ሁለቱ የሚዲያ ወጎች

0
1131

እስራኤል የመርሳት ችሎታው ልክ እንደ ዛሬው የአማራ ህዝብ ነበረ። አሁን ነግረኽው አሁን የሚረሳ። እዚህ ጋራ ተራራ ሲጨስ፣ ከሰማይ ክብር ሲወርድ፣ ተራራ ሲንቀጠቀጥ፣ የነበረው ክብር የሚታየው ግርማ ሲያስደነግጥ፣ ምድር ሸብ እረብ ስትል ፈጣሪዋን ልትሸከም አቅም ዓጥታ፣ ከህያዋን አምላክ ፊት ከክብሩ መንጸባረቅ የተነሳ ቃዴስ ሲነዋወጥ፤ ህዝበ እስራኤንን የብርሀኑን ጨረር አድርቆ እንዳያስቀረው የክብር አምላክ በደመናና ጨለማ እራሱን ጋርዶ ሲወርድ አይቶ የጮኽው እስራኤል ሙሴ ወደ ተራራው ተጠርቶ ትንሽም ሳይቆይ ያንን ሁሉ ረስቶ፤ ሙሴ እስኪወርድ መታገስ አቅቶት ለራሱ ችግር እራሱ መላ ሊል አምላኩን ፈጥኖ ረስቶ ወርቅ አቅልጦ ጥጃ ሰርቶ መሴን ጠበቀው። ሙሴም በጣም ስለነደደው በዛ ሁሉ ክብር የሆነውንና በእግዚአብሄር ጣቶች የተጻፈውን ድንጋይ ወርውሮ ሰበረው። የአሮንና የእስራኤል መንፈሳዊ ውስልትናቸውን መታገስ ቢሳነው ወርውሮ በእጁ የያዘውን ለህይወት የሆነችይቱን ህገ ፅላቷን ሰባበራት! አርባ ቀንና አርባ ለሊት ቆይቶ ያመጣውን ክቡር ድንጋይ በዘመናችን አነጋገር አግዚአብሄር ሎድ አድርጎ የሰጠው የመጀመሪያ ታብሌት ነበር ሰብሮ ከጥቅም ውጭ ያደረገው። ምን ያደርግ?! የማይገባው ዝንጉ ህዝብ መኃል ሲኮን ተበሳጭና ተንገብጋቢ ነው የሚያደርገው። መፅሀፍ እኮ ሙሴን በጣም ትኹት ሰው ነበር ይለዋል ነገር ግን እንዲያ ብስጩ የሚያደርገው ህዝቡ ነበር። ቁጡ ነች ትሉኝ የለ እኔንስ 🙂 የሚያስቅ ነገር እንዳለ ሁሉ?! ጥጋበኛስ እመስላችሁ የለምን አንዳንዴ! እንዲሁ እኮ ነው መተጣጣት።

እና ቅዳሜ ማታ ጽፌላችሁ ትሎ ደግሞ ረስታችሁ ዛሬ አንድ ኩንታል ጸጉር ተሸክማ፣ ልቅ በሆነ አንደበቷ ያለ ሙያዋ እንዳሻት የምትለፋደድን እዚህ ግቢ የማትባል የወሬ ጣቢያ ወረኛን እንደ አጀንዳ ታዞራላችሁ። አናታችሁ ላይ የሚወረወር ባገኝ እኔም በወረወርኩባችሁ ነበር። ማንም እየኼደ በወሬ ጣቢያ በጉራ ዘለል ሰው መዘለፍ የፈለገ ይዘለፍ ይህ የእኛ አጀንዳ አይደለም። በመሰረቱ ማንም ጋዜጠኝነት በበቂ ትምህርት ፊልዱ አድርጎ ያላጠና ሰው ቢጋብዘኝ ለመሄድ ፍቃደኛ አልሆንም፤ እራሳችን ደርጃውን (standard) መድበንና አውጥተን ካልተንቀሳቀስን እንደ በግ የትም ሄዶ በእእእእ ማለት ይሆናል ትርፉ። ይህች ቤቲ የምትባል ሴት ምንም አታጣም ምንም አይቀርባትምም ሰዎችን በማበሻቀጥ (she has nothing to lose) እርሷ ጋር የሚሄዱ ሰዎች ግን ስንት ስራ የሰሩና በመስካቸው አንቱ የተባሉ ሰዎች ናቸውና ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል። ከሁሉ የሚብሰው ሰቅጣጩ ጉዳይ ደግሞ “ጋዜጠኛዋ” የሚሏት ጋዜጠኝነት ምን እንደሆነ የማያውቁ ሰዎችን ማየት ነው!

ወደ ገደለው ስንገባ– ቅዳሜ ማታ እንደጽፍኩላችሁ መሰረት ሚድያ ሁለት ግብአት አለው:-

፩) ነገር ማሳየት

፪) ነገር መፍጠር

አከመቼ ነገር ሲፈጠርብህና አጀንዳ ስታስበላ ትኖራለህ ወገኔ? በእውነት ፌስቡክ ላይ የበዛው ስራ ፈት መሆን አለበት። ናቅ አድርጎ በራስ ስራ መጠመድ ባህልን ተማሩ አስኪ። መንደር ለመንደር ወሬ የሚያዞሩ ቡና ዓጣጭ ወረኛ ሴቶችን መሰላች ሁሳ?! ሀይ!

ዋናው ኣንገብጋቢ ነገር ማሳያ ልስጣችሁ:-

፩) ሀረር አማራ ጉዳይ

፪) የአዲስ አበባን ድብቅ የማወረም አኩይ ተግባር

፫) የቡሌ ሆራ ተማሪዎች ጉዳይ

፬) ደራ ሸዋ የጨዋዎች ሀገር ጉዳይ

፭) በአማራ ክልል ዐሁንም አድብቶ ያለ የቅማንት ኮሚቴ ስሩ አልተነቀለም

፮) ማሰልጠኛ እስከመክፈት የተጠናከረው የጠላት ሀይል በገዱ ዐንዳርጋቸው ንህዝላልነት ዐሁንም ለጥቃት ዕየተንቀሳቀሰ በለሆሳስ እየሰራ አንደሚገኝ ይታወቅ

፯) ሱር ኮንስትራክሽን የተባለ የወያኔና የአብይ እዝ አሁን አማራ ክልልን ለመረበሽ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ

፰) የኣማራ ማንነት ኮሚቴ የተነሳለትን ድንበሮቻችንን የማስመለስ አላማ በየቀኑ ንቃት፣ ጩኽት የሚፈልግ ስራ ነው።

፱) የስደተኞች አዋጅ በሚል የሚተገበር አገርን የማፍረስ ስውር ሴራ

ይህ ነው በተጨባጭ እየሆነና እየተተገበረ ያለ አንገብጋቢ ጉዳይ:: ትኩረታችንን ያለምንም ማወላዳት ይሻል:: ስንት ችግር እያለብን አጀንዳ እንዳጣ ሌላ አጀንዳ አታስቆልሉብን! ለዚህ ነው ሁላችን አንፃፍ የምለው:: ትኩረት ሰጥተው የሚንቀሳቀሱን ፀሀፍት መከተል ያሻል:: ግድ ነው!

ሚዲያ ነገር ሲፈጥርህ በተቀደደ ቦይ አትፍሰስ ጠላቶችህ ይኼኔ ይሄ ጅል አያሉ በንቃተ ህሊናህ ላይ ይሳለቁበታልና።

ሚዲያዊ ነገር ፈጠራ ለማዘናጋት:-

፩) በረከት ታሰረ

፪) ይልቃል በባለጌ ልጅ ተጠየቀ

፫)አላሙዲን ተፈታ

፬) መራራ ጉዲና ሀይለስላሴ ኦሮሞ ነው አለ ወዘተ

፭) ፋሲል የእኔ አለም በደደብነቱ አመረረ ኢሳት በቅጥረኝነቱና በፀረ- አማራነቱ በረታ

ሆን ብለው ጠላቶች ልክ በዋና ጉዳያችን ላይ ስናተኩር ኮልኮሌ ምሁራን ተብዬዎቻቸውንና ትራዝ ነጠቅ ሰዎቻቸውን ወደ ሚድያ በማምጣት አማራን ትኩረት ለማስቀየስ ይጠቀሙባቸዋል። በየቀኑ ለፍጆታ የሚለቀቁ ማዘናጊያዎችን አንደ በግ እየሰማህ በዚያ ላይ ስታላዝን አትዋል አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሌለው ህዝብ፤ አታሰድብ እራህን፣ አታስገምት ንቃተ ህሊናህን። ጠላቶች ጠጃቸውን ይዘው የታባቱ ደሞ ለሳምንት ይነጫነጭ ይሁኻልና። ትንሽ ጋብ ሲልልህ የቂል ጩኸትህ ደግሞ አንደኛውን ይልኩና “ይኩኖ አምላክ ጃፓናዊ ነበር” ይልሀል አንተ ለዚህም ትነጫነጫለህ አጀብ ነው መቼም። ምን ብንሆን እንዲህ ደደብን! ማነጫነጫ ኣጀንዳ ነድፈውልሀል ካልሰለችህ ይግቱኃል። ትጋተው ቁጭ በልና። ኦሮሞ አክራሪው እንኳ ተሳለቀብህ ስርአትን ጠልተሀልና፣ አልገራ ብለሀንልና፣ ራእይ አላነግብ ብለህ መረን ወጥተሀልና።

አደብ ግዛ አንደወንድ፣ ስርአትን አንግቢ እንደ ብልህ ሴት ለሳር ለቅጠሉ እያላዘናችሁ እኛንም አታድክሙን። በማያስፈልግ አጀንዳ ትግል አትጎትቱ። አደብ ግዙ ወይ ከአማራው ትግል ጫንቃ ላይ ውረዱ። አሰዳቢ አትሁኑ በራሳችሁ አማላዋቂነት የተነሳ።

ተንቆ መታለፍ ያለበት ጉዳይ ተንቆ ይታለፍ። ስራውን እንደሆን መሬት እየተሰራ ነው። አንዴም ሚዲያውን ስኝዝ አንዲህ ያሉ የሞኝ ባገኝ ክስተቶች የስም ማጠልሸትና ማበሻቀጦችን በቀላል የምንፈታው ይሆናል። እስከሲያው እንደ አንድ ስልት ልታደርጉት የሚገባ ነገር ቢኖር ጋጥ የወጣ ነገርን እንደዛሬው ስታዩ ንቆ በማለፍ ችሎታ ማለፍ። እውቅናን በመንሳት አቧራውን ከመጨስ መታደግ። ሁለተኛ ስልት የሚሆነው የዚህ አይነት ጥቃት ሲከፈት ቶሎ ወደ ውስጥ ዘለቅ ያለ ዓጀንዳዎችን ለምሳሌ ከ15ኛው ክፍለ ዘመንና ከዚያ በኃላ በኢትዮጱያ ላይ የኦሮሞ ወረራ ያስከተልወን ውድቀት በስፋት መቃኛ ግዜ ማድረግ ወዘተ ይሁን ስራችን።

በፍጹም በፍጹም ግን በተወረወረልህ አጅንዳ ዳግም ገብተህ የነገሪባው መሳቂያ መሳለቂያ አትሁን። እራስህን ታደግ ከዚህ አይነት ቂዥቢነት:: ይህንንምየህልውና ጋሬጣ ሆኖ አግኝቼዋለሁ!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ