አብይም እንደ ሙርሲ

0
1666

ሙርሲም ብዙ ድጋፍ ተችሮት ነበር! አለም አቀፍ ብዙ ጋዜጦች አትተውለት ነበር:: ሆኖም አሜሪካኖቹ old friendዳቸውን ሙባረክን አውርደው ሙርሲን ሲተኩት ሙርሲ ስራቸውን በተሰጠው ትእዛዝ ዝንፍ ሳይል እየተገበረ እንዲፈፅም እንጂ እንዳሻው እንዲያንቧችር አልነበረም:: ሙርሲ ልክ እንደ አብይ የራሱን ቡድን ይዞ ተሰየመ! የግብፅን ህገ መንግስት አሰልፎ ባስገባው አክራሪ ሞስሊም ክንፍ ህገ መንግስቱን ለመቅረፅ የሄደበት መንገድ በህግ አካሄዱን ያዛባ ነበርና ይህንን አንድ ገለልተኛና ነፃ ጋዜጣ ዘገበ ግብፅም ግልብጥ ብሎ ወጣ! ሚሊተሪው በተጠባባቂ መንግስትነት ይሰራ የነበረውም ጣልቃ ገባ ብሎም አልሲሲን አምጥቶ ሙርሲን ዘብጥያ ወረወረው!

አብይም የሚይዝና የሚጨብጠው እስኪምታታበት ኦሮሞ አክራሪ ይዞ ገብቶ ህጋዊ አካሄዶችን እየደረመሰ በቀን አስር ግዜ ተለዋዋጭና ህግ የጣሱ ብዙ ነገሮችን ይላል ያደርግማል:: እንግዲህ ሉአላዊ የሚባል ክልል የለም ያለን ሰው ነው:: ፌደራል ክልልን ሰራ እንጂ ክልል ፈደራልን አልሰራም ብሎም ፍፁም ከህገ መንግስቱና ክልሎች አወቃቀር ተፃራሪ ነገርን ሲናገርም ተሰምቷል::

ዛሬ ደግሞ ጥሚዶኮ አብይ ፓርቲዎችን ሁሉ አፈርሼ አንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ የሚል ድርጅት እገነባለው ሲል ተደምጧል:: ይህ አካሄድ በራሱ ህገ መንግስት ተፃራሪና አምባገነናዊ አካሄድ ነው:: የአብይን ከዚህ ቀደም ሁኔታውን ያስተዋለው ታይምስ ሜጋዚን እንደዘገበው አኳኃኑ ሁሉ አምባገነኖች የሚያደርጋቸው መሆኑን ብዙ አካሄዱ አመላካች ነው ብሎታል::

አብይ እንደ ሙርሲ ይዟቸው በመጣውና ከኃላው አነፍንፈው ባሉ “ኬኛ ሁሉም የኔ” የሚሉ ቀማኛ ደፍጣጭ ፖለቲከኞች ቡድኑን ይዞ ብቻውን ህገ መንግስቱን አፈርሳለው ብሎናል ዛሬ! ይህ ፍፁም ወደ ሆነ አምባገነናዊ እየገሰገሰ ያለ ልዝብ ሰይጣን አሁኑኑ በተቃውሞ አጅበን የውጭ ኃይሎችን በማነሳሳት እንደ ሙርሲ ማስወገድ አለብን! አብይ በቅርቡ እሱና ለማ ውጭ ሌላ የክልል አስተዳደር በሌለበት ወታደራዊ ትር ኢቶችን ያደረገ መሆኑ ይታወሳል:: ማስፈራሪያ መሆኑ ነበር:: It’s part of the intimidation process. ሚሊተሪው መፈንቅል ሊደረግብህ ነበር ብሎ እንዳጠረውም ከዚህ በፊት በፑሻብ የታጀበ ልቅ ንግግር አድጎ ነበር:: በልጅነቱ ብዙ የቫንዳምን ፊልም የኮመኮመ ይመስለኛል!

ኦሮሞ አክራሪዎችን በግራም በቀኝ አሰልፎ ሲያበቃ አንድ ትልቅ ፓርቲ ሁሉም የሚሳተፍበት እመሰርታለሁ ይላል አንድ ትልቅ የኦሮሞ ፓርቲ በሚል ተቋቁመን ቅኝ እንገዛለን እንዳይለን ፈርቶና ህዝቡንም ከሞኝ ቆጥሮ መሆኑ ነው! ባለፈው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብሎ ሲያወያያቸው የኦሮሞ ፓርቲ ባፌ እንዳየነው ሁሉ መራራ ጉዲና ፥ ሌንጮ ለታ፥ ሌንጮ ባቲ፥ ዳውድ ኢብሳ፥ ወዘተ ኦሮሞ በያይነቱን እንዳስደመሙን ከነሱም አለፍ ሲሉ እነ ብርሀኑ ፀረ- አማሮቹ፥ በየነ ጼጥሮስን፥ አረጋዊ በርሄን የመሳሰሉ ሰዎች ሰብስቦ ከአማራ ፅዱ ስብሰባን ማየታችን ይታወስል:: ( ፕሊዝ አብን ነበር እንዳትሉኝ እሱማ ጋሽ አበራ ሞላም ነበር) እናም አሁን አንድነት ብሎ ኦሮሞ አክራሪዎችን ሰግስጎበት ህገ መንግስት እንዳሻው ቀርፆ ሊፋንን ማለት ነው::

አቢቹ ልክ እንደ ሙርሲ ተራሽ ደርሷል! ህገ መንግስት አፍርሶ አዲስ አገራዊ አኃዳዊ ፖርቲ ለማቋቋም አንተ ለብቻህ በእኔ አውቃለሁ የምትወስነው አይደለም:: ሲጀመር በእውቀትህ ውስን ነህ:: ሲለጥቅ inexperienced ነህ:: በልምድ ያካበትክው ነገር የለም! ሲጠቃለልም እስካሁን ካሳየኸን PR stunt የፎቶ ጋጋታ ውጪ በአገራችን ሰላም በየትኛውም ስፍራ የለም! አማራን ለይተህ ከለገጣፎ ብሎም ከአዲስ አበባ አፈናቅለሀል፥ ቤት አስፈርሰሀል፥ አስደብድበሀል!

አቢቹ እንደ ሙርሲ ቶሎ ተቀየስ! አገር እቃ እቃ መጫወቻ አይደለችም!

የኦፒዲኦን የዛሬውን የብሽሽቅ መግለጫ ላየው አገራችን የበሰሉ ሰዎች አጥታ በኦሮሞ አክራሪ ወጠጤዎች እየታመሰች መሆኑን ያሳያል! ወያኔ ተሽላ ታየች እኮ በነዚህ ልቅ አክራሪዎች ምክኒያት! ማን ያምን ነበር ከወያኔም የባሰ አለ ብሎ? ዌል ዌል ዌል … ትብስ መጣችና አረፍነው!

Abiy must go! Abiy is unfit, inexperienced, slow to learn and immature! Abiy got to go!

ሊዲያ ዘ አዲስ አበባ ጊዮን አማራ