የቄሮ አለቆች መሰረታዊ ችግር ራስን አለማየት ነው

0
1186

የቄሮ አለቆች መሰረታዊ ችግር ራስን አለማየት ነው

1) የተሳሳተ የራስ ምስል፡-

እንደሚታወቀው የኦሮሞ ተቃውሞ ከአማራ ተቃውሞ በአንድ አመት ይቀድማል፡፡ ሲሞቅና ሲቀዘቅዝ ቆይቶ ጭራሽ ወደተስፋ መቁረጥና መክሰም ሲያመራ የአማራ አብዮት ተጀመረ፡፡ የአማራን አብዮት መጀመር ተከትሎ የኦሮሞ ተቃውሞ መልሶ አገረሸ፡፡ ከአማራው አብዮት የትግል ስልቶች በመማርም ራሱን አሻሽሎ ህወሀትን ወደመጋፋት አደገ፡፡ በአማራ አብዮት ቅስሙ የተሰበረው ህወሀት የማያንሰራራበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ኦህዴድ ወደስልጣን መጣ፡- ለኦህዴድ ወደስልጣን መምጣት ሶስት ምክንያቶች ነበሩ፡፡

ሀ) ህወሀት ኦህዴድ ውስጥ ብዙም ቀጥተኛ ጫና አልነበረውም፡፡ በአንጻሩ በወቅቱ የነበረው ብአዴን ራሱ ህወሀት ነው ማለት ይቻል ነበር፡፡ በአማራ በኩል ትግሉን ወደፊት የሚያራምድ የተወሰነ ነጻነት ያለው ድርጅት አልነበረም፡፡ ብአዴን እስከ እግር ተወርቹ ድረስ በህወሀት የተጠረነፈ ነበር፡፡ በአንጻሩ ኦህዴድ የተሻለ ውስጣዊ ነጻነት ስለነበረው በቀላሉ ወደፊት መገስገስ ቻለ፡፡

ለ) በለውጡ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩት የብአዴን አባላት አማራ በመሆናቸው የአማራነት ባህርያቸውን ተወጡ፡፡ ሰው አማኝ የሚለውን ጸባይ ደገሙት እና አያሌው (አማራ) ሞኙ ሰው አማኙ ሆኑ፡፡ ማለትም ኦህዴዶችን ወደስልጣን ማውጣትን እንደ ትልቅ ስኬት ቆጠሩት፡፡ ኦህዴድም የአያሌው ሞኙን ችሮታ በሚገባ ተጠቀመባት፡፡

ሐ) የኦሮሞ ሊቃን ዲፕሎማሲዊ ትግል የተሻለ ደረጃ ላይ ስለነበረ፤ ትግላቸውም ሌላ ረብሻ ስላልነበረበት የአገር ቤቱን አገዘውና ኦህዴድ ወደስልጣን የሚያደርገውን ግስጋሴ ጨመረለት፡፡ በአንጻሩ አማራ በዲስፖራው ውስጥ የረባ አደረጃጀትም የረባ ሰውም ስላልነበረው ትልቅ ክፍተት ተፈጠረ፡፡ ይሄም ለኦሮሞ ሊቃን ተጨማሪ አቅምን ፈጠረ፡፡

2) ውሸት፡-

እንግዲህ ወያኔን በማባረር ዋናውን ድርሻ የሚወስደው የአማራ አብዮት ነው ብለናል፡፡ የቄሮ አለቆች ግን ይህንን ሀቅ ሽምጥጥ አድርገው በመካድ “ለውጡ” የቄሮ ብቻ ነው አሉ፡፡ ለውጡን የአማራ ወጣት አመጣው የሚለውን ሀቅ ሊቀበሉ ይቅርና ተቃውሞ ሲያደርጉ በነበረበት ጊዜ አማራ በአጠገባቸው የነበረም አይመስሉ፡፡ የውድቀታቸው መጀመሪያ የሆነው የኬኛ ብቻ አስተሳሰብ ትግሉም ኬኛ ብቻ በሚል ነው የጀመረው፡፡ አስቂኙ ነገር ይሄንን ራሳቸው የፈጠሩትን ውሸት እውነት ነው ብለው ማመናቸው ነው፡፡ ይሄም የሌላቸውን አቅም እንዳላቸው ሁሉ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡

3. ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሆንዋን አለመቀበል፡፡ ይሄም አስተሳሰብ ያዩትን ሁሉ የኛ ብቻ እንዲሉ ገፋፋቸው፡፡

4. ወደመንግስት ስልጣን ሲወጣ የመንግስት ስራ ምን መሆን እንደነበረበት አለማጥናትም ለውድቀት ዳርጓቸዋል፡፡ መንግስት ላይ ሆነው አንድ ያኮረፈ ጎረምሳ መምሰል የጤናም አይደል፡፡

5. ሲስተምን ለማዛባት መስራታቸው ዋናው ችግር ሆኖ ወደውድቀት መርቷቸዋል፡፡ ወደዱም ጠሉም የኢትዮጵያ መሰረታዊ ስርአት ማንም እንዲህ በቀላሉ ሊጋፋው የሚችል አይደለም፡፡ የአማራ የባህል የበላይነትም ምንም በለው ቀድሞ የተዘረጋ ስረአት አለ፡፡ በዚህ ስርአት ውስጥ ገብተህ ትሄዳለህ እንጅ ለማፍረስ አትሞክርም፡፡ ህወሀት ራሱ አልሞከረውም፤ ቢሞክረው መጥፊያው እንደሆነ ስለሚያውቅ፡፡ የቄሮ አለቆች ግን ዴሞግራፊ ማዛባት የሚል ኋላቀር ዘመቻ ወዲያው ጀመሩ፡፡ ባህሉንም ለመቀየር አሰቡ፡፡ የማይሆነውን፡፡ አሁን ይሄው ከአጼ ምኒልክ ጀምሮ የተዘረጋ ባህላዊ ስርአት ወይም አጠቃላይ ማህበራዊ ሲስተም ጋር ተጋጩና መፈረካከስ ጀመሩ፡፡ ከሲስተም ጋር ያደረጉት ግጭት ሲያነጥራቸው ከአማራ ጋር የተጋጩ መሰላቸው፡፡ አሳሳቢው ነገር፡፡

6. ህወሀት ለምን እንደወደቀ ለመማር አለመቻል ጎድቷቸዋል፡፡

እንግዲህ በማናቸውም መለኪያ የውድቀታቸው ምንጭ ራሳቸው ናቸው፡፡ ራሳቸውን አደናቅፈው ሲያበቁ ድንጋዩን አማራ አስቀመጠው ማለታቸው አሁንም የራሳቸውን ችግር መርምሮ መረዳት አለመቻላቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ አሁን አማራ ላይ የሚደረገው ፉከራ የራስን ስህተት አለማየት ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአማራን “ክልል” ለማበጣበጥ በሚዲያ ሽፋን በመስጠት ለሚያደርጉት ነውረኛ ስራ ደግሞ ተመጣጣኝ አጸፋ ይጠብቃቸዋል፡፡ አማራን ለመከፋፈል እየሰሩ አማራን መውቀስ ግን አይጋጭም? ያላወቁት ደግሞ አማራ እስካሁን ድረስ መልስ መስጠት አለመጀመሩን፡፡

ምስጋናው አንዱአለም