የጎንደር ህብረቱ” ሊቀመንበር ሙሉጌታ ካሣሁን ማን ነው?

0
2175

ጉድ በል ጎንደር!!!

/ “የጎንደር ህብረቱ” ሊቀመንበር ሙሉጌታ ካሣሁን ገመና ሲጋለጥ/

*****ክፍል አንድ*****

በግልጽ እንደሚታየው የአማራ ህዝብ ህልውና በሦስት ኃይሎች ማለትም በፋሽስታዊ የኦሮሞ ኃይሎች፣ በወያኔ ትግሬ እና ራሱን “የቅማንት ኮሚቴ” እያለ በሚጠራው ቡድን ከበባ ውስጥ ወድቋል።

ፋሽስታዊ የኦሮሞ ኃይሎችና የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት የሆነው ወያኔ ትግሬ የደቀኑት ስጋት እና ትንኮሳ ከውጪ ወደ ውስጥ የሚሰነዘር /Implosive/ ሲሆን በተቃራኒው እ.አ.አ. ከሜይ 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በግላጭ ራሱን “የቅማንት ኮሚቴ” እያለ የሚጠራው፥ ከዚያ በፊት ግን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ከወያኔ ትግሬ ጋር ተለጥፎ ለአማራ ህዝብ ጥፋት አመቺ ጊዜ እስኪመጣ አድብቶ የኖረው የቅማንት ካፖዎች ስብስብ ከስጋትም በዘለለ እያስከተለ ያለው ጥፋት ከውስጥ እየተሰነዘረ ያለ /explosive/ የህልውና አደጋ ነው።

ይህ ራሱን “የቅማንት ኮሚቴ” እያለ የሚጠራው ቡድን እንደ አንድ የትግል ስልት ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች መካከል ቅርጽ-አልባ /Amorphous/ እንዲሁም የሽፋን /Undercover/ አደረጃጀቶችን መጠቀም ነው።

ከነዚህ አደረጃጀቶች መካከልም ራሱን “የቅማንት ኮሚቴ” እያለ ለሚጠራው ቡድን የዳያስፖራ ክንፍ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው “የጎንደር ህብረት” የተባለው ስብስብ አንዱ ሲሆን ዋነኛ አላማና ተግባሩም አማራዊው በአንድ አማራዊ ታዛ ስር እንዳይሰባሰብ፥ ይልቁን “ጎንደር”፣”ጎጃም”፣”ወሎ” እና “ሸዋ” እያለ በመንደርተኝነት እንዲከፋፈልና እንዲዳከም በማድረግ በሂደት አሳካዋለው ለሚለው ከሰሜን ተራራ እስከ ፓዌ ተራራ ለሚዘረጋ የሀገር ነጠቃ ፕሮጀክት ጥርጊያ መንገድን ማመቻቸት ነው።

ከሰሞኑም የዚህ የቅማንት ካፖዎች የዳያስፖራ ክንፍ የሆነውና ራሱን “የጎንደር ህብረት” እያለ የሚጠራው ቡድን ሊቀ መንበር የሆነው ሙሉጌታ ካሣሁን ደሴ (ዶ/ር) “ህብር” ለተባለ የሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃለ ምልልስ “ጎንደር የራሱን ክልል መመስረት አለበት” የሚል አማራን ለመከፋፈልና ለማዳከም የጭቃ ጅራፉን አንድ እርከን ከፍ አድርጎ አስጩሆታል።

መልካም። ጆሮ እንጥል የለውምና እኛም በአርምሞ ሰምተነዋል። ነገር ግን ሙሉጌታ ካሣሁንና ቢጤዎቹ የዘነጉት ነገር ቢኖር ዛሬ ትናንትናን አለመሆኑን ነው። ትናንት ማንም እየተነሳ ባልታጠበ እጁ በአማራ ጉዳይ እየገባ ሲፈተፍት፣ ሲዘልፍ እና ሲሳደብ፣ ሲገድል እና ሲያፈናቅል ምላሻችን ሁሉ “ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ፤ ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ” የሚል ድምፀት ያለው እንጉርጉሮ ብቻ ነበር።

ዛሬ ግን እጁን በአማራዊ ህዝባችን ላይ የሚያነሳ ሁሉ መቼውንም ቢሆን ዕረፍት እንዲያገኝ ዕድሉን አንሰጠውም። የአማራ ብሔርተኝነት የመዳህ ዘመኑን እያገባደደ ጥፍርና ጥርስ እያወጣ እንደሆነ ከጥቃቅን ቀበሮዎቹ ሙሉጌታ ካሣሁንና ቢጤዎቹ እስከ ትላልቆቹ ተኩላዎች ድረስ ይህንን አዲስ እውነት ይረዱት ዘንድ እውነትንና ማስረጃን ተንተርሰን ይህን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ወደድን።

የግራ አካሌን አመመኝ ብሎ የሄደን ህመምተኛ፥ ቀኝ አካሉን እየቆረጠ መካን ሲያደርግ የኖረ ሐኪም ነኝ ባይ እማማ ጎንደር በወልቃይትና በራያ፥ በመተከልና በደራ የተበተኑ አማራዊ ልጆቿን ከነርስታቸው ለመሰብሰብ ደፋ ቀና እያለች ባለችበት በዚህ ወቅት “ነይ አንቺኑ ከሌላው አካልሽ ቆርጬ ልውሰድሽ” የሚል መደዴን ስታይ እንዲህ የሚለው የአብሃም ሜስሎ ድንቅ አባባል ወደ አእምሮህ ይመጣል፡- “I suppose it is tempting, if the only tool you have is a hammer, to treat everything as if it were a nail.”

እነሆ አንባቢን ላለማሰልቸት እስከዛሬ ድረስ በኋላ ኪሳችን ይዘነው የኖርነውንና በበቂ ማስረጃ የተደገፈውን የዚህ ነውረኛ ግለሰብን ጥቁር ታሪክ የምንዳስስበትን ጽሑፍ በሶስት ክፍል የምናቀርብ ሲሆን፡-

– በክፍል አንድ ዳሰሳችን በ2008 ዓ.ም. ድርጊቱ ተፈፅሞ፥ ነገር ግን የኔቫዳ ግዛት የሐኪሞች ቦርድ በሴፕቴምበር 2012 ዓ.ም መፍትሔ የሰጠበትን ጉዳይ የምንመለከት ሲሆን፤

– በክፍል ሁለት ዳሰሳችን ይህ ነውረኛ ግለሰብ በ2009 ዓ.ም. ጄን አሌክዛንደር ኤልቢኪ በተባለች ታካሚ ላይ የፈፀመውን ጆሮን ጭው የሚያደርግ ፀያፍ ተግባርና ያንንም ተከትሎ በኔቫዳ ግዛት ክሌርክ ካውንቲ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት በክስ መዝገብ ቁጥር፡ A-09-601458-C የቀረበበትን ክስና የጥፋተኝነት ውሳኔ ከነማስረጃው የምናቀርብ ይሆናል። እንዲሁም፡-

– በክፍል ሶስት የምንዳስሰው እ.አ.አ. በ2000 ዓ.ም ከዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ኃይል የመጡ መልማዮች /Recruiters/ በሮችስተር ኑዮርክ ለተጠባባቂው ጦር የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሐኪሞችን ሲመለምሉ በወቅቱ የዩሮሎጂ ትምህርቱን እየተከታተለ የነበረው ሙሉጌታ ካሣሁንም ይመዘገባል። በ2004 ዓ.ም መገባደጃ አካባቢ ቴክሳስ በሚገኘው ሳን አንቶንዮ ሚልትሪ ሜድካል ሴንተር መሠረታዊ የጦር ግምባር ህክምና እርዳታ ስልጠናን ከወሰደ በኋላ በ2005 ዓ.ም. ጀርመን ሀገር ወደሚገኘው የአሜሪካን ሚሊትሪ ሆስፒታል ለስድስት ወራት አገልግሎት እንዲሰጥ ይላካል። አራት ወራት ያህል በጀርመን ሀገር እንደቆየም ከተላከበት ተልዕኮ ውጪ እንዲሁም የሙያው ሥነ-ምግባር ከሚፈቅደው ያፈነገጠ ተግባር ውስጥ ሲሳተፍ በጀርመን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ይውላል። ሁለቱ ሀገራት የኔቶ አባል ሀገራት በመሆናቸውም እንደዚህ አይነት ተግባር ሲፈፀም ወታደሮቹ አልያም የሚሊትሪ አባላቱ ጉዳያቸው የሚታየው በመጡበት ሀገር እንደሆነ በጁን 1951 የወጣው Status of Forces Agreement (SOFA)፣ እንዲሁም በኦገስት 1959 የወጣው the SOFA Supplementary Agreement ስለሚያስገድድ ሙሉጌታ ካሳሁንም በቀጥታ ከጀርመን እስር ቤት ወደ አሜሪካ የተመለሰበትን፣ ምን ድርጊትስ ፈጽሞ ነው ከጀርመን ተጠርዞ በአሜሪካ ሚሊትሪ ቅጣት የተወሰነበት? በወቅቱ የጀርመን ሚዲያዎች በተለይ ታዋቂው “ዴ ሽፒግል” /Der Spiegel/ የተሰኘው ጋዜጣ ምን ዘገባ ይዞ ወጣ? የሚለውን ከጋዜጣው ኮፒ ጋር አያይዘን እናቀርባለን።

ለዛሬ ወደ ክፍል አንድ ዳሰሳችን እንመለስ። መልካም ንባብ።

ጊዜው ኦክቶበር 17, 2008 ዓ.ም. ነው። አንድ ዕድሜው 28 ዓመት የሆነው ግለሰብ ወደ ህክምና “ባለሙያው” ሙሉጌታ ካሣሁን ዘንድ ይቀርብና በግራ የዘር ፍሬው /Testicle/ ላይ እባጭ /cyst/ እንደወጣ ይነግረዋል።

ሙሉጌታም እባጩን ከሰውየው የግራ የዘር ፍሬ ላይ በቀዶ ጥገና እንደሚያወጣለት ይነግረውና ቀጠሮ ሰጥቶ ያሰናብተዋል።

በቀጠሮው መሠረትም ታካሚው የ28 ዓመት ሰው በኦክቶበር 24, 2008 ዓ.ም. ወደ ሙሉጌታ ተመልሶ ይመጣል። በሂደትም ሙሉጌታ ወደ ቀዶ ጥገናው ይገባል። አሳዛኙ ክስተትም የተፈጠረው ከዚህ በኋላ ነበር።

ታካሚው የታመመው የግራ የዘር ፍሬውን ሆኖ ሳለ ሙሉጌታ ግን ጤነኛውን የቀኝ የዘር ፍሬ ጃርት እንደበላው ዱባ መቆራረጥ ይጀምራል። በዚህም የታካሚውን የቀኝ የዘር ፍሬ ከዩሬትራው ጋር የሚያገናኘውንና የዘር ፈሳሽ ማስተላለፊያ የሆነው ቫስ ዴፈረንስ የተባለውን አካል ይቆርጠዋል /Vasectomy on Patient´s right vas deferens/። እንግዲህ ፈጣሪ ያሳያችሁ! የወንድን ልጅ ቫስ ዴፈረንስ የሚባለውን አካል ቆረጥክበት ማለት ያ ሰው መካን ሆነ ማለት ነው።

ሙሉጌታም የታካሚውን ጤነኛ የቀኝ የዘር ፍሬ ብልሽትሽቱን ካወጣው በኋላ አስቀድሞ ህመምተኛው እባጩ ያለው የግራ አካሉ ላይ እንደሆነ የነገረውን አስታውሶ ወደ ግራው የዘር ፍሬ በመሄድ እባጩን ያያል። ተመልሶ ወደ ቀኝ የዘር ፍሬ በመሄድ የቆረጠው ቫስ ዴፈረንስ ስህተት መሆኑን ሲያውቅ እሱን መቀጠል እንዲያስችለው ሌላ ስራ ውስጥ ይገባል /Reapproximation of the injured right vas deferens/ በመጨረሻም በዕለቱ ከታካሚው የግራ የዘር ፍሬ ላይ ያለውን እባጭ ያወጣለታል ነገር ግን የቆረጠውን ጤናማውን የቀኝ ቫስ ዴፈረንስ ሳያስተካክል ሰውየውን ወደ ቤቱ ይልከዋል።

በማግስቱም ማለትም በኦክቶበር 25, 2008 ዓ.ም. ታካሚው ስፕሪግ ቫሊ ሆስፒታል በመገኘት የተቆረጠው የቀኝ ቫስ ዴፈረንስ መልሶ እንዲቀጠልለት /vasovasostomy/ ተደርጓል፡፡

እናም ይህ ቅሬታ የቀረበለት በወቅቱ በዶክተር ቤንጃሚን ሮድሪጌዝ የሚመራ የአጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ

በመዝገብ ቁጥር /Case No./ 12-29294-1 የተመዘገበ የምርመራ ውጤት ሪፖርት በጁን 5, 2012 ዓ.ም. ለኔቫዳ ግዛት የሀኪሞች ቦርድ ለውሳኔ አቀረበ። /በዚህ አጋጣሚ የዚህን ምርመራ ውጤት ኮፒ ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያይዘነዋል/

የኔቫዳ ግዛት የሀኪሞች ቦርድም የቀረበለትን የምርመራ ውጤት ከተመለከተ በኋላ በሴፕቴምበር, 2012 ዓ.ም. የሚከተሉትን አራት ውሳኔዎች በሙሉጌታ ካሣሁን ላይ አሳልፏል፡-

1ኛ. ዶ/ር ሙሉጌታ ካሣሁን በ28 ዓመቱ ታካሚ ላይ የፈፀመው ተግባር የተሻሻለው የኔቫዳ ህግ ምዕራፍ 630 ቁጥር 040ን የሚጥስ በመሆኑ በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 301 /4/እና 352 መሠረት በገንዘብ እንዲቀጣ፥ የገንዘብ ቅጣቱንም በ30 ቀናት ገቢ እንዲያደርግ፤

2ኛ. አጣሪ ኮሚቴው ጉዳዩን ለማጣራት ያወጣውን ወጪ ሙሉጌታ ካሣሁን ለቦርዱ እንዲከፍል፥ ክፍያውንም በ30 ቀናት እንዲፈጽም፤

3ኛ. ሙሉጌታ ካሣሁን ለአስራ ሁለት ተከታታይ ሰዓታት ተጨማሪ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲወስድ (“He should attend in person twelve hours of Continuing Medical Education in medical systems errors/procedures and or medical records in addition to the credits required for licensure”.)

4ኛ. ሙሉጌታ ካሣሁንን በአደባባይ መገሰፅ /Public Reprimand/ የሚል ሲሆን ይህንን ለህዝብ ይፋ የሚሆን ግሳፄም /Public Reprimand/ ማክሰኞ ሴፕቴምበር 11, 2012 የወጡ የኔቫዳ ግዛት ጋዜጦች ሰፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን ከነዚህም መካከል “ኔቫዳ ሰን” የተባለው ጋዜጣ በዋናነት ይጠቀሳል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ዝርዝር ማየት የሚፈልግም የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ /link/ http://medboard.nv.gov/Patients/Disciplinary/DisciplinaryActions/ ተከትሎ የሙሉጌታ ካሣሁን ስም ላይ “ክሊክ” ቢያደርግ ዝርዝሩን ማግኘት ይቻላል።

እንግዲህ አማራዊው ወገናችን ሆይ! እንዲህ አይነቱ ሰለጠንኩበት በሚለው ሙያ እንኳን በብቃት መስራት የማይችል፣ ያየውን ሁሉ ካልቆረጥኩ የሚል ድኩማን ነው የአማራዊ ታሪካችን መሶበ ወርቅ፥ የትውፊታችን አክሊል የሆነችውን ጎንደርን ከቀሪው የአማራ ምድር ቆርጬ ክልል እመሰርታለሁ እያለ የሚያቅራራው። እኛም ለሙሉጌታ ካሣሁን እንዲህ ልንለው ወደድን፡- የአማራን ምድር ለአማራዊው ተወውና ይህን ምክር ተቀበል “ከመጠምጠም፥ መማር ይቅደም!!!”

ጆሮን ጭው የሚያደርገውን የዚህን ሰው ነውረኛ ገመና በክፍል ሁለት ከማስረጃ ጋር በቅርቡ ይዘን እንመለሳለን።

የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም!!!

ቸር እንሰንብት!

ዴቭ ዳዊት።