ብሩቲስታንቱ አፄ

0
382

ብሩቲስታንቱ አፄ

=============

መቼም ጥራዝን ሲነጥቁ የማይሆኑት የለም:: እናም ዛሬ ስለዚህችው አባይ አገር ላወራ ተእደድኩኝ! ደርሳ ራሷን የፍጥረት መሰረት የምታስመስልይቱን፥ በዲስኩርዋ ከፍጥረት ቀድማ ሁሉን ከላይ የቀዳች የምታስመስለውን፥ የህዝቧን መሃይምነት ተማምና በማሃይምነትም እንዲታተም ገና ድሯን የምታደራ ቃል አባይ ምድር ኢትዮጵያ! እንኳን ሃይማኖቷን ስሟን እንኳ በግሪክ የተቸረች መሆኗን እረስታ!

አፄ ቴዎድሮስ መፅሃፍ ቅዱስን በአማርኛ ባስተረጎሙ ግዜ ጦር የሰበቁባቸው ቄሳውስቱ እንደ ነበሩ ታሪክ ያወሳል:: ለምን? እንዴ መፅሃፉን ለራሱ አንብቦ ህዝብ ሊረዳው ይሆናላ! እናም አፄ ቲዎድሮስን ለማሸማቀቅ እሱ “ቡርቲስታንት” ነው እያሉ ቄሶቹ መስደብ ጀመሩ:: ፕሮቴስታንት ለማለት ፈልገው ነው! ቡሩቲስታንት 🙂

እስከዛሬ በዘለቀው ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ ደቂቀ እስጢፋኖስን በማጥፋት የጀመረ እነሆ ዘመናትን አልፎ እዚህ ደርሷል:: ይህ ዘመቻ መቼም የሚቆም አይደለም! እንዲቆምም አንጠብቅበትም! “የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም።” መክብብ 1:9 እውነት ቃሉ በእባቡ ተንኮለኝነት መገፋት የጀመረው በሴቲቱ ሃሳቡን ካሳደረ ጀምሮ ነው!

የእውነት ቃሉ ከጥንት ጀምሮ ፀሃፍት ነን በሚሉ፥ ፈሪሳዊያን በሆኑ የህግ መምህራን፥ ካህናትና ቄሳውስት ነው ሲገፋ ሲዳፈን ሲበረዝ የኖረው:: ከአዝሙድ ሰናፍጭ አስራትን የሚያስወጡ ፍፁማኑ ፈሪሳዊያን ሚዛኑን እኩል ሊያመጡ አንዲትን አስሙድ በሚዛን ላይ ልዮነት አምጥታለች ብለው ለሁለት ትሰንጠቅ የሚሉ ፍፁም የሚሆኑ በሰንበት በግ ጉድጓድ ቢገባ ከጉድጓድ በግን ሊታደጉ ግን ሰንበትን የሚሽሩ ቃል አባዮች ናቸው:: በጉድጓድ ለገባው ለበጉ ግድ የሚላቸው የአስራት በግ ስለሆነ መስዋእት ሲቀርብ እነርሱ ከመሰዊያው ሊበሉ ህግ ስለሚያዝላቸው ስለዚያ ሲሉ ነው:: ጌታ ደግሞ የራሱ የሆኑትን ልጆቹ በጎቹን በሰንበት ቢፈውስ ምን ሲኮን ይሄ ይደረጋል ብለው አገር ይያዝልን ይሉ ነበር:: ምክኒያቱም የተፈወሰው ሰው እነሱን ደጅ መጥናት ስለሚቀር ነው:: ፅዋ እያጠጣ በትፈወሳለህ የእነርሱ ተስፈኝነቱ በአዳኙ እጅ ፈውስ ስለተላቀቀ ነው::

እና ዛሬ ይህንን ትንሽ ጥሁፍ ልፅፍ ያስገደደኝ የውልደት በአል የኦርቶዶክሶች ብቻ ነው የሚሉ ተከራካሪዎች ስላየሁኝ ነው! ሰነፍ በስንፍናው ሲመካ እንደማየት የሚገርም ነገር የለም መቸም!

To set the record straight የዛሬው ቀን (እርግጡን የጌታን ውልደተ ቀን ማንም ባያውቀውም) የጌታ ልደት ተብሎ የሚከበረው በኢትዮጱያ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ እራሷ ከኮረጀች ከቀዳችባቸው አገራት ከ Graeco-Roman orthodox church ነው!ዛሬ ቀንን የጌታ ልደት በማለት የሚያከብሩት አገራት መካከል ራሺያ፥ ሰርቢያ፥ ላትቪያ፥ ሉቴኒያ፥ ግብፅ፥ ግሪክ ወዘተ ናቸው:: ይህ ቀን የተደነገገው በግሪኮ ሮማን ኦርቶዶክስ ቸርች ነው! አገር በቀል አይደለም! የተቀዳ ነው! እና ማንም በእነዚህ አገራት ተወልዶ የሚኖር እንደሰው ባህልና ወግ ይህንን ቀን ልደት ብሎ የመዘከርም ሆነ የማሰብ መብቱ የአንድ ሃይማኖት ጥገኝነት አይጠይቅበትም! የሰው ልማድና ወግ ነው አለቀ!

Graeco-Roman orthodox church የኢኪውሚኒካል (ecumenical ) ሙቭመንት አራማጅም ነች:: ይህ ማለት One World Religion በሚለው መድረካቸው ”ሁላችንም አንድ አምላክ ነው የምናምነውም የምናመለው” በሚል ሃሳዊ አጀንዳ የክርስቶስ ተቃዋሚ ክርስቶስ ነኝ ብሎ ብዙዎችን ሊያስት

“ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና። እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።” 2ኛ ተሰሎንቄ 2:3-4

መድረኩን እያዘጋጁለት ይገኛል! የተመረጡትን እስኪያስት የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነውና!

ታዲያ ከዚህ ማን ሊያመልጥ ሊድን ይችላል? በልባቸው ውስጥ ክርስቶስ የተወለደባቸውና መንፈሱ የታተመባቸው እነርሱ ብቻ ያመልጣሉ:: ፃድቁ ሰው እዮብ እንዳለ “ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።” እዮብ 19:20 ጭንቅ ነው ስለዚህም ነው ጳውሎስ “እራስህን እግዚአብሄርን መምሰል አስለምድ” ሲል ለጢሞቲዎስን የፃፈለት! ካለመዱት ክስሁኑ ኋላ ግዜው ግዜ አይሰጥምና!

እና የዛሬ ቡና ተጎዝጉዞ አረቄ ተደፍቶ የሚከበር ልደት በራሱ አጠያያቂ ነው:: እኛዋ አገር ላይ የጨለማውና የብርሀኑ አለም በጥምረት ለማሰራት በድርብ የሚንቀሳቀስ መንፈስ እንዳለ ይታወቅ! ቡና በሳር ጉዝጎዛ የሚፈላው ከየት መጣ? ከባእድ አምልኮ ነው! ቡና እየተፈላ አተላ እየተደፋ እጣን እየጨሰ ግብር የሚወጣለት ይህ የባእድ አምልኮ ዛሬ በጌታ ደም ታጥበናል በሚሉ ወንጌላዊያን ቤትና ቲቪ ሾው ሳይቀር ሰተት ብሎ ገብቶ ደርቦ ይመለካል ያለው:. ”ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ” ማርቆስ 7:13 እንዲል ቃሉ ዛሬ በብዙ ባህላችን ሰበብ ባስተላለፍነው ወግ ጂኒ የሚጠሩበትን የአህዛብ ልማድ ወደ ጌታ ቤተሰቦች ሰተት ብሎ ገብቶ ቅዱሱን መንፈሱን እያሳዘንን እንገኛለን! ባህላዊ ክፍሉን ወስደን እኛ ግን የሱስን እናምልክበት ልንል አንችልም:: ልክ እንደዚሁ ሁሉ የህንን የአንድ ምናልባትም የግሪክ ወይንም የሮም የኮንስታንቲን ድብቅ ሴራ በሃይማኖት ካባ የገባ አንድ ጣኦት የተወለደበትን ቀን ሊሆን የሚችልን ቀን ከቀኖች ሁሉ በላይ ልናደርገው አንችልም:: እርግጥ የሆነውን የውልደት ቀኑን ማወቅ ከፈለግን በልባችን ይወለድ!

በእርግጠኝነት ልናገረው የምችለው በውስጤ የተወለደበትን ዘመን ቆጥሬ ብቻ ነው:: ብርሃኑ የበራልኝና ከአስፈሪው የአለም ጨለማ የተናጠቀኝ ቀን ለእኔ ጌታ በዚያች ቀን በትንሿ ልቤ ገብቶ ተወልዷል እናም ይህንን የግሪኮ ሮማን ፔጋን ቀን እንደ አንድ አምድ ይዞ ለሚያውለበልብ የታሪክና የእውቀት እጥረት ሰለባ ስለወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሄርን ህግ ትሽራላችሁ እንዳለ አዳኛችን ስለወግና ስለልማድ ሲባል ክርስቶስን የአንድ ሃይማኖት ጥገኛ ማድረግ አይቻልም!

ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኃለሁ እንጂ ወደዚህ ሃይማኖት ግቡ ከዚህም ውጡ አልተባልንም:: ወደ እርሱ የመጣን ደግሞ ከየትም ነገድ ዘር ብንሆን እንኳን የሱስ ክርስቶስ ብቸኛው እውነት ህይወት መንገድ የጌቶች ጌታ የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነው ብቸኛው የመዳን መንገድ በሚለው ቋንቋችንን አንድ አድርጓል:: አዎን ደግሞም ይመጣል! አዎን ጌታ ሆይ ቶሎ ና!

ሊዲያ ዘ ወንጌል