Home ምልከታ ብአዴን የዛገ የተመዘመዘ ቀዳዳ ብረት ነው!

ብአዴን የዛገ የተመዘመዘ ቀዳዳ ብረት ነው!

0
ብአዴን የዛገ የተመዘመዘ ቀዳዳ ብረት ነው!

የዛሬው የብአዴን/አዴፓ የሚባል የትግሬ ስሪት ድርጅት በአማራዋ ታሪካዊ ግዛት ላይ ያለውን አቋም ቅልብጭ አድርጎ የአዲስ አበባነቷን አለመግለጥ ትልቅ ታሪካዊ ሸፍጥ በግዜው መንግለን የምጥለው ቢሆንም ቅሉ እነዚህ የቤት ባሮች ያደረጉትን ግን በሂሳብ ስናወራርደው በአገር ባዶች ላይ በተደረገው አይነት ቅጣት ነው! አትገደሉም ግን ጉንድሽ ሆናችሁ አገር ማለት ፅናት ማለት እንዴት እንደሆነ በኩሩ ፅኑ አማሮች አማራዊ ምድራችን ስትሰራ ቁጭ አድርገን እያሳየናችሁ ካላችሁበት መንገድ ዳር ሳንቲም እየወረወርንላችሁ የእዝነ ማሪያም ልመናችሁን እንዳንሰማ አፍንጫ ቆንነን ምላሳችሁንም ቆርጠን ነው! እንዳትረሷት እናንተ ባንዶች!

—እራስን በራስ ማስጠፋት ፖለቲካ ሰለባ ብአዴን—

ብአዴን የሚጎለብት ተቋም ቢሆን ኖሮ በዛሬው አይነት አወዛጋቢ በተደረገ የአዲስ አበባ ከተማ ጥያቄ ላይ የማያሻማ መልስ በመስጠት ወደ ጠረጼዛው ለክርክርም ሆነ ለቀጣይ አዲስ አበባን ያማከለ ጥያቄ ላይ እንዳይገኝ እራሱን በፍቃዱ በማግለል ፖለቲካዊ suicide በራሱ ላይ ባልፈፀመ ነበር :: ብአዴን የሚጎለብት ድርጅት አይደለም! የፈለገ ሰዎችን በላይ በላይ እየከተተ ልታደስ ቢል የሚሆን አይደለም! ለምን? ምክኒያቱም እግሩ ልምሻ አለበት! ቀጥ ብሎ መቼም አይቆምም! እራሱን የሚሸከምበትና የሚያቆምበት የጀርባ አጥነት የለውም! ስለሆነም የሚታመኑበትን ይታደሳል ሲሉም ተስፋ የሚጥሉበትን የሚያሸረግዱለትን ሁሉ ይዞ ገደል የሚገባ ሲሰራም እንዲፈርስ እንዳያድግ መሰረቱ ጭቃና ረገረግ ተደርጎ ነው! ዛሬ ብዙዎችን በውስጡ ቢከትም እንደነ Masresha Setie እንደነ አሳምነው ፅጌ ወዘተ ያሉ ተወርዋሪ መሆን ይችላሉ የሚባሉን ሰዎች እንዳይሰሩ ወጥመድ ሊያደርግ ከእርሱ ውጭ ሆነው የህዝብ ታዋቂነታቸውና ታአማኒነታቸው ስላስፈራው አቅጣጫ ለመቀየስና ህዝብ ለማስነሳት አቅም አላቸው ብሎ ስላጤነ ተቀናቃኝ ሊሆኑኝ ይችላሉ ብሎ እንዳይገዳደሩት ቶሎ ጠርንፎ በስሩ አስገብቶ ስልጣን አደላድሏል:: ያደላደላቸው የስልጣን ተዋረድ ግን ልክ ጃንሆይ ድጃዝማቹንና ፊት አውራሪው ወዘተ በዘመናዊ ማእከላዊ የሚሊተሪ ማዋቀር ስራ በሚል ሴራ ከነኝህ አማራዊ በባህላዊ አደረጃጀት በስራችው ብዙ ጦር የሚያዘምቱና ጦር ተነሳ በተባለ ግዜ የየራሳቸውን ጦር አስከትተው ዳርድንበር ያስጠብቁ የነበሩን አማሮች ጦራቸውን ከስራቸው በስልት በማውጣና በማስፈታት ስሙና ማእረጉ ብቻ ሲቀራቸው የሚያዘምቱትም ሆነ ደሞዙም ሳይኖር ጭራ ይዘው ብቻ ቁጭ እንዲሉ እንዳደረጓቸው አይነት ሴራ ነው ብአዴን የሚፈፅመው! ያም ይኸም አማራውን ከውስጥ የመፍታትና ወታደራዊ አቅሙን የማምከን ሴራ ነው! (ጃንሆይ ግን አማራ አይደሉ እንዴ እያልክ የምትሟዘዝ ቂል አትጠፋም ዝም ብለህ አንብብ)

እናም ይህ ወርቃማ እድል ብአዴን ሰው የሚሆን ድርጅት ቢሆን ኖሮ ጠበቅና ረዘም ባለ መግለጫ ብአዴንም ሆነ የአማራው ህዝብ አዲስ አበባን በአማራ ታሪካዊ ግዛትነት እንደሚያውቅና ሆኖም እንደተመሰረተችበት አላማ ዋና ከተማነቷ ብዙኃኑን ከየስፍራው አቅፋ የምትኖር ብዙ ማህበረሰቦች በውስጧ የሚያድሩ መሆናቸውን ቢያትት ኖር የሚከተሉትን ውጤታማነት ይቀዳጅ ነበር :-

1) የአዲስ አበባን የአማራ ርስትነት ላይ በማስመር ብሄርተኝነት እንቅስቃሴውን ከማገዝ ባሻገር ለራሱም ጠንካራ constituents በማበጀት ብሎም አብንና ሌሎች መስል አማራ እንቅስቃሴዎች ላይ በአማራነት ትግል ልቆ መታየት ይችል ነበር:: በሰጠው መግለጫ የአማራውን ድጋፍ የማጣቱን ሂደቱን አበራክቷል::

2) በአዲስ አበባ የሚኖሩ አብዛኞችን ማህበረሰባት ቀልብና ልብ ይስብ ነበር! የሌሎች እንደ ጉራጌ ወዘተ አይነት ማህበረሰባትን አጋርነት ድጋፍን ከውጭ ማግኘት የሚችልበት አጋጣሚን እንደ ጉም አበነነ:: የጎለበተ የራሱን መብት አስከብሮ የቆመ ድርጅት ሲያዮት ነው ሌሎች ንኡስ ማህበረሰባትም ልባቸውን በአንድ ድርጅት ላይ የሚጥሉት! ብአዴን እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ እንዲሉ ድሮም ከቁጥር የሚከተው አልነበረም አሁን ደግሞ ይልቁን ከመጤፍም እንዳይቆጠር ሆኗል! “የሁሉም ነው” የሚለው በራሱ የኔ ነው ከሚለው ድምፅ እኩል አይገዳደርምና! ማንም ለራሱ ላልሆነ ነገር ከመኖር ውጭ መስዋእትነትን አይከፍልበትማ! ብአዴን የእኔ ነው ቢል ግን ሌሎችም አጋርነታቸውን ብአዴንን በማጎልበት በጦርም ይሁን ሰላማዊ መንገድ ለማጎልበትና ለማጀብ ይነሳሱ ነበር! አሁን ግን የኔ ነው ብሎ ፊንፊን ለሚለው እብሪተኛ ጀግኖ በተፈናፋኙ እኩል ባለ ቆራጥነት ዞር በል ማለት አልቻለምና እንኳን የሌሎቹን ያማራውንም ድጋፍ አሳጥቶትል!

3) የኔ ናት ለሚለው ስኳር የቃመ ህፃን ተንቀዥቃዥ ኬኛ ፖለቲከኞች ግልፅ ባለ የኔ ነው የሚለው ድርጅት አጥቷል ማለት ነው! በይገባኛል ጥያቄው ተቀናቃኝ የለውም ማለት ነው:: ይህ ብአዴንን ወደ ብሄራዊ መድረኮች ዝር እንዳይልና በዛው በኩሽናው እንዲቀመጥ የሚያደርግ ነው! የምጎለብትበትን ዋና ምክኒያት አጥቷል!

–የብአዴን ሲጠሩ አቤት ሲላኩ ውዴት የኩሽና ሎሌ ፖለቲካው–

ብአዴንን ይህ የዛሬው የባሪያ መልሱ እዛው ከኩሽና እንዳይወጣ ባለፈው አመታት እንዳየነው የገረድ ሲጠሩ አቤት ሲላኩ ውዴት ፖለቲካው ላይ ማሸርገድና ሽርጡን ለብሶ የሌሎቹን ፖለቲካ አብሳይ መሆኑ ይቀጥላል! ገዱና ግብረ ሀይሉ ከሆዱ በላይ ማሰብ የሚያስችል የትምህርትም ሆነ የስብእና ማንነት የለውምና ይሄም ለርሱ ያልታሰበ እጅግም ሊደርስበት የማያልመውን ቦታ ነው! ስለሆነ “የሁሉም ነው” እያለ ተመልሶ ወጡን ይወጠውጣል!

ኦነግን (ኦዴድ አብር ጀዋር ዳውድ ወዘተ) መግጠም የሚቻለው እነሱ እራሳቸው በያዙት ፅንፍ ልክ ብቻ ነው! Counterpart አጥተው እያክለፈለፋቸውና ይህንን ሰው በላ ኬኛ አላዛኝ የኔ ብቻ ፖለቲካ እቅዳቸውን በሌሎች አገሪቷ ክፍል ላይ ሁሉ ለመተግበር ተነስተዋል! አብይም ፈቶ ለቋቸው ቤት ያስፈርስል! ሰው ያፈናቅላል!

አዲስ አበባ የሁሉ ከሆነች ታዲያ ብአዴን አማራ በዘር ተነጥሎ ሲፈናቀል ካዲሳበባ ምነው ዝም አለ? እንደው ለይስሙላው በራሱ የባሪያ ትርክት ምነው ዜጎቼ አይፈናቀሉብኝ አዲስ አበባ የሁሉም ናት ለምን አላለም? ሆድ ሲያቅ ዶሮ ማታ አሉ!

በፖለቲካ አንዴ የድንበር ጥያቄህን አውርደህ የሁሉም ካልክ ወዲያ መልሰህ የኔ የምትልበት አግባብ የለም! አሰብን በአንድ እብድ ሰውዬ የማሽቋለጥ ፖለቲካ ምክኒያት እንዳጣነው ሁሉ ዳግም መጠየቅ የማይታሰብ ነው! አለም ቁጭ ብሎ ተፈራርሟላ! አይደለም እንዲህና እንዲያ ሆኖብን ነው ብንል አይሆንም!ጦር ብቻ ነው ሊፈታው የሚችለው ያ ደግሞ እንዳይሆንconventional war እንክፈት ብንል እንኳን አለም እራሱ አይፈቅድም! የቀረ ጉዳይ ነው!

እናም የዛሬውን አይነት ዋና ፀረ አማራ ውሳኔ አማራን ርስት አልባ ለማድርግ የሚደረግን በሞግዚት እጅ ግዛቶችን የማስቀመጥን ሴራ አለመግንዘብ ዋጋ ያስከፍላል! አማራ አክትቪስቶች በሙሉ ይህንን መግለጫ በመቃወም ብአዴንን አማራ ህዝብን ውክልና እንደሌለው ማሳየት ይገባል!

መለስ በአሰብ የፈፀመብንንን አይነት ስህተት ነው ብአዴን የሚፈፅመው! ሁለቱም ስህተቶች ሆን ተብሎ አማራን ርስቱን የመቀማት ሴራ ናቸው!

አዱ ገነት የሁሉም ከሆነች ምነው የአዋሳውን ጉዳይ በተመሳሳይ ብአዴን አላወሳበትም? የሲዳማ ጥያቄ ላይ ብዙ ነዋሪው አማራ የሆነበትን ይህንን ከተማ ምነው የሁሉም ናት አላለም ብአዴን?

በር ጠባቂ ካፖው ብአዴንን ሳንጥል አንዲት እርምጃ ወደፊት መራመድ አንችም!

ጥሩ ሰዎች ነን የሚሉም አማሮች ከዚህ የበሰበሰ የወያኔ ስሪትና ቅሪት ድርጅት እራሳቸውን ቶሎ ቢያገልሉ ከታሪክ ተጠያቂነት ያመልጣሉ!

“ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር”

**** ወጥር አማራ*****

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራን

#Ethiopia #AddisAbeba #ADP #Amhara