ ሆይ:- እንቅርቱ ፈንድቶ በቅርብ ክልል አልባም ትሆናለህ! ተነስን ስላልሰማህ ተኛ ነው የምልህ! አዎ ተኛ!