አካሄዳችን ቅልበሳ ያስፈልገዋል!

0
1242

አማሮች አሸንፈን ወደ ቀደመ ክብራችን መመለስ ካሻን የህዝባችን ስነልቦናዊ ስሪት እና ባሕል የግድ መለወጥ አለበት:: እኛኮ አገር ያነፅን ነን:: ለዘመናት የቆየ መንግስት ሥርዎ መንግስትና የፍትህ ስርዓትን ያሰፈንን ነን:: የራሳችን የሆነ የመማር ማስተማር ሂደትን የሃይማኖት ቀኖናን ያፀናን ገዳማት መስጊዶችን የገነባንና ልዩ ጣዕመ ዜማን ያሰረፅን ነን:: የግዕዝ ሥነጽሑፍን ያሳደግን: ቅኔን የዘረፍን ያሬዳዊ ዝማሬንና መንዙማውን ባይነት ባይነቱ ያንቆረቆርን ነን:: አሁን የሀበሻ/የኢትዮጵያ ባሕል የሚባለውንና በሌሎች “ጫኑብን” እየተባልን የምንከሰስበት አምጠን ወልደን: ተንከባክበን አሳድገን ለሌሎች ያጋራን ለጋሶች ነን:: ያለቀለት ሸጋ ባሕልንስ ለሌሎች በመቸራችን በመመስገን ፈንታስ ስለምን እንከሰስበታለን? የሌሎች ጎሳዎች ባህል አሁንም ሳይነካካ ያለ ቢሆንም ከአማራው ያሸበረቀ ባህል ጋር መገዳደር ስላልቻለ የኛው ባህል የበለጠውን ሊያሸበርቅ ችሏል::

የአማራ ባህልንና ሂፕ ሃፕ ሙዚቃን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር በሌሎች ዘንድ ራሳቸው ካላቸው ነገር በልጠው መወደዳቸው ነው:: አማራ ያልሆኑ አያሌ ዝናን ያተረፉ ገጣሚያን እና ጸሐፍት በኢትዮጵያ ምድር ኖረው አልፈዋል:: ይህ የሚያሳየው የአማርኛ ቋንቋ አሁንም በሌሎች ምን ያክል ተወዳጅ እንደሆነ ነው:: አማርኛ ነገሮችን የመግለፅ አቅሙ እጅጉን የጎለበተ በመሆኑ አብዛኞች የትግሬና ኦሮሞ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ስለህዝባቸው በአማርኛ በመፃፍና በመናገር ሃሳባቸውን ያስተጋባሉ::

ይህ የአገር ግንባታና ባህልን የማውረስ አበርክቶ ከቱርኮች: ሩሲያውያን: አረቦች እንግሊዞችና ፐርሺያዎች ጎን የሚያሰልፈን ይሆናል:: እኒህ ህዝቦች እንደሻማ ቀልጠው ለሌሎች ነገዶች አገርና ባህልን አበርክተዋል:: አገር ገንቢና ባህልን አውራሽ በመሆናችን የተነሳ የአማራ ስነ ልቦና ከጎሳዊ መዋቅር ጋር የተጣላና ከግለሰባዊነት ጋር የተጣባ ነው:: አማሮች ማህበራዊ ችግሮች (የፀጥታና ምጣኔ ሀብትን ጨምሮ) ለመንግስታዊ መዋቅሮች የሚተው ናቸው ብለው ያስባሉ:: ይህ ለግለሰባዊ የአማሮች ባህል ሊጣጣም የሚችለው ፍፁማዊ መስፍነ መንግስት ያለባቸው ምዕራባውያን አገራት ጋር ነው:: ለዚህም ነው ባለፉት 27 ዓመታት የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው ፀረ አማራ ጎሳዊ አገዛዝ የማይገጥም ብቻ ሳይሆን ምቹ ታዳኝም የሆነው:: በመሆኑም ህዝባችን በሁለት በኩል በተሳለ ሰይፍ ሲገዘገዝ ኖረ:: ከአገዛዙ ጋር የማይጣጣመው ግለሰባዊ ባህሉና ፀረ አማራ በሆነ የጎሰኞች አገዛዝ::

“ለመኖር ብቁ ስትሆን ብቻ ትኖራለህ” በሚለው የዳርዊን ህግ መሰረት አማሮች ለመኖር ሥነ ህዝባዊ ስሪታችን ላይ አብዮታዊ ለውጥን ማምጣት አለብን:: ለችግሮቻችን መፍትሄ ከመንግስታዊ መዋቅር መጠበቅን ለደህንነችን ሲባል እርግፍ አርገን መተው አለብን:: ግለሰባዊ ባህልና አስተሳሰባችንን በመጣል ጎሰኞች እንደሚያደርጉት አንዳችን ላንዳችን ዘብ መቆምን መልመድ አለብን:: በየአካባቢያችን ተደራጅተን መንደራችን ከጥቃት መከላከል አለብን:: በህብረት የማሰብ ባህላችን የበለጠ ማዳበርና ይሉኝታን አሽቀንጥረን ጥለን ከባላንጣዎቻችን በበለጠ ፈርጥመንና ፀንፈን ለፍልሚያ መቅረብ አለብን:: የበለጠ ቸልተኞች እየሆንን በመጣን ቁጥር ባላንጣዎቻችን የኛ የሆነን ሁሉ ከመንጠቅ ወደሗላ አይሉም:: የአዲስ አበባን ጉዳይ ማየት ብቻ በቂ ነው::

አማራ ተራመድ!

ይህንን ፅሁፍ ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ ለተረጎመው ወንድማችን GM Melaku ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁኝ::

ሊድያ ዘ አዲስ አበባ ግዮን አማራ