የኤርትራ ቀጣይ ጉዞ ወደዚህ ወይስ እዚያው

0
1099

የኤርትራዊያኑ ፖለቲካቸው መካከል ሁለት ትልልቅ ቤቶች ይታያሉ:: ንኡስ አካላትም አሉ በዚህ በህለቱ ትልቅ ስንጥ መኃል:: ስለ ብብዙኃኑ አይደለም የማወራው:: ብዙኃን ያው ብዙኃነው:: ኤርትራ ይሁን ኢትዮጵያ ኬኒያ ይሁን ጃካርታ ብዙኃን አንድ ነገር ታሲዘዋለህ እሱን እንደ ዳዊት ሲደግም ይኖራል:: በእርግጥ በአፍሪቃ ቀንድ በፖለቲካ ንቃት ቢመዛዘን ኤርትራዊያኖቹ በመጀመሪያው ተርታ ከሚሰለፉ ሶስት አገራት የመጀመሪያ የሚሆኑት!

ወደ ሀሳቤ ስመለስ ያጤንኳቸው እነዚህ ሁለት ቤቶች አንደኛው የኢሳያስ ክንፍ ነው:: ሌላው ደግሞ የምሁራኑ/elit ክፍል የሆኖ ግን የኢሳያስና የኤርትራ ዲፕሎማሳዊ እርምጃና አካኄድ እያሰጋቸውና ገና አሁን ጥርጣሬ እያጫረባቸው ያለ ይመስላል:: ሌሎችም እስካሁን ዝም በለው አንድ ሰአት ጨምረው በሀያ አምስተኛ ሰአት ላይ ጥርጣሪያቸውን ወርዋሪ ሆነው እስከ ዛሬ የት ነበራችሁ እየተባሉ ነው::

አንድ በተመለከትኩት ቪዲዮ በእድሜያቸው በግምት ወደ ስልሳዎቹ አጋማሽ ላይ ያሉ ጠበቃ ሰውዬ በእንግሊዝኛ ያደረጉት ሀተታ ስሰማ አንዳችን ነገር አስገነዘበኝ:: ከዛም ብዙ ያለውን ውጥረት ዝግ ከሆነው ቤታቸውና ሚስጥር ከማይባክንበት ፖለቲካቸው ሊካድና ሊደበቅ ያልቻሉ እውነቶች እንደ ጀበና ቡና ፉር እያለ ወደ ላይ መገንፈል የጀመረበትን ሁኔታ እንዳለ አይቻለሁ::

ለጥምቀት አውድ አመት በጎንደር የቀድሞ የኢትዮጵያን ካርታ ተንጠልጥሎ ባደባባይ ማየታችንን የአማራውን ብሄርተኞች ማስቆጣቱ ይታወሳል:: እናም ባደረግነው ክትትል እነማን ለምን ሲሉ ካርታውን እንዳሳሉት ግልፅ ሊሆን አልቻለም:: ከዚህ ኃላ በተጠናከረ ቁፈራ ጀመርኩኝ:: ወዲያውም ማህበራዊ ሚዲያው በቀድሞ በኢትዮጵያ ካርታ ይጥለቀለቅ ጀመር:: ኦኬይ አንድ trend አለ ማለት ነው ብዬ ዱካ ስፈልግ ያው በእርግጠኝነት የሞተችዋ ግምቦቴ የመጨረሻ ጠብ አጫሪነት ገብታ በአማራው ጉያ ውስጥ ሆና ያደረገችው ይሆናል እያልኩ የማገኘው ፍንጭ ይህንን በሀሳቤ ሰንቄ እያብሰለስልኩ የደረስኩበት ድምዳሜ ግን በተጨባጭ ልለው በምችለው ሁኔታው ከግምቦት ዜሮ ካምፕ አለመሆኑን ነው:: ለነገሩ እንዲህ የሰፋ እቅድና ambitionንም የላትም ግምቦት ዜሮ::

ይህንን ስራ የሚሰራው ግን ማን ነው? ለምን? ምን አይነት የፖለቲካ እድምታን ለመፍጠር ነው? የአብይ መንግስት? ለምን ሲል? ወዘተ ብዙ ጥያቄዎች አጥለቀለቁኝ….

የደረስኩበት ማሳረጊያው ይህ ካርታ ከኤርትራዊያኑ ከኢሳያስ ክንፍ ከሆነው at lower rank ኦፐሬት የሚያደርግ ክፍል ለመሆኑ ምንም ጥርጥር ይለኝም:: ኢሳያስ ከአብይ ጋራ ያደረገው ስምምምነት እስካሁን ምን ይዞታ እንዳለው አናውቅም:: ፊርማ የሰፈረው በምን ውል ነው? እርቁስ የትኛውን ቅሬታ አስወግዶ ተከናወነ? እኛም ኤርትራዊያኑም blindsighted ተደርገናል:: ቦርደሮቹም ማርክ አልተደረጉም! ብቻ ይከፈታል ይዘጋል ያለው:: ብዙ የኢስያስንና የአብይን ሽርሽሮች back and forth visitation አይተናል:: ያም ብቻ አይደለም አስመራ ድረስ የክልል ርእሰ አስተዳደሮችን እየጠራ ኢሳያስ አነጋግሯል:: ገዱን ከነቲሙ ለማንም እንዲሁ ከነቲሙ ጠርቶ ለማናገር ምን አይነት ፕሮቶኮል እንደፈቀደላቸውና አሁንም በምን ላይ ምክክሩና ስምምነቶች እንደተካኄደ የሚያውቅ ማንም የለም:: አማራም ክልልም ኦሮሚያም ክልል ሳይሆኑ አገራት የሆኑ ይመስል እራሳቸውን እየወከሉ የሄዱበት ጉዳይ እንቆቅልሽ ነው::

ወደ ጉዳይ ስንገባ የኢሳያስ ክንፍ የኤርትራን ቦርደር ስልታዊ በሆነ መልክ በመክፈት ከዚህም እዚያ እሄዱ መስራት መነገድ መማር ወዘተረፈ አይነት ግንኙነቶችን ያለ ገድብ ለማዳበር በመክፈት ቀስ ብሎ ውጥረቱንና የቦርደ መስመር ስስነት ለማስወገድ በማላመድ ቦርደሩንና አገር አድርጎ የሚለየንን ውጥረት dissolve እያደረጉ ወደ አንድ የምስራቅ አፍሪቃ አገራት ወደ መሆን ከOne World Order አራማጅ አበዳሪዎቻቸውና አሳዳሪዎቻቸው የተሰጠ አጀንዳ ያለ ይመስላል:: ይህንን ኤርትራዊያኑ በአፅንኦ እየተከታተሉ ይገኛሉ:: ውጥረትም አለ:: ብዙኃኑ የከፈለውን ዋጋ ሁሉ ላለፈው ሀምሳ አመት የከፈለው ለኤርትራ ሉአላዊነት ነውና ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል የሚል ነገር ቁስላቸው ላይ ሆምጣጤ ማፍሰስ ነው የሚሆነው::ለዚህም ነው አበክረውበማህበራዊ ድህረ ገፆች በተለቀቁት በካርታዎች ላይ ጠበቅ ያለ እርማትንና ማስተካከያን የሰጡት!

ሁለተኛው ክፍል የኢሳያስን ስልታዊ በለሆስስ የሚሄድን አረሳስቶ እየፈታ ያለውን ብሎን እየለቃቀሙና መልሰው ለማጥበቅ ጠንከር ያለ አስተያየትንና ኢሳያስን በthreason እስከመክሰስ የደረሰ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ::

በእውነት የኢስያስ ህልሙ በፍሪቃ ቀንድ ላይ ትልቅ አገርን መዘውር ነውን? አብይስ ቦታው ምን ሊሆን ይችላል? የእኛስ የአገራችን ሁኔታ በዚህ ዝርክርኳ ወጥቶ የምትናጠው ልናተኩርበት የሚገባ ሌላ የሚሸረብ ጉድይ ስላለ ይሆንን?

በኤርትራ የነገሰው የፖለቲካ ውጥረት የሚያጭረው ብዙ ጉዳይ አለ? የቤት ስራው ብዙ ነውና ነቅተን መከታተል ይበጀናል::

ምእራባዊያኑ በቅጥረኞቻቸው በአብይና በኢሳይስ በኩል በአፍሪቃ ቀንድ ላይ ወደ ሚፈልጉት አቅጣጫ ለመምራል ግፋ በለው ያሉበት ሁኔታ እንዳለ ይታያል::

አማራ ነቅተህ ተከታተል:: ይኸ ነገር ለኛ ነው! በአማራ ኪሳራ ላይ ብቻ የሚሰራ የአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ ነው ያለው:: ከገለበጥነው ደግሞ የአማራ መጠናከር ሁሉንም አድክሞ ማለፍ ይችላል:: የኛ ግን መዳክም የነኝህን ሁሉ ኃይላት መጠናከር ዋናው መሰረቱ ነው! ኤርትራዊያኑን የሚያደርስላቸው ካለ እኛ አማሮች በእራሳችን ቆም ነውና አጀንዳችን የእናንተን አገር ደግሞ ጨምሮ በላያችን ለመለጠፍና ካርታ ለማሰሪያ ግዜም ፍላጎቱም አጀንዳውም የሌለን መሆኑ ይሰመርበት!

በመጨረሻም:- ይህችን ፎቶ ተመልከቷት እስኪና authenticityዋን አጣሩልኝ!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ