በአማራ ኪሳራ የምትሰራ ኢትዮጵያ አትኖርም!

0
1351

ቄሮ የመንግስትን ህግ ተፃርሮ ሰው ለመግደል እንጨት ይዞ እንደፈለገው ሲሰለፍ ያልተደራጀና በግሌ ያለመናበብ የአዲሳባን ነገር ልቋጨው ብሎ የተነሳው እስክንድር ስብሰባ እንኳን እንዳያደርግ አሻጥሮች እየተደረጉ ነው::

ይህ ምን ያሳየናል? ሳትደራጅ፥ አማራነትን ሳታነግብ፥ ህዝባዊ መሰረት ሳይኖርህ መንቀሳቀስ ትርፉ ድካም መሆኑን ነው! እስክንድር ነጋ እስከማውቀው ድረስ አማራ ነው ታዲያ ስለአማራነቱ መቆምና በአማራነት መደራጀትን ምነው አልፈለገም? እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እኮ ነገ እሱ ጋር ሄዶ የሚታደመው ያው አማራው ነው! ታዲያ ተማግቶም ለማይሟገትለት አማራዊ ጥቅሙንም ለማያስከብርለት ሆኖም አዲስ አበባን የሁሉም የማድረግ እንቅስቃሴ ለአማራ ምኑ ነው? አዲስ አበባ ሁሉ ይኖርባታል እንጂ የአማራ ናት አለቀ! ታሪክ ምስክር ነው!

እንደ እስክንድር ያሉ ኦሮሞዎችና ትግሮች ወዘተ ብሄራቸውን ለማጎልበት ደፋ ቀና በሚሉበት ወቅት እንደ እስክንድር ያሉ አማሮች እስከመቼ ከአማራነት ይሸሻሉ? እስከ መቼ “ዲሞክራሲ” በሚል እና “ኢትዮጵያ” በሚል ህዝባዊ መሰረት በሌለው መርህ አልባ ፅንሰ ሀሳብ አይናቸውን በሻሽ አስረው በከንቱ ጉልበታቸውን ያፈስሳሉ?

ኦሮሞዎች ዲሞክራሲዬ የሚለው የራሱን ቨርዥን ከቄሮና ጀዋር ብሎም በድርብ ከሚሰሩላቸው አብይና ለማ እንጂ ከእስክንድር ተጠቅልሎ እንደ ስጦታ ቢሰጠው እንኳ በእንጨት አይነኩትም! እራስን በራስ ማጎልበት ነው ሞቶው! የትግሬውም እንደዛው! ታዲያ የኛዎቹ እስከመቼ ባልተፈለጉበት በመባዘን የራሳቸውን ህዝብ abandoned በማድረግ ይቀጥላሉ? እስክንድር ሲፈታ አማራው ነው በጎንደር፥ ጎጃም እያዞረ ወግ ያሳየውና አቀባበል ያደረገለት ሌላው ዝግትግት ነው ያደረገው አንድነቱን ጨምሮ! ታዲያ ለአማራ ላለመቆም ምንድን ነው እነእስክድርን የሚቸግራቸው? ዞረው ዞረው አሁን ያነሷትን ሀሳብ አማራን ለማሸከም ነው እንጂ ከነእስክድ ነፃነቱን የሚቸር ኦሮሞም ሆነ ትግሬም ወይን ጉራጌ ከንባታም የለም!

“ድል ለዲሞክራሲ” ብሎስ ነገር አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ምን ትርጉም አለው? ያለው የብሄሮች መቃረን ነው! ተቃርኖውም በዲሞክራሲ የሚፈታ አይደለም:: ምክኒያቱም ዲሞክራሲ ስለጠፋም የተቃረንነው ቅራኔ አይደለም:: እንደውም የተገኘችን ጭላንጭል ዲሞክራሲ ተጠቅሞ ፀረ- አማራነት የተሰራበት ገደብ ያጣ፥ መረን የወጣ፥ ባለጌ የነፃነት ጥግ እንጂ!

አዲስ አበባን ነፃነት ያገኘ ብሄርተኛ ነው እየፈነጨና “ሁሉ የኔ” በሚል መኖሪያ ቤት የሚያግትባት ብሎም የኔ መንደር ነች የሚላት …. እና ንትርኩ በዲሞክራሲ የሚፈታ ሳይሆን ታሪካዊ ሀቅን በመጋፈጥ በባለቤትነት ቆሞ የቀድሞዋ እንድጥና በረራ ያሁኗን አዲስ አበባን አማራዊ ግዛትነት በማመሳከር ብቻ የሚደረግ ዲስኩር እንጂ በሌላ ዘዴ “የሁሉም ነች” በሚል ከእጃችን ርስት በማውጣት አይሆንም! ከዚህ ቀደም እንዳልኩት ኢትዮጵያን በአማራ ኪሳራ መስራት ከእንግዲህ አይቻልም!

ሊዲያ ዘ አዲስ አበባ ጊዮን አማራ