ሊሆን የሚገባው ይሁን፥ ሊደረግም ያለው ይደረግ

0
1456

ወደ ገደለው!

እንግዲህ 800 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል አሁን እዳው በዛው በሰብሳቢዎች ላይ ነው:: ምንም ምክኒያት አይኖርም መልሶ ተፈናቃዮችን ላለማደራጀት:: ገንዘቡም በቂ ነው:: መልሶ ማደራጀት እንጂ መሸከም አይደለምና basic need ከተሟላ ተሯሩጦ ኑሮና ብልሀቱን ማሳካት የህዝቡም ኃላፍነት ነውና!

ነገር ግን ለእኛ ለአማራ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች በዚህ ጉዳይ በተለይ በገንዘቡ ላይ ብዙ ልብ ማንጠልጠል አይገባንም! ለእኛ ከገንዘቡ በላይ የኃይል አሰላለፍን በኢትዮ ፖለቲክስ ማስቃኘቱ ነው ዋናው ነገር:: ምክኒያቱም it’s obvious ተፈናቃዮች የተፈናቀሉት በክልሉ አስተዳደር ንህዝላልነትና አንዳንዱም በክልሉ መንግስት ሃይ ባይነትም ነው:: የጎንደር መፈናቀል በቀጥታ አዴፓን ይመለከታል:: አገሩ ላይ ስርአት አልበኝነት ሲሰፍንና በቅማንት ማሊያ ተጫዋች ጥቂት ወሮበሎች ጨዋውን ያገሬን ሰው እንዲህ ለጥቃትና ውርደት ሲጋብዙ የክልሉ መስተዳደር አፉን ከፍቶ ስፓርታከስ የታደመ ነበር የሚመስለው:: የኦህ ዴዱ አምበል አብይ ፌደራል ሰራዊት አሰልፎ ንፁኃንን ሲፈጅ የአዴፓ ሹምባሾች እንዳላየ እንዳልሰማ ሆነው አማራን እናዋይ ብለው አማራ ክልልን ትተው አማራ ያጡ ይመስል በአገራቸው አማራ ፍለጋ አሜሪካን መጥተው ነበር! ወይ ግሩም! ባፉ በጆሮው ሳይቀር ቃላት ተቀጣጥለው እየወጣ እንዳበደ ውሻ እያለከለከ የሚያወራውን ፀረ አማራውን ጀዋርን ጃኖ እያለበሰ ሲሞላፈጥ የነበረው ይኸው ወራዳና የበከተው ድርጅት ነው:: አሁን አምበል በመቀየር ማዘናጊያ ግዜ መግዣ ዶ/ር አምባቸውን ሾሟል:: ባይ ዘ ዌይ ይሄ ሹመት አይደለም ለአምባቸው በደንብ ካጤንነው ጉዳዮን it’s a demotion. ከፈደራል level አውርደው በክልል ማስገባታቸው ይታወቅ:: ስልታዊ የኦህ ዴድ ከአማራ የፀዳ አስተዳደርን ለመፍጠር ማስፈንጠራቸው ነው:: At a national level ባለው ፖለቲካ ሚና እንዳይጫወት የሚስጥርም ተካፋይ እንዳይሆንም ነው:: ሲያፀድዱት!

እና አሁን ዶ/ር አምባቸው ህዝብ ላወያይ እያለ የአቢቹን አይነት ቀልድ ባስቸኳይ አቁሞ አሁን ስራ መስራት ይጠበቅበታል:: ህዝቡማ ሳይመርጣችሁ ትሿሿሙበታላችሁ ደግሞ አወያየን ትሉታላችሁ:: ምን ያለ ቅጥ አንባሩ የጠፋው ጉንድሽነት ነው?! ዶ/ሩ ተምሮ አገር ለማገልገል ብቃት አለኝ ብሎ ለራሳቸው ድል ያለ ግብዣ ደግሰው በድንገተኛ ተሿሹመዋል አሁን የሚጠበቅባቸው ስራውን መስራት ነው!

በአማራ ክልል በዋናነት መተግበር ያለባቸው ጉዳዮች:-

1) Homeland security:- ፀጥታውንና ደህንነቱን ለአማራው ህዝብ መርፌ ቢወድቅ በሚሰማበት ልክ ሊያረጋግጡለት ይገባል!

2) Change of Policy:- የፖሊሲ ለውጥ በኢኮኖሚው ረገድ ፥ በአፈናን በማስቀረት ረገድ ፥ ለወጣቱ ስራ መፍጠር ወዘተ

3) Diplomacy:- የዲፕሎማሲ ስራዎችን አጠናክሮ ከአጎራባች ክልሎችና ከአጎራባች አገራትም መስራት!

4) Media:- ሚዲያን በአማራ ክልል የተመቻቸ በማድረግ ብዙ ድምፅ ህዝቡ እንዲኖረውና የሀሳብ መንሸራሸር እዛው በራሱ ክልል እንደፈለገው እንዲኖረው ብሎም ለአናሳ ለሆኑ አጎራባች ክልሎች እንደ ጌዲኦ ፥ ሶማሌ ፥ ሲዳማ ወዘተን ስርጭት ማድረግ እንዲችሉ እድሉን መክፈት::

5) Defence:- በቋራ አላጥሽን ጉዳይ እልባት በቶሎ:: የቅማንት ኮሚቴ ተብዬ የህውሀትን ገረዶች አድኖ ለፍርድ ማቅረብ! በክልሉ በስለላና በተለያየ ተልእኮ ይዘው ገብተው ሽብርን ለማስነሳት መሳሪያ የሆኑና ጆሮ የሚጠቡን ጆሯቸውን ይዞ ከክልሉ ማባረር አሊያም በቂ መረጃ ካለ ማሰር..ወዘተ

6) Restructuring:- ልዮ ዞን እያለ በዘመነ ወያኔ ወጥ የረገጠ አከላለል ብልግናን ባስቸኳይ በመሻር በአማራ ክልል ልዮ የሚባል ዞንን ድራሹን ማጥፋትና ወደ ቀደመ አከላለል መለወጥ!

7) Nile Project:- የአባይን ጉዳይ በቀጥታ ከግብፅ መነጋገር!

8)Trade:- ምርት አቅራቦት ለጎረቤት አገራትና ለውጭ አገራት የንግድ ድርድር (fair trade) ማካሄድና ገበሬውን በቀጥታ እህሉን እንዲሸጥ በማድረግ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ በፍጥነትና በቶሎ የህብረተሰቡን ድህነት መቅረፍ!

9)Educational Reform:- ከውጭ ገራት ጋር በተለያዮ ጥቅማ ጥቅሞችን በማቅረብ የክልሉን የትምህርት ቤት ቁጥር በየቀበሌው ሁለት ሶስት እጥፍ በማሳደግ በገፍ እና በጥራት ትውልዱን ማስተማር::

10) Health:- ከታላላቅ አገራት ጋር በመተባበር ሆስፒታሎችን ፥ ክሊኒኮችንና መድሀኒት አቅራቦትን ማበራከት እንዲሁ ይህንንም አውታር 100 እጥፍ ማሳደግ ነገ ዛሬ የማይባል ነው::

11) Energy:- ውሀ ፥ መብራት ፥ ኢንተርኔት ወዘተን ሀይልን በማመንጨት ህብርተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ብሎም ሌሎች ከክልላቸው ውጭ ያሉ አማሮችም ክልላቸው እየተመለሱ ለክልላቸው እየሰሩ ክልላቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ! ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ማመቻመቻ ኢንተርኔት ተጠቃሚው በአማራ ክልል በ1000 እጥፍ በማስደግ ወጣቱን የኢንፎርሜሽን አድማሱን እንዲያሰፋ ማድረግ የሚጠበቅ ነው::

12) Housing:- ቤቶች ግንባታን በማድረግ ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በመስራት ባለሀብትንም ተምሮ አዲስ አበባና ሌሎች ኦሮሞ ክልል ላይ በስቃይ ስራ የሚሰሩትን የሰው ኃይል ወደ ክልሉ የሚጋብዝ ይሆናል:: ዶክተሩን ፥ ኢንጂነሩን ፥ አስተማሪውን ወዘተ ወደ እራሱ ክልል እንዲመለስ (recruit) ጋባዥ ነው::

13) Investment- በውጭ ያሉ አማሮችንም በክልላቸው ኢንቬስት እንዲያደርጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አመቻቹ!

14) የወልቃይት ፥ ራያ ፥ መተከል ፥ አዲስ አበባን ጉዳይ በፍጥነትና በፅናት ታግሎ ቶሎ ወደ ነበሩበት ስፍራ ወደ አማራ ጉያ ማስገባት!

15) ወታደራዊ ስልጠና ከ18:25 ያለውን እንደ national service የሁለት አመት ግዴታ በማድረግ ማሰልጠን!

እላይ የጠቀስኳቸው ጉዳዮች በቅደም ተከተላቸው ባይሆንም ሊጠቀሱ የሚገባን ጉዳዮች ከሞላ ጎደል አንስቻለሁ ብዬ አስባለሁ:. እና ይህንን ስራ ለመስራት ካቢኔ አዋቅሮ ዶ/ር አምባቸው ቶሎ በስራ በተግባር ውጤት ሊያሳየን ይገባል: በዛውም ተንከሲስ ተንከሲሱን ከአዴፓ እያፀዳ ቆራጥና ብቁዎችን ወደ ፊት በማምጣት ስራ መጀመር አለበት:: ከዚህ ኃላ ፎቶ እየለቀቁ ሰው አወያዬ ቀልድና ቧልት ለመስማት አንታገስምና! ለአቢቹም አልበጄው ፎቶ ግጥገጣ!

ይህችን የሰበሰባችሁትን ገንዘብ እንደ kick off ሆኖ በተጨባጭ በስራ ከታዬ ደጋግሞም መጠይቁ ሳያስፈልጋችሁ ህዝቡ እራሱ በራሱ ተነሳሽነት ይሰጣችኃል!

#Amhara #AddisAbeba #Ethiopia #ADP

ሊዲያ ዘ አዲስ አበባ ጊዮን አማራ