ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጂግራ ነች ይሏታል ***

0
1919

ሲዳማንም በ40/40/20 አፓርታይድ ለመያዝ የኦሮሞ አክራሪዎች ሴራ ሲግለጥ::

የሲዳማው ወደ ክልልነት መምጣት ለምን በነጀዋር ይቀነቀናል? ጉዳዩ እንዲህ ነው:: አዋሳ የታወቀቺዋ ያማራ መዲና ነች! አማራን ሄደህ ሄደህ በኢትዮጱያ ወርድና ስፋት ልክ አታጣውም! አማራን የማታገኘው ሲኦል ብቻ ነው::

የድሬደዋን እጣ ፈንታ ልትጎነጭ መራራ ፅዋ ልትጋት ያለችው ሲዳማ-ሀዋሳ ናት! በሲዳማ ውስጥ የአማራው ቁጥር ሲዳማን ተገዳድሮ የሚገኝ ነው:: በተለይም በአዋሳ! ብሎም ሌሎች ማህበረሰባትን ታቅፋለች!

እናም የነ ጀዋር ቀመር ከየትም አልመጣም ያው የጌታቸውን የመለስን ስልት በድሬደዋ ላይ የተገበረውን ስልት ሊደግሙ ነው አላማቸው! መለስ ዜናዊ አፈር ይክበደውና ድሬደዋን ሐረር የቻርተር ተብላ እንድትካለል አደረገ። ብዙም ሳይቆይ ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ክልል 13 ትካለል ተባለ ይህም የቆየው ለወራት ብቻ ነበር። እንደገና ሀገሪቷ በ9 ክልል ስትከለል የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ተብላ በምድር ላይ ጩጬ ክልል ሆና ተወለደች።

EJOTTE POWER (ቄሮ በማሊያ)

ዛሬም የነጀዋር አጉል ድጋፍ የሚቸሯት ነገ የድሬደዋን ፅዋ አማራውን ሊያጠጡት ነው:: ቄሮ የሚባለው ስድ የወጣቶች ማፊያ ቡድን አገር በጥብጠውበት ጨርሰው አሁን ስሙን ቀይረውለት ኢጆቴ ብለው ሊያርዱበት እየተዘጋጁ ይገኛሉ::

የሃረሪ ክልል 18 ቀበሌ የኦሮሞ ገጠር ቀበሌዎችን 7 የሃሪሪ ከተማ ቀበሌዎችን 12 የአማራ ፣የጉራጌ ብሄር ተወላጆችን አዋቅራ 36 ወንበር ያለው ምክር ቤት አዋቀረች። 19 ወንበር ከሃሪሪ ብሄር የተከለለ ማንም ሰው ሊወዳደርበት አይችልም። 18 ወንበሩ ለ18 ገጠር ቀበሌዎች እና 12 ከተማ ቀበሌዎች ሲሰጥ ከኦሆዲድ በስተቀረ ማንም ሊወዳደር አይችልም ተባለ። የክልሉ የስራ ቋንቋ የሐረሪ እና የኦሮሞ ቋንቋ ብቻ ተደረገ። አማርኛ ተናጋሪዎች ያለውክልና አንዲቀሩ ተደረገ። ምንም እንኳ አብላጫው ነዋሪ አማራ ቢሆንም ቅሉ!

40/40/20 የሚለው ቀመር ጀመረ! አማራው ከንግድ ከመንግስት ስራ ወዘተ ተገለለ ግላጭ በሆነ አፓርታይድ!

Sidama should have been a federal city given its composition.

ይህንኑ በሃረር ላይ ህውሀቶች የተጠቀሙትን ስልት እነጀዋርም ሊደግሙ ተነስተዋል:: ስለሆነም ከሲዳማ በመጣ ጥያቄ ሳይሆን ከውጭ በመጣ ጥያቄ ቅስቀሳ ተደርጎ ዛሬ ያየነውን ትር ኢት ለማየት በቅተናል! አንዳንድ የአማራ አክትቪስቶች ይህንን ጉዳይ በጥልቅ ሳይመረምሩ እደግፋለሁ ገለመሌ ሲሉ ተሰምተዋል:: አስተውሉ! እንዲያው ለcheap rhetoric አትሩጡ! የዚህች አገር ፖለቲካና ሴራ ግማዱ ስውር ነውና! በዚህ መልክ ሲዳማን ከፋፍለው ካዳከሙ በኃላ በሰፊው አማራ ነዋሪነት ያላትን አዋሳን በእጅ አዙር በእጃቸው ያስገባሉ ማለት ነው!

ከኛም ለሲዳሞቹ ይከፋል! እንዴት? አንዴ ሀረርን በ40/40/20 ከጠፈነጉ በኃላ ሶማሌውን ሀረሪውን አማራውን እንዴት እይደረጉት እንደነበር የዛሬ ሶስት ሳምንት ያየነው ነው:: ኬኛ ፖለቲካቸውን በመቀጠል ሀረር ኬኛ ጀምረዋል:: ሶማሊውን ጥግ አስይዘውታ! የሲዳማ ከደቡብ ህብረት ወጥቶ በራሱ መቆም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለው የመቀመጫ ቁጥር በፍጥነት ያሽቆለቁላል ብዬም አስባለሁ ብዙም የህጉን አተገባበር ባላጤነውም::

“ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር”

**** ወጥር አማራ*****

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ