ስለ ዓለም አልለምንም *********************

0
421

ስለ ዓለም አልለምንም

*********************

“እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤” ዮሃንስ 17:9

ስለአለም ሰላም ፀልዮ ያለው ማን ነበር? ቄሱ ነበር ፓስተሩ?! ኦ ኦ ያ ሁለቱም!

ሆኖም ቅዱስ ቃሉ እንደሚያሳስብና ይሆን ዘንድ በትንቢት እንደተቀመጠልን ሰላም በመጨረሻው ዘመን ብርዬ እና ድንቅዬ ከመሆን እንደ ዳያኖሰር ( ዳያኖሰር ብላ በራሪውን እባብ ሌዋታንን ቢሆንም ቅሉ በዚህ አሳቻ ስም አለም አሾልካ (academiaም ተባብራ) አግብታ የጠፋው ብርቅዬ እንስሳ ትለናለች… በጥልቁ ታስሯል እስከሚፈታበት ቀን ድረስ ፤ የትም አልጠፋም:: የእፉኝት ልጆች የተባሉት ልጆቹ ዛሬ በoffshore drilling ስም ነዳጅ እናውጣ ሰበብ ማእድን ፍለጋን ተገንና ሽፋን አድርገው የምድርን ከርስ አልፈው crust መስበር ቢችሉና ከጥልቁ ሊፈቱት ይመኛሉ ፤ አልቻሉም አይቻልምም እንጂ:: ወደ ሰማይም ይተኩሳሉ ሳተላይት ልናመጥቅ ገለመሌ በሚል ሰውር ደባ ሮኬቶች ይወረወራሉ የሰማይን ጠፈር መስበር ብንችል ብለው ልፋ ያለው… “የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።” ዳዊት 2:2 ልኡል በማደሪያው ሆኖ ይስቅባቸዋል አንዱም ልፋታቸው እንዳይከናወን ያውቃልና) ….. ወደ መጥፋት ይደርሳል:: እየደረሰም ነው!

እና ወደ ነገሩ ስመልሳችሁ ጌታ ለራሱ ለሆኑት ፀጋውን ያበዛል:: እስከመጨረሻ እስከሞት የታመንክ ሁን እንደሚል ቅዱስ ቃሉ እስከሞት የታመንን እንድንሆን በመጨረሻው ዘመን ጥፋት ውስጥ የምናልፍ እያለፍንም ያለን መሲሁን የምንጠብቅ እኛ ሰላምን ሊሰጠን በምድር እንጠብቀው ዘንድ ፥ ለአለም ተላላዋ ሰላም ይሰፍንላት ዘንድ ልንፀልይላት በዚህ የለንም:: ሰላም ሳይሆን ሰላም ልንልና “የሰላም ንጉስ ነኝ” ብሎ አምላክ ከተባለው ከሚመለከው በላይ እራሱን ድርጎ ለሚቀመጠውና ያዳምን ልጆች ሊያስት ለሚመጣው ሃሳዊ መሲህ መንገድ ሰላም እያልን አንጠርግም:: ሆኖም የይሁዳ አንበሳ ሞትን ድል የነሳው በአምባው ላይ ፈረስ ተቀምጦ ሰይፉን ስሎ በብረት እንደ ሸክላ እቃ ሊቀጠቅጠው የሚመጣውን የካህናት አለቃ ፥ ስሙ ድንቅ መካር ፥ የዘላለም አባት: የበጎች እረኛ የተባረከውን ተስፋችንን ይፈርድ ዘንድ ስለሰማእታት ሃዋሪያቱ ደም “አቤቱ ተነሳ ጠላቶችህም ይበተኑ” እያልን ማራናታ ጌታ እንለዋለን እንጂ ሰላምን ከክፉዎች መንደር ከጨካኞች ዙፋን እንደፍርፋሪ አንለምናትም አንመኛትምም! የሰላም ንጉስ የሱስ አዳኙ እራሱ ሰይፉን በደማቸው ካሰከረና ልብሱንም በደማቸው ካቀላ በኋላ በመጨረሻም የአብ ቃል የተባለው ከሱ ከምድኃኒታችን አሁን በዚህ ውጥንቅጥ መካከል እንደተቸርናት ሰላም ደግሞ ትበዛል ዘንድ ገና አላትና::

የነፍስችን ምስራች ነጋሪ ፥ አዳኝና መሲህ ፥ የምንጠብቀው እርሱን እንጂየዚህች አለም ተስፋን አይደለም:: የኢትዮጵያንም ትንሳኤ አይደለም:: እንኳን ትንሳኤ አግኝታ ሞታም ደማችንን ከመምጠት የማትታቀብ መተተኛ ምድር ናት ኢትዮጵያ! ለኢትዮጵያ ሳይሆን ትንሳኤ በቃሉ ተስፋ የተደረገላቸው በደሙ ታጥበው የመንፈሱን በኩራት ለተቀበልን እንጂ ብሎም እንዳንበሰብስ ለሆንን ያንኑ ክርስቶስን የሱስን ከሞት ያስነሳውን መንፈሱን ለጠጣን እንጂ፤ አለምም ሆነች ኢትዮጵያ ለትንሳኤ ሳይሆን ለጥፋትና እሳት ተቀጥራለች!

የክብርን ተስፋ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ፊታችንን ወደ ጌታ ዞር ብናደርግ ግን መጋረጃ ሁሉ ይወሰዳል ክብር ከሚሆን ጌታም በማይከደን ፊት እያየነው ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን!

ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ እንደሚል ህያው ቃሉ እልከኛ አንሁን! መታዘዝ አምልኮ ነው! መታዘዝ የሌለው ህይወት ጌታን አያውቅም አያመልክምም ሊያመልከውም ተስኖታል:: እሱ ግን በመስቀል ሞት መታዘዝን ተማረ ይላልና ቅዱስ ህያው ቃሉ በአባቱ ፊት የምወደው ልጄ ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ የተሰችበት የመረጥሁት ባርያዬ ፥ የተባለለት እስከ መስቀል ሞት የታዘዘ ሆኖ ነው:: እንታዘዘው ዘንድ ልባችን ፈጥኖ የሚታዘዝ እንዲሆን እንፀልይ!

ክርስቲያኖች በመጨረሻው ዘመን ስደትና መከራን ስለ እምነታችንንና ስለክብር ተስፋችን ለየሱስ ክርቶስ መሲህ አዳኛችን ስንል አንገታችንን እንኳ ልንሰጥ አለን እንጂ ክርስቲያናዊ ጂሃድ ግን የለንም! ሰሞኑን ግን አንዳንዶች የክርስትና ጂሃድ ዋህቢያን ሆነው አርፈውታል:: በየትኛው ቃል ተደግፈው ይሆን “ለኢትዮጵያ የተለየ ተስፋ ትንሳኤ አለ” የሚሉን? ዳግማ እየሩስሌም ናት የተባለችው ኢትዮጱያ የት ቦታ ቅዱስና ህያው ቃሉ እንዲህ ሲል በመፅሃፍ ተናግሯልና ነው? ስለኢትዮጵያ በመጨረሻው ግዜ በቀጥታ የተተነበየውንማ ከቅዱስ ቃሉ ካየን እግዚኦ ማረን የሚያሰኘን እንጂ ምንም መልካም ነገር የለም!

የተስፋ ሁሉ አምላክ ከተስፋ ለራቃችሁ ወደ ተስፋው የሚጣራበት የየምስራች ዜናው በያላችሁበት ይደረሳችሁ!

ጌታ ይባርካችሁ!