እጅ ወደ ላይ

0
513

ትናንት በስተያ ያስነበብኳትን ፅሁፍ ተከትሎ ጥያቄ ቀርቦልኛል:: አይ ‘ደው እድሌ! ጥያቄው በትንቢት ቃል በህያው ቃሉ ስለ የተነገረ “የኢትዮጵያ ትንሳኤም” ሆነ በመልካም የሆነ የጉብኝት ግዜ እንደሌለ በማስነበቤ ነው:: ያም ብቻ አይደለም የመጨረሻው ዘመን መጠቅለያ ትንቢት (end-time prophecy- eschatological prophecy) ኢትዮጵያን ባማከለ ያለው ትንቢት “እግዚኦ” የሚያሰኝና እጅ ወደ ላይ የሚያስነሳ እንጂ የሚያንጎማልል እንዳይደለ ነው:: ኢትዮጵያ እጇ ባስር ማሰሮ ጠልቆ ወደ ላይ እንዳታነሳው ስራ ብዙ ሆናለች:: እጇን ታንሳ ብሎ በርሃብ ቢገርፋት ወደ ምእራባዊያኑ ትዘረጋና ጠኔዋን ኤክስፓየር ባደረገ ስንዴ ትሞላለች:: ነውጥ ሲያስነስባት እርዱኝ ብላ ወደ እንግሊዝ ወደ አሜሪካን ትዘረጋለች:: ደጅ ትጠናለች:: ችጋር ሲቆላት አቆራርጣ ሄዳ በስደት በየአገሩ ትመስጋለች እጇን እንዳጠፈች::

ጥያቄውም ይህንኑ እጅ ወደላይ የተባለበትን የማስማረክ ጥቅስን ከመዝሙረኛው ዳዊት መዝሙር ላይ ተንተርሶ ነው:: ‘ኢትዬጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች’ የተባለው ምን ማለት ነው” ይላል አንባቢዬ….

ጠያቂዬ ሰለሞን ብርሀኔ ወንድሜ ሆይ:-

ዳዊት በመዝሙሩ “ኢትዬጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” ሲል ምን ማለቱ ነው’ ላልከው እስኪ ሙሉ ቃሉ እንመልከት:: “መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” ይላል::

የግብፅ መኳንንት እንመልከት በመጀመሪያ:: በተደጋጋሚ ግብፅ ፥ ኢትዮጵያ፥ ፉጥ፥ ሉድ አንድነት በተራ ቅደም ተከተል እየተሰለፉ የእግዚአብሄር ቃል በትንቢት ሲናገርባቸው እንመለከታለን:: በቅዱሱ ላይ ከጥንት ጀምሮ የሚያጉረመርሙ ግብፃዊያን እስራኤልን ጭሰኛ ያደረጉ፥ በባርነት የገዙ ሲሆኑ አምላካቸው እግዚአብሄር በፀናች ክንዱ ከእግር ብረት ቶን አስፈትቶ ያመልኩት ዘንድ ቢለቃቸው የግብፅ መኳንንቶች ግን አሻፈረን ብለው መለስተኛ አርማጌዶን በሰማይ ካለው ጋር ማካኄዳቸው አይረሳም:: ሆኖም “ሙሴም ለሕዝቡ፡— አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።” ዘፀአት 14:13 እንዳለ ….ባህርም እንደ የብስ ሆነች፤ እስራኤልም በደረቅ ምድር ተሻገረ:: ግብፅና መኳንንቱ ይህንን ህዝብ ወደ ባርነት እኛን ወደማገልገል እንመልሳለን ሲሉ ተከትለው በባህር ገቡ ሆኖም በባህር ጥልቅ ፈረስና ፈረሰኛውን ሰጥሞ ቀረ:: እንደ ግድግዳ የቆመ ውሃ ተከለበሰባቸው:: ጥልቅ ዋጣቸው! ሙሉ ታሪኩን ዘፀአትን ማንበብ ለበለጠ ግብንዛቤ ይረዳል:: እና እነዚህን እኛ የምድር አማልክትና መኳንንቶች ነን የሚሉ ግብፃዊያንን ከእግሩ ፊት ትምክህታቸው ተሰብሮ ሊመጡ ቀነ ቀጠሮው ገና ነው:: ሕዝቅኤልም 29:9 እንደሚናገር በመጪው ዘመን “የግብፅም ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ አንተ፡— ወንዙ የእኔ ነው የሠራሁትም እኔ ነኝ ብለሃልና። ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።” …እያለ ይቀጥላል:: ግብፅን ከመንግስታት ሁሉ በታች ታናሽ ትሆን ዘንድም በሌላ ስፍራ እዲሁ ተነግሮባታል:: ያልተወራረደ ሂሳብ ከዛ ከጥንት ትእቢቷ ጀምሮ፥ የበደል ላይ በደሏ ይከፈላት ተብሎ አለ ገና:: በፀናች ክንዱም ትደቆሳለች:: እናም “መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ” አዎ እነዚህ መኳንንት ነን የሚሉ ይመጡና በንጉሱና በተመረጡት ህዝቡ ስር ይሰግዳሉ:: በተራቸው በጫንቃ ላይ ተሸክመው የስራኤልን ልጆች ያገለግላሉ:: የመዝራትና ማጨድ ህግ አለም እስካለ ቀጣይ ነውና!

ኢትዮጵያን ወደ ሚያነሳው ቀጣይ የጥቅሱ ክፍል ስናልፍ ደግሞ “ኢትዮጱያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” ይላል:: ይህ የሚያሳየው ኢትዮጱያ እጆቿ እንዳልተዘረጉና ሆኖም በሂደት ግን እጇን እንደሚያዘረጋ ያሳየናል:: በሂደት በምታልፍበት መንገድ ውስጥ ወዳም ይሁን ሁኔታዎች አስገድደዋት እጅ ወደ ላይ እንደምታነሳ ተተንብዮላታል ማለት ነው:: እጆቿ አልተዘረጉም ማለት ነው ባጭር ቃል:: ሆኖም ትዘረጋው ዘንድ ትመከራለች:: እጅ ወደ ላይ አስደርጎ የሚማርክ አለ! እጆቿን ትዘረጋ ዘንድ አስገዳጅ አለ:: እጇን እንዳትዘረጋ ያቀፈቸውን ትምክህቷን የሚያስጥል አለ:: “እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብፅ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤” ኢስያስ 20:5

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከተጠቀሰችባቸውን ጉዳዮች ስንመለከት በመሲሁ ላይ ያመፀች አገር ሆና እናገኛታለን:: በዚሁም ምክኒያት ለኢትዮጵያ የተፃፉ የዘመን ፍፃሜ ትንቢቶች “ማረን ጌታ ሆይ” ብለን የምንማፀንበት በንስሃ ሱባኤ የምንገባበት እና ብቸኛው የማምለጫ ከተማና የዳኛዋ መንገዷን የሱስ ክርስቶስን አዳኟ ማድረግ ነው:: አዎ የጌቶቹን ጌታ፥ የነገስታትን ንጉስ፥ ብቸኛ አዳኝ የሆነውን፥ በአብ ቀኝ የተቀመጠውን፥ የምስጋና ዘውድ የተጫነለትን፥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ” ብሎ አብ ያከበረውን፥ ስለእኛም በአብ ቀኝ የሚማልደውን፥ አለም ሳይፈጠር በነበረ ክብሩ አብ ሲያከብረው “እኔም የሰጠኸኝን ልጆች እነሆ በወደድከኝ መጠን ወደድኳቸው” ብሎ በወደደን በዚህ አዳኝ ስር እራሷን አዋርዳ ብቻ ትድን ዘንድ አላት! አሊያ ትምክህት ይሰበራል:: በሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ፈንታ ሶስት ቢሊየን መከራ ትከናነባለች! ተከናንባለችም:: ከአልተገዛሁም እራስን ማስካድ ቀረርቶ ይልቅ ቶሎ በርከክ ብላ ለእርሱ ባትገዛ የምትሮጥበት የጥፋት ሜዳ ድጥ ይሆናል:: ከድጥ ያመለጠ ጉድጓድ ይውጠዋል:: ጉድጓድ ያላገኘውን ባህር ያሰጥመዋል:: የተሰደደውን ጎግ ይገዛዋል::

***እጅ ወደ ላይ፥ ፊት ወደ ክርስቶስ ፥ እግር መሬት ይዞ ቶሎ በፍጥነት በረከክ…..***

ኢትዮጵያ እጆቿ ስራ በዝቶባቸው ጉድ ጉድ ላይ ናቸው:: የራሷን ገድል ትፅፋለች:: ሲላትም ከተመረጡት በላይ ብፁህ ልትሆን የሚዳዳት የራሷን ሹመት ፈጥራ ካህናቷን ደርድራ ለራሷ ያስተነበየችበት ገድላት አሉዋት:: እራሷ ኢትዮጱያ “ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ” የምትልበት ድርሳን አላት:: “ከተፃፈው አትለፍ” የሚለውን ቃል ተላልፋ ብቻ ሳይሆን ተረማምዳበት ብሎም “በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤” ራእይ 22:18 ተብሎ የተፃፈን ቃል “ወዲያ በሉ” ብላ የራሷን ፊጥሞ ደሴት ስትሰራና በራሷ ተመስጦ ብዙ መፃሃፍትን የደረሰች እና እየደረሰች ያለች ቃል አባይ አገር ነች:: ትንሳኤውን እንዳታስብ የራሷን “የኢትዮጵያ ትንሳኤ” አለ ትለናለች:: መሲህ በደመና እንደሚመጣ እንዳታወራ “ሳልሳዊ ቲዎድሮስ መጥቶ አገሪቱን ፌሽታ በፌሽታ ያደርጋል” ትለናለች::

ነገሩማ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ካልን እኮ ወይን ልትሞት ነው አሊያም ኦልሬዲ ሞታለች ማለት ነው:: በሞት ጎዳና ላይ ጉዞ ተያይዛ እነሳለሁ እኔም እንደ ክርስቶስ እያሉ ማለት ምፀት ነው!…… ድርሳኗን ስናገላብጥ ደግሞ ጌታ ስለ እኛ ኃጢያት ከፈለ ከተባለው ዋጋ ሲነፃፀር ” ዋጋ ከከፈሉ አይቀር እንደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ” የሚያስብል የክርስቶስን የማዳን ስራ ልታደበዝዝ በምናባዊና አነሁላይ horror movie ለምኔ የሚያስብል ለፊልም ስክሪብትነት ተወዳዳሪ የማይገኝለት ገድል ታስነብባለች:: አንድ ካነበብኩት ገድል መኃል እንዲህ ይነበባል “በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድል ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ጻድቁ በዝቋላ ገዳም ላይ ‹‹የኢትዮጲያን ሕዝብ ካልማርክልኝ ከዚህ አልወጣም›› በማለት በገዳሙ ውስጥ በሚገኘው ባሕር ውስጥ በመግባት ተዘቅዝቀው ለመቶ ዓመት ጸልየዋል፡፡ በዚህ በመቶ ዓመት ውስጥ አጋንንት በየቀኑ ከአራቱም አቅጣጫ በመምጣት ከባሕር እንዲወጡ፣ለእኛ ለኢትዮጲያውያን የሚጸልዩትን እንዱያቋርጡ በክፉ ፍላጻዎቻቸው መላ ሰውነታቸውን ይነድፏቸው ይወጓቸው ነበር፡፡ ይህንን መከራ የሚያደርሱባቸው የአጋንንት ቁጥሮች ሰባት መቶ ሺ ሦስት መቶ ነበሩ፡፡ እነዚህ አጋንንቶች ይህ አልበቃ ብሏቸው የጻድቁን አጥንት በሻፎ/ሱፋጭ/ ድንጋይ ይፈጩ ነበር፡፡” …….ብላ ከክርስቶስ በላይ ፅድቅ የሰሩ ሰዎችዋን ስትደረድር ጌታ “ተፈፀመ” ያለበትን የማዳን ምስራች ስራ “ተፈፀመ” ከሚል ይቀጥላል (to be continued) አድርጋ መሆኑ ነው:: ብዙ episodeዶች ሰርታ ማለቂያ ጠፍቶታል:: የጌታም የመስቀል ሞት እዳችንን ከፍሎ በማያዳግም ሁኔታ ላንዴም ለመጨረሻ እንዳልተዋጀንና በገዛ ንፁህ ደሙ የኃጢያታችን ስርየትን እንዳላገኘን ሁሉ፥ ወደ ሰማየ ሰማያት ወደ ቅዱሰ ቅዱሳኑ እንዳልገባና መልካም ጣፋጭ የመአዛ ሽታ ሆኖ በሰማይ እለእኛ ተሸትቶ ኪዳኑን በደም እንዳላፀናልን ሁሉ እነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ክርስቶስ ሰምራዎች ከጌታ በላይ ሊፀድቁና ቅዱስ ከተባለው በላይ ቅዱስ ሲደርጉ መቶ አመት በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው እንደፀለዮ ትናገራለች ኢትዮጵያ:: የራሷን ክርስቶሶችና ወንጌል ፅፋ ፅፋ የማያድን የአዳኝ ብዛት አይጣል ነው! ከአለም እራሱን ያስታረቀበት የምስራች ዜናው እያለ ኢትዮጵያ በራሷ የምስራችን ዜና በጭንቅላት ተዘቅዝቆ ከመፀለይ ባንድ እግር ቆሞ ለዘመናት መማለድ (ባይ ዘ ዌ ይሄ የቡድሃ እምነት መጠቅን ሲሉ የሚደርሱበት የምጥቀት ከፍታ ነው:: የእባቡ ኃይልን ተቀብለው የሚደርሱበት የሂዱኢዝም የእምነት ሂደት ነው:: They do this by raising the serpent from the bottom of their spine- kundalini spirit. They believe there is a serpent coiled up in the base of their spine. ከታችኛው ከጀርባ አጥንት መቀመጫ በተለምዶ tail ተብሎ ከሚጠራው ክፍል እባብ ተኝቶ አለና በተለያዮ ተመስጦዎች እና ሂደቶች እባቡን አስነስተው በጀርባ አጥንታቸው ላይ መወጣጫ በማድረግ እስከ ጭንቅላታቸው ድረስ ይመጣና የሶስተኛ አይናችንን ይከፍትልናል ብለው ያምናሉ:: በረጅም ግዜ ልምምድ ለዚህ ሰይጣናዊ ድቁና ሰውነታቸውን ማደሪያ የሚያደርጉበት የሃይማኖት ጉዞ ነው:: ከዛ ሶስተኛ አይናችንን ያበራልናል ያም ከሌላ ዳይሜንሽን ያለውን እንቅስቃሴ ማየት መስማት ያስጀምረና ይላሉ:: መፃሂ የወደፊት እጣ ፈንታቸውንም እራሳቸው አቅጣጫ ማስያዝ እንደሚችሉ ያምናሉ:: ሆኖም ጥናቶች እንደሚያሳዮት የዚህ እምነት ተከታዮች መጨረሻቸው ጀዝባና ካእምሮዋቸው ውጪ ይሆናሉ:: ዝም ብለው በጥንታዊ Gnostics and mystical በሆነ የአጋንንት አለም ወሬ ሲያወሩ ይውላሉ:: ስለ መሰወር፥ ድምፆችን መስማት፥ energyን tap ማድረግ የሚል የአጋንንት ዝክር ሲዘክሩ ይውላሉ:: ባጭር ቃል የእብደትን መንገድ እንደ ብርሃን መላእክ መስሎ በሚያስተው አሳች በመታለል መንፈስ “በራልን” “awakened” ሆንን በሚል ጀምረው አንዴ አጅሬው በቁጥጥሩ ስር ካደረጋቸው ኃላ በሂደቱ ፍፃሜ እብዶችና ከሰውነት ተራ የወጡ የአጋንንት መፈንጫ ይሆናል አካላቸው) እና አቡነ ተክለሃይማኖትም በእባብ ሃይል ገዳማቸው ላይ ተስፈንጥረው እንደወጡ ይናገራል ገድላቸው:: ዘንዶው ገዳሙን መስራት ሲያስቡ ከገዳማቸው ላይ እንዲወጣጡበት እንደ ገመድ ሆኖ እንዳወጣቸው ገድላቸው ይተርካል:: በአንድ እግር እስከ መቆምደረስን ይላሉ እግዜሩ ሁለት እግር ሰጥቶን በአንድ እግር ቆመን እንፀልይ ዘንድ የሚፈልግ ክፉ ሲያስመስሉ:: ባንድ እግር የሚያቆም በጭንቅላት የሚዘቀቅዝቅ ክፉው ነው:: ሰውን በሃምሳሉ የፈጠረን ጌታ ግን ፈጥሮ ሲጨርስ የህይወት እስትንፋሱን እፍፍ ብሎበት ህያው ሰው አርጎ በመልኩ አቆመው መልካም እንደሆነም አየ ይላል:: “ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው በሉት” በእግሬ እንድቆም ሰርቶ ለምን በጭንቅላቴ እንድዘቀዘቅና እንድፀልይ ይፈልጋል ጌታ? ባፍንጫ መተንፈስ ጀምረሽ በጆሮሽ ተንፍሽ እንደማለት አይሆንም? አቅሙንስ ችሎታውን የት ተገኝቶ ይህ ይሆናል? እንዴ በእግራችን መቆማችንን አልፀፀተው ስለምን በጭንቅላት መዘቅዘቅ ብፅህና ሆነ:: ይልቅ “ልጄ ሆይ ሰው ሁን” እንደሚል ቃሉ ሰው ሆነን እንደሰው ግብር እንድንኖር ያዛል ቃሉ;; ውሃ ውስጥ ግማሽ አካል አዘፍቆ የሚያኖርና የሚያፀልይስ የትኛው መንፈስ ነው? ሰው አርጎ ሰርቶ ግማሽ አካልን አሳ ነበረች የሚሏት በሩቅ ምስራቅ “mermaid” የሚሏት የባህር አጋንንት ነች:: መዋኘት እንኳየማይችል ህዝብ ነው እንግዲህ እንዲህ አይነት ገድል ሲቀዳ ሲተረጉም በጥራዝ ሲጠርዝና አገራዊ ሲያደርግ የሚወለው!:ወይ ግሩም! ምንም መፅሃፍ ቅዱሳዊነት የሌለው ግብር:: this diety is a hybrid of some sort, which is an utter abomination! This kind of ገድል suggests a contaminated seed, or human intermingled seed with other species. Now that is demonic! ነገሩማ አልስተር ክራውሊን እኮ የፍሪመሲነሪን መስራች በዚህ እውቀት ኢትዮጵያ ነች ያጠመቀችው:: ዛሬ ከወደቁ መላእክት የተለያየ እውቀት ጥበብ ወዘተረፈ የሚቀስሙበት ጥራዝ ከኢትዮጵያ አግኝቶ ሰርቆ ይዞ እንደሄደ ይታወቃል::

እና ይቺ እንግዳ ምድር እጆቿን ብዙ ቦታ አጥልቃ ትገኛለችና ልኡል በቃሉ “ኢትዮጱያ እጆቿን ወደ አምላክ ትዘረጋ” ይላታል:: ይህ ማለት ከነዚህ አጉል ትምክህትና የሶስት ሺህ አመት ታሪክ ጉራ፥ ከጥንት ሃይማኖቴ ምፀት ወጥታ ከሃይማኖቷም በላይ ከማንነቷ ታሪኳም ሁሉ በላይ የያዘቸውን ጥላ እጅ ወደላይ ተብላለች ልትማረክ:: የኢትዮጵያ እጆች የያዙትን ቅራቅንቦ አስራግፎ ወደ ላይ ያስነሳል:: የሶስት ሺህ አመት ታሪክ ብለን ልንደነፋበት የምንችለው በአውሮጳዊያኑን ብቻ ካልሆነ በቀር አካባቢያችን ያሉ አገራት ኑቢያ ነሽ መዛሪያም (ግብፅ) ፉጥ ይሁን ሉድ ፥ እስራኤል ይባል ኢራን ፥ ኢራቅ ነው ህንድ ወዘተ ወዘተ የሶስት ሺህ አመት ታሪክ የሌው ኸረ ማን ይሆን??

እውቁና ባለ ጥኡመ ዜማው መረዋው ደረጄ ከበደ እንደዘመረው

አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ

ባጥንቴች ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ

የምድረ በዳው ኑሮ ይበቃኛል

እጆቼን ላንሳ ዛሬስ ማርከኸኛል

ተማርኬአለሁ 1000x ….

እያዘመረ እጅ ወደላይ አስነስቶ ምርኮኛ ያደርጋታል:: የያዝኩትን አለቅም ብላ እጅ ባታነሳ መቀመቅ ይከታታል:: መች ከመቀመቅ ወጥተን እናቅና እንዳትሉኝ ብቻ … የሶስት ሺህ አመታ ታሪክ ባለቤት ኢትዮጵያ ብቻ ትመስል የሞኝ ዜማ ታዜማለች:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቅዱሳን የተደረጉ ድርሳን የተፃፈላቸውን በሌላ ስም ዞር ብለህ ይህንኑ ገድል በድርሳን ተጠርዘው በህብር ተሸልመው ይገኛሉ:: ሁሉም የተቀዳ ነው:: በኢትዮጱያ በግእዙ አለ የምንለው በሂብሩም ፥ በአረብኛም ፥ በሳንክሪስት ፥ በባቢሎንም ፥ በግብፅም ፥ በግሪክ የሚገኝ ነው:: እኛ በግእዝ ስለጠረዝነው የኛ አይሆንም! መሰረቱ ባቢሎን ነው:: የጥንት Gnosticism and mythicism ነው “ከፀሀይ በታች አዲስ ነገር የለም”

ስለውቅር ቤተ እምነት ከሆነ ሂድ እነ ፔትራን እይ ፈዝዘህ ትቀራለህ:: ሂድ አፍጋኒስታን አክሱምን ትረሳዋለህ:: ሂድ ኢራቅ ግባ ፥ ኢራን ውረድ ፥ በሶሪያ እለፍ ፥ በየመን አቋርጥ ፥ በግብፅ ውጣ ፥ ወደ ግሪክ ግባ ካልደከመህ ደግሞ ላትመለስ ትችላለህ እንጂ ሂድ እስያ:: ቻው ቻው! እስያ ገብቶ በቀላል መውጣት የለም:: ህንድ ብቻ ከሶስት ቢሊየን በላይ አማልክት አለልህና ገድል ስታነብ አይንህ ሟምቶ ይፈስል:: ቅርስ ስታይ ዘመንህ አልቆ ይጠቀለላል:: እራስህ አንተን ካልደከመህ ሰይጣን እራሱን የብርሃን መላእክ እስኪመስል ሊለውጥ ተፈልፎሎ ተደቃቅሎ በየገድልና ድርሳናት ታገኘዋለህ:: ግን ከዚህ ሁሉ ልፋትህ ”እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አይደለሁም ሰማይና ምድርን የሞላሁ እኔ ነኝ” ያለውን ባለህበት በርከክ ብለህ በቃሉ አግኘው የክብርን ተስፋ!

ኢትዮጵያ ደም ከማፍሰስ ታቅባ ፥ ሰው ማሳደዷን ትታ ፥ ክርስቶስን መገፍተር አቁማ ወንጌሉን እስክትከፍትና እጆቿን ዘርግታ እስክትጎበኝ ድረስ ቸር ሰንብቱ!

Lydia Ze Beloved Daughter Yah