ከፀኃይ እንቁስላሴ እስከ እኔ

0
1161

አማራ እስኪነቃ ዳግም ምፅአት ይሆናል:: አውቆ የተኛ ነዋ ነገሩ! ከደጃች ፀኃይ እንቁስላሴ እስከ እኔ ድረስ ለፈፍን ሰሚ የለም! ከሞቱ ወይ ከኄድን ኃላ “ብሎ ነበር ብላ ነበር” ቢባል ምን ዋጋ አለው! ዝም ብሎ እራስን መሸንገል?! ሁሉም ሰምቷል የሆነውንም የሚሆነውንም ሁሉም ያውቃል::

ብላ ነበር ለመባል እኮ አልነበረው ጩኸቴ፥ ትንተናዬ፥ ሙግቴ፥ ቁጣዬም ሰብሰብ ቶሎ ብሎ ጥፋትን ለመታደግ ነበረ እንጂ:: ነቅተህ ቆመህ ለመታገል ሰንፈህ አንድ ግዜ ግምቦት ዜሮ፥ አንዴ ተታለኩኝ፥ ተሸወድኩኝ፥ ቅብርጥስ እያልክ ስታምታታ ትውላለህ::

የበቀለ ገርባ ዛሬ ያቦነነው አቧራ እንኳን ምክኒያቱ ግልፅ ነው! ምክኒያቱ አማራው አሁንም ተስፋ የሚያደርገው እነዚህን የሌላ ብሄሮች አለቆች እንዲሰበስቡት ስለሆነ ነው! የዛሬው የአማራው እዬዬ እስካሁን ተስፋው በነበቀለ ዙሪያ እንዳልተቆረጠና ነገ በቀለ ከፈለገ ማድረግ ያለበት “አይ እንዳውም ሳስበው ኢትዮጵያ አንድነት ይሻላል” ማለት ብቻ ነው:: እንደ አብይማ ተረት ከጨመረበት “ስንቀመጥ ኢትዮጵያዊ ስንሮጥ ኢትዮጵያ ነን” ምናምንማ ካለ ሞተ ነገሩ! አማራው አሁንም ተሰባስቦ “መሪ የለንም” የሚለው እነኝሁን እነበቀለን፥ እነ መራራን ወዘተ እትትት ብለውት እስኪመጡለት ነው:: መሪ ማውጣት እራሱ እንቅስቃሴው እራሱ አይፈልግም እንደማየው ከሆነ! ዛሬም ዛድጊ የተባለን ትግሬ የራያ ማሊያ አልብሳ ወያኔ ብትሰደው ኢሳት እንደለመደው የፕሮፖጋንዳ ስራውን ጀምሯል! ለምን? ምክኒያቱም ቁጭ ብሎ ወሬ እያዳመጠ አይምሮውን የሚያስጠበጥብ ከአማራው ሌላ ስለሌለ ነው:: ነገ ዛድጊ ሌባ ነው ምናምን ቢባል ተነስቶ ልግደልሽ የሚለው አማራው ነው:: ሌላ ማንም አይደለም! የፈለገ እየመጣ የሚፈነጭበት ህዝብ! ከወያኔ ጉያ የወጣን ይህንን ሌባ እንኳ ያሾራችኃል ብቻውን ጦር ሳይመዝ! ለአማራው መተረት ብቻ ነው የሚያፈልገው! አለቀ! አባይ ፀሀዬም ከፈለገ መጥቶ ” አማራ እኮ ትልቅ ህዝብ ነው እኛ አጥፍተናል ደረረረ” ማለት ከዛ አለቀ! …. “እስኪ ለመቃወም አቸኩይ … አንቺ ደግሞ አሁን ሊቀየር አይችልም እንዴ… ተፀፅቶ ቢሆንስ?…..”. ይኼ ነን እኛ! እኔን ለመስደብ ግን አፉ የማይሾል የለም! ለምን ግን? አማራ ነኛ! ይኼኔ ኦሮሞ ወይን ትግሬ ብሆን አማራው እራሱ ጋብዞ ፖለቲካ ተንትኝልኝ ይለኝ ነበር:: ነገሩ ኦሮሞ ወይን ትግሬ ብሆን by now አንዲት ትንሽዬ ስልጣን ቢጤም አላጣ ነበር: ወይ ነዶ 😅

ለጉራጌ ደጋፊ ለመሆን የራሱን ሁሉ ታሪክ በመቸር ያሽቃብጣል አማራው:: ሶማሊን አጋር አድርግ ስትለው አብድረህማን ፕሬዝደንቴ በማለት ጭራ ይቆላል:: እረ ልክ ይኑረን?! ጀዋርን ጃኖ አልብሶ በአማራ ምድር ያንጎማለለው አማራ ቀና ብትል በሜንጫ ነው የምልህ የሚለውን የጥፋትን ልጅ ነው:: አሁን ይኸው በምድር ላይ እንደ ጃኖ የሚያስጠላኝ ነገር ይኸው ጠፋ በዚህች ምድር ላይ! ብርሀኑ ውልቅልቅ ብላ አርጅታና ድርጅቷ ፈርሶ እንኳ አማራ ምድር ትደመምበታለች:: ይንቃ! ወይ ይንቃ ነቅቶማ አለ! ነቅቶ ሰው አንጋሽ ነው:: የራሱን ማውጣት መች ሆነለት ሰው በጠመቀው ጠጅ ይሳከራል እንጂ “አንድ ነን” እያለ!

ትንሽ እንስራ ሲባል ሁሉም ወገቤን ይላል አዳሜ! አሁን አሁንማ በየሚዲያው rhetoric ማሰማት ትግል ያ ሆኖልኛል:: እንጅብራ ላይ ግምቦት ዜሮ ፈርሳ ሊያውም እያንጀባረረችው ነው:: ከዚህ በባዶ ቂጣቸው ገርፈን አባረናቸ ሲያበቁ አገር ቤት ገብተው በጨበጣ የሚቀልዱበት ይኸው የኛኑ የራሱን የሚያጥላላ የሰውን ሰው አናቱ ላይ የሚጭንን ሞገደኛን ነው!

እኔ ተነስቼ በቀለ ገርባ ያለውን ግጥም አድርጌ ብናገር “ሌላ ቋንቋ አትናገሩ” “አማራ ጋር ብቻ ተጋቡ” ምናምን ብል no Oromo or Tigray will blink. እና! ታዲያ ድሮ ምን ታስቦ ነበር ነው የሚሉት ቢበዛ! እኛ ጋር ደግሞ አማራ ብሎ ተሰባስቦ ኦሮሞው ብሄርተኛ ለምን ወገኑን በራሳችሁ ቋንቋ ብቻ ተናገሩ አለ ብሎ ፍራሽ ዘርግቶ ልቅሶ ይቀመጣል! የተወዛገበ …..

እዚሁ ግን ውሎ የሚያድርበትን ፌስቡክንና ትዊተርን ለማንቃት ብሎም awareness ለማግኘት እንስራ ሲባል ወፍ የለም:: ትናንት በስተያዋ ጥሩ ማሳያ ናት!

ተደራጅ ማለትን ከደጃች ፀኃይ እንቁስላሴ እስከእኔ ድረስ ሞከርነው አልሆነም! ባህርዳር ላይ የፈረሰችው ግምቦቴ እንኳ ሄዳ ፈስታበት ትመለሳለች::

ሊዲያ ዘውዱ