ማነው ምሁሩ?

0
1354

ሀዋ ጋሹ እንዲህ ትላለች የልጅ አዋቂዋ! ሳትማር የተማረችይቱ አማራይት ልበ ብርሀን!

“ዶክተሬት ፕሮፌሰርነት (ማለቷም ዲግሪህ) ….ወዘተ ሚጠቅሙት ስራ ስትፈልግ ለእንጀራህ ማፈላለጊያ ማስታወቂያ ላይ ለክፍቱ ቦታ ስራ መስፈርት ስራ ለመያዣነት ብቻ ነው። ለአማራ የነፃነት ትግል መስፈርቱ ቆራጥ አማራነት ብቻ ነው።” አፌ ቁርጥ ይበልልሽ! አንቺ ነሽ ምሁር!

*****ምሁር አታርቁ ስላቅ *****

ምሁር ለመሆኑ ማን ነው? የኢትዮጵያም ሆነ በተለይም የአማራው ጠላት የሆኖ አገርና ወገን አሳልፎ ሰጥቶ አገር የሸጠው እኮ ቀለም ያልቀመሰው የህብረተሰብ ክፍል አይደለም:: ተምሯል ተብሎ ምሁር የተባለው ነው እንጂ አገር የሚሸጠው:: ውጪ ተምሮ ሊመጣ በተፈሪ ግዜ ጀምሮ የተላከው ጉብል ሰላይ ሆኖ፥ ክር በጥሶ፥ የማኦንና የሌኒንን ቆብ ደፍቶ፥ ለገንዘብና ጥቅማ ጥቅም መንኖ አገር የሸጠ ምሁር ነው! የኢትዮጵያ ምሁር አገር ሲሸጥ እንጂ ሲያለማ አላየንም! በተለይም አማራ ምሁር ከሌሎች ለየት የሚያደርጋቸው በገዛ አገርና ህዝባቸው ላይ የመቆመር ችሎታቸው ነው! ሌላውስ ወሮ ገብ ነው! አገር የሚያለማው በአገር በድንበር የማይደራደረው ምስኪኑ ገበሬና የገበሬው ልጅ ሳይማር የተማረው ለማተቡ ያደረው እንጂ ምሁርማ አገሬን በቁንጮዋ ይዞ የሚያስማማ፥ በፈረንጆች ደሞዝ ኪሱን ያሳበጠ፥ የገዛ አገሩ ላይ ጆሮ ጠቢ የሆነ አሪዎስ ነው:: ምሁር አታርቁ በሚል ደግሞ “ምሁር” ነን ባዮች የወረቀት ምስለኔዎች መጥተው ቅርሻት ያቀርሹባችሁ ይባል ተጀምሯል! ይህቺኛዋን ደግሞ ባሪፍ ዘይደዋል!

ገና ዘላ ሳትጠግብ፥ በእንቦቀቅላ ዘመኗ ቤቶችዋን ልታግዝ ለራሷም ፀሀይ ልትወጣላት ብላ ምሁሮች ቸርችረው ሸጠዋት አልስማማ ያለችን እድል ነፋጊ ቀዬዋን ትታ አረብ አገር ገብታ በመማሪያ እድሜዌ የምትለፋ ያልተማረች ምሁር ይህች ህፃን እንኳ እንዲህ አለች:: ዲግሪህን ስራ ለመፈለጊያ እንጂ አማራ ትግል ላይ ለመዘርፈጪያነት ብቁ አያደርግህም ትልሀለች አእምሮዋ የበራላት! አማራ ትግል ቁርጠኛና አንድ አማራ የሚል ነፍሱን ሊሰጥ የማይሳሳ ሰው እንጂ ያንተን ከየኮሚውኒቲ ካሌጅ የሰበስብከውን ዲግሪ qualify አያደርግህም ትልሀለች! አቤት ውርደት!

ገበሬ እኮ አልሸጣትም ኢትዮጱያን! ያልተማረው ክፍል እኮ አይደለም አገርን ያስማማ፥ የጎጃም የጎንደር የወሎ የሸዋ ገበሬ እኮ አይደለም ድንበር የሸነሸነው ምሁር ነኝ እያለ ቁንፅል እውቀቱን በነአርስቶትል በነናትዚሽ በነአይንሽታይን አባባል የማይረባ ሀሳቡን ውሀ ሊያስነሳ እነዚህን የሞቱ የጥንት ፋላስፋዎችን አባባል ሲታሽ የሚውል የይስሙላ ተማሪው እንጅ! በራሱ ሀሳብ የማያፈልቅ፥ አገር አልሚ ምንም አይነት አቅጣጫን በራሱ የማያመላክት ሆኖም የነቻይናን የነሲንግፖርን ተመክሮ ነባራዊ ሁኔታውም፥ ባህልም፥ ስነልቦና ስሪታችንም ጋር የማይዛመድ ማሳያን እያሳዮ እራሳቸው ጠፍተው አገር የሚያጠፉ ሆድ አምላኩ ናቸው የኢትዮጵያ ምሁሮች!

ቅንጅት በተነሳና አገራዊ ማእበል በተነሳ ወቅት እድሜ ለልደቱ ይስጥውና ምሁር ተዬዎች ቁጭ ይበሉ “ዶ/ር” ብርሀኑና መስሎች አገር ሊያምሱና የአገራችንን ስሪት ደግመው ሊፈቱ ሲታትሩ ይደግፋቸው የነበረ ቅርብ ጓደኛዬ አማራው የአየር ሀይል አብራሪ የነበሩ አባቱ ጋር ሄዶ “አባዬ ቅንጅትን ልመርጥ ነው” እትትት እያለ አባቱን ሲወተውት እሳቸውም ቀስ ብለው ያማራ ነገር በብልሀት ነው መቼም እና አሉትም “አይ ልጄ “ዶክተሮች” ነፃ ያወጡኛል ብለህ ተስፋህ እንዳትጥል” ብለው እጢውን ዱብ አደረጉት!

ዛሬም አልማሪያም የተባለ ጨበሬ በቀለም ያበደ ፀጉሩን ተተኩሶ ሴት እንዳንለው ወንድ እየቸገረን የአማራውን እንቅስቃሴ ሁሉ በትግሬ ጠንሳሽነት የተነሳ ሲያስመስልና አብንን ሲያዋድቅ፥ በዚህም ዞር ብለው አማራ ትግል ላይ ሲፈናጠጡና አጉል እገሌ ሊሆኑበት ሲዳዱና በህዝብ ህልውና የግል ዝናን ለማጋሸብ የበሬው ወለደ አያቴ ሸዋን አምጦ ወለደ ጣናን አገኘ ማለት የሚዳዳቸው ብዙ ጠንቆች በትንሹ እውቀትን ያልዘበሩ ያነበቡትን መፅሀፍ ያለምንም ማመዛዘንና ማመሳከሪያ እንደገባ መልሰው እየተፉ አዋቂ ሊሆኑ የሚፈልጉ የሳይኮፓቶች ጥርቅም ነው የበዛው!

ተምሮም ዶክትሮ ለህዝብ ጮሆ ነፍሱን ያስቀመጠ አስራት ወልደየስ ጀግናው አንድ እሱ ብቻ ነው! ሌላው ጎንድርን ልገንጥል የሚል ቅማንት ኮሚቴ ሰርጎ ገብ ስራውን እንኳ በደንብ የማይከውን ቡቸር ነው አማራ ላይ መጥቶ ጎንደር ልገንጥል ብሎ በአፉ የሚፀዳዳው! ትምህርት ቀምሶ ዶክትሮ አገር ሲቸበችብ እንጂ ሲያለማ ማንንም አላየንም!

እድሜ ለገበሬ ለአርብቶ አደሩ አገር ቀላቢና አገር ጠባቂው!

በገበሬው ድሀ ልጅ እንጂ አገር ተማርኩኝ ባለ ያገር ቦዘኔ የፖለቲካዊ ተጧሪ ኢኮኖሚ ተስፈኛ አይደለም አገር የተጠበቀችው! ጦሽ ሲል ከነልጅ ልጆቹ ሮጦ አገር ጥሎ የሚወጣ ገበሬው አይደለም ተማርኩኝ የሚለው አንድ ዲግሪ አለኝና አገር ካልገዛው የሚለው ብኩን እንጂ! በሀሳብ እንዳይሞግት ዲግሪው ስር ተወትፎ ስም የሚያጠለሽ ተሳዳቢ ነው ዶክተር ተብሎ ያየሁት! አገር ሻጮች! በወገን ደም ቆማሪ ኮማሪዎች!

ሊዲያ ዘ አዲስ አበባ ጊዮን አማራ