ንቁ እና አንቁ

0
1773

አብንን ተናገርሽ ተብዬ በየካሜንት ባክሱ ስሜ በተነሳ ቁጥር እዘለዘላለሁ! እርድ ስጋ ብሆን ኖሮ ጥሩ ጥብስ ወይንም ቋንጣ ይወጣኝ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ውዝፍ ስጋ ሆንኩባችሁ 😫 እንዳማራችሁ ሳትበሉ በማስቀሬቴ እቅርታ! 🥶

== አብን ==

አብን 129 ቢሮ በአገሪቷ ስፋትና ወርድ ወጥቼ ወርጀ ከፈትሁላችሁ ብሎናል:: እኛም ደስ ብሎናል! ዛዲያ በምን ሂሳብ እሱ ደብረ ማርቆስ ላይ ቢሮ ከፍቶ ሳለ፥ እያነቃሁኝ ነኝ ብሎ ሳለ፥ ባለ 129 ቢሮ ሳለ፥ ግምቦት ዜሮ በቆረጣ ያለምንም መርህ በደፈናው ኢትዮጴ ደቡቤ ስታይል ቆርጣ ገብታ ደብረ ማርቆስን ደብረ ግምቦት ዜሮ አደረገችው? እውነት እውነቷን ተነጋግረን እርስ በእርስ አጉል መሞካሸት ትተን tough loveቬን ተቀብላችሁ ተመከሩ! Tough love gift for Valentines from me ተቀበሉ! ጥሩ ልጅ ሁኑና አታልቅሱ ግን ምክርን ዋጥ ስልቅጥ አድርጉ! ቆፈጠን በሉ! ትንሽ ትግላችሁ መቆንጠጥ ፈልጓል! እኔ ደግሞ ጥፍሬ አድጓል ትንሽ ልመዘልግበት ያሻል! መቼም በህት መመዝለግ ይሻላል አይደል? አህያ ቢዛለል ነውና ነገሩ… አዲስ አበባ ላይ በየማኪያቶ ቤቱ እና በከሰሩ ሚዲያ አውታሮች በእናንተ ከኪሳራ ሊወጡ በሚደረግ ግብዣ ሰፍ እያላችሁ ከመንጠልጠል፥ ለኤሊቱና ከተሜው ህዝብ ብቻ ተደራሽነት ያለውን ትንታኔውን ትታችሁ ቶሎ ወደ ገጠሪቱ አማራ ምድር ተሰማርታችሁ ወረቀት መበተን፥ ሰው አስር አስራምስት እያደረጋችሁ ካለፈም ሜዳ የሞላችሁ፥ ጉሮሮዋችሁ እስኪነቃ አስተምሩና አንቁ! ብሬን ዋሽ አድርጉ! ፌስቡኩን ለኛ ተውልን! ማለቴ እኛ እዚህ እንወጥራለን እናንተ ግን መሬቱን አጥብቃችሁ ያዙልን! መሬት ላይ ወጥሩልን! በቶሎ ይህንን ማድረግና የከሰሩ ሊሞቱ አንድ ሀሙስ የቀራቸው የስልሳው ፖለቲካኞችን በህዝባችን ላይ ቀልድ አስቁሙ! ይህ በሆነ ቁጥር ከመወቀስና በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን አታመልጡም!

==ብአዴን ባንዳው ካፖው==

ይህ የባሮች ስብስብ ግምቦት ዜሮ ናችሁ እያለ ስንት አማራን ልጆች እያሰረ፥ እየደበደበ፥ አይን እያወጣ፥ ጀርባ እየሰበረ እንቁ ልጆቻችንን በአጭር የቀጨው ማሊያ ለባሽ ትግሬ ሰራሹ ብአዴን ዛሬ ደግሞ ተላላኪው ናችሁ እያለ ያሰረበትን ይህንኑ ግምቦት ዜሮን ክልሉን ከፋፍቶለት እንዲፈነጭበት ቅስቀሳ ስራውን ሁሉ የሚሰራለት እራሱ ብአዴን ከጢብኛ በጀቱ እየቆረጠ መሆኑ ይታወቅ!

==የግምቦት ዜሮ ==

ሲደራጅ ጀምሮ ተልእኮው በእጅ አዙር አማራውን በወጥመድ ለማስገባት የተሰራ ፀረ- አማራ ስሪት ደቡቤ ነፃ አውጭ ነው! ስለሆነም ባለፉት ግዜያት ተልእኮው potential የሆነ ተቃዋሚ ሆኖ እንዳይነሳና እንዳያንሰራራ ዱር ቤቴ ሊል የሚችለውን አማራ በኤርትራ trap በማድረግ ወያኔን አገልግሏል:: ኤርትራ ውስጥ ትግል ሜዳ ሳይሆን እስር ቤቶች ብቻ ነበሩት ይህ ድርጅት አማሮችን አጉሮ የሚያሰቃይበት እንደነበር ይፋ ሆኗል! ኤርትራ የገባውን አማራን ሁሉ ወይ አኮላሽቶ፥ ወይ በፅኑ ደብድቦ ሰባብሮ፥ ወይ ጨርሶ ገድሎ ጨርሷል! እነ ዘመነ ካሴም ቢሆኑ በblackmail ተይዘው ትንፍሽ እንዳይሉ ሆነዋል! ያው ተመልሰውም የግምቦት ዜሮ ቀኝ እጅ ብአዴን ስር መግባት ነውና ያላቸው ብቸኛ ምርጫ! ሌሎች ደግሞ ወደፊትም መጥተው በተለያዩ ሚዲያዎች ተናግረዋል:: ምፅዋ ላይ ቦርጩን እያሻሸ ሜሎቲ እየደበሰቀ የከረመው ብርሀኑ በደቡቤ አይን አውጣ ዋሾ ባህላቸው ዛሬም ህዝቡን ያምታታሉ!

==ደብረማርቆስ ==

በግነት ጥሩ ነው! ነገር ግን በግነት ለውነተኛው እረኛ ለመድሀኒተ አለም እንጂ በግነት ለደቡቤ የተኩላ ስብስብ ከሆነ ግን ናና ዘነጣጥለኝ ማለት ይሆንባችኃል! ከደብረ ማርቆስ ነኝ ማለት ከሞኞች የጅላንፎ መንደር ነኝ ማለትም ይሆንባችኃል ዳግም ለእንደዚህ ያለ ስድ ስብሰባ መታደም! የደብረማርቆስ ወጣት ለስምህና ለገፅታህ አስብ! በጣም ታስጠሉና ታሳፍሩ ነበር በስብሰባው ገፅታችሁ! አላዋቂ ሆናችሁ ለአለም ታያችሁ! እኛም አፈርን! ሀፍረታችሁ የኛም ሀፍረት ይሆን ዘንድ ደማችን ናችሁና! አላወቅንም ማለት አትችሉም! የነዚህን ነፍሰ በላዎች ስራ የማያውቅ ማንም የለምና! አለማወቃችሁ እራሱ የገልቱ ማህበር ስለሚያደርጋችሁ በግዜ እወቁ! ለእርድ በእ እ እ እያላችሁ ሰው ሳላችሁ እንሰሳ አትምሰሉ! አታሳፍሩት ደብራችሁን! ማርቆስ ሳይሆን ማፈር ደብር አታደርጉት! ይህንን ለም አለች ብላችሁ እሪ ብትሉ የሚያስተጋባልህ ገደል ማሚቱ የለም ጉሮሮህ ይነቃል እንጂ! ይህንን ብልግና ደብረታቦር ላይ አይተን ነበር:: በጎንደር አይተነዋል! እንዴት የኮማሪ ፖለቲከኞች ሴሰኝነት ማብረጃ ትሆናላችሁ?

አስተውሉ! ታቀቡ! እራሳችሁን ውቀሱ! ንስሀም ግቡ!

ይህንን ነውር ገናም በአንዳንድ ስፍራ እናየው ይሆናል አብን እራሱን እስኪያነቃ! ወይ ነዶ!

አብን ሆይ ንቃ! ተደራጅ! አብን ሆይ ስራ ስራ! አብን ሆይ ቢሮዎችሁን ስብሰባ እየጠራህ ለማንቃት ስብሰባ መጥሪያ አድርገው እንጂ የፖለቲካ ድራማ መስሪያና መስፈርት ለማሟያ እንደው አለን ለማለት አይሁንብህ! ቢራ ማስተዋወቁን ተውና ሰው አንቃ! የፈረሰ እምነት ተምቋምና የተፈናቀለ ህዝብ እየፈለግህ ሄደህ ፎቶ እየተእሳህ “እነገሌን የአብን አመራሮች ጎብኝተዋል” የሚል የአቢቹ አይነት ፌስቡክ photo and PR stunt በቶሎ አቁም!

ወይንስ እናንተም አንቂ ትፈልጋላችሁ? ምን ሽግር አለው ኑ ወደ እኔ እንዲያ ተሆነ ጉዳዮ!

ሊዲያ ዘ ጊዮን ብሄረ አማራ!