መርህ አልባ ባቢሎኒያዊነት

0
1203

መርህ አልባነት ባቢሎኒያዊ ያደርጋል

*********************************

እንግዲህ በጣም አጠያያቂ እየሆነ ያለው ጉዳይ በተለይም በጠላቶቻችን ዘንዳ አማራው የሚጋራው አንድ ስነልቦና አለው ወይ በማለት ሸንቋጭ ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳል። ይህ ጥያቄ ምንም እንኳን ተንኳሽ ቢሆንም ቅሉ ግን የምናሳያቸው ያለመናበብ ብሎም ጠላቶቻችን ከሚጠሉን በላይ እርስ በእርስ መጠላላታችን አንደኛው ምክኒያት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ አንድ የተቀረጽንበት የሚያናብበን መርህ ስለሌን ነው። አንዱ ወገን የኅልውና አደጋ አለብን ይልና መልሶ ከአብይ እና ከህገ መንግስቱ መላ ይጠብቃል፤ ሌላኛው ደግሞ ኅልውና እያለ በህገ መንግስቱ ተደራጅቶ ያንኑ የተደራጀበትን ህገ መንግስት ይፍረስ ይላል። ሌላኛው ደግሞ የለም ኅልውና ካልን በራሳችን ቆመን እራሳችንን ካለብን ፈተና መክተን የራሳችንን መንግስት በማቆም ለወያኔው አብይ ለሚተገብረው ህገ መንግስትን በመሻር ያለምንም ጥያቄ ወደ መንግስትነት ልንመጣ ይገባናል ይላል ያ የእኔ ጎራ በጣም ትቂት ሰው ያለበት ነው፤ በጣት የሚቆጠር ሰው ነው ይህንን ህሳቤ ያሚያጠናጥነው። ይህንን ህሳቤ ያራመድንበት መድረክ እንኳ ዛሬ ዛሬ ከዚጅም ከዚያ ተሻሽቶ ይህንን የጠራ ሀሳብ አደፍርሶታል። ሰለሆነም ነው የዚህ ህሳቤ አቀንቃኞች ቀን በገፋ የተመናመን ያለነው። ቢሆንም አዋጪው መንገድ ስለሆነ ይዋል ይደር እንጂ ይህ ህሳቤ ብቸኛ አማራጭነቱን ሁሉም የሚረዳው ግዜ እሩቅ አይሆንም፤ ስለዚህም ጠንካራ የሆነ በብቃት የታጨቁ ሰዎች አስፈላጊ በመሆኑን በጠራና በማያወላዳ የራስን አድል በእራስ ለመወሰንና በዐጭር ግዜ ገደብ ነጻ ለመውጣት በትኩስ ኃይል አንድ አሰባሳቢ የሚሆነን ድርጅት ማቋቋም ግድ ይላል።

የአማራው ህዝብ መናበብ ያቃተው አንድ መርህ ስላላነገበ ነው። ኅልውና የምትልውን ቃል ሁሉም ይጠቅሳታል ግን ኅልውናን ለማስጠበቅ የሚኬክበትን መንገድ ካለማወቅም ባሻገር ኅልውናውን አደጋ ላይ ከጣደው ህሳቤ ገለል ብሎ ነገሮችን ማየት አልተቻለም። አማራ ብሄረተኝነት ትልቅ አደጋ ተጋርጦበታል። እየከሰመ የሚሄድ ነገር ግን እንደ ማሽላ በእሳት ላይ እየፈካ ያለ ይመስላል። ማሽላ ሲያርር ይስቃል ይባላል። ግን ከሳቁ በኃላ ይበላል ይቆረጠማል። ስለሆነ ባለው የተለያየ አማራዊ የመሰለ እንቅስቃሴ እየተሳበ ምንም መርሆ ሳይሰርጽና በመጣው አጀንዳ አየተወሰደ ዘራፍ ዘራፌዋው በተለቀቀው ሙቀት አየተንጣጣ አንደ ፈንዲሻ ፈክቶ መክሰሙ ስለሆነ ቶሎ ሰከን ብሎ ከብአዴን ኣዴፓ ስር መርመጥመጥ ትተን፣ ከህገ መንግስቱ ስር ማሸርገድ አቁመን ሉዐላዊነታችንን በአንድ ህሳቤ ላይ ተተክለን አለመታየት ይሄ የተበታተነ አስተሳሰብ አንድ ስነ ልቦና አንዳለመያዝ ይወሰዳል፤ ደግሞም ሊያስኬድ ይችላል። በአንድ ህሳቤ አለመተከል አማራን ዳግም መልሶ መቃብር መክተት ይሆናል፤ Mesganaw ምን አለኝ በቀደም ለታ ”እኛ እኮ ብሄርተኝነቱን ባቀጣጠልነው ሰአት ባናቀጣጥለው ኖሮ አልቆልን ነበር” ሲለኝ እኔ ደግሞ ”አይ አልቆልን እንዳሉትም ቀብረውን ነበር። በተለይ የተሰራብንን የግፍና የዝርፊያ ብዛት ስናይ ሞተን ተቀብረን ነበር ነገር ግን የእኛ ትግል ያደረገው ትንሳኤ ነው ለአማራ።” አልኩት የትንሳኤ ኃይል ደግሞ ሞትንም ያሸነፈ ነውና ግዙፍ ነው።

እናም ወገን እንዴት ይናበብ ይህ ትግል ትላላችሁ? ዝም ብለን ሁላችንም ጸሀፍትና ኮማች ሆነን በላይክ እየናወዝን አገር የገዛን እየመሰለን እንዲሁ እንዲሁ እያልን ትግሉ ይክሰም ወይንስ አደብ ገዝተን፣መርሆ አበጅተን፣ ጥቂቶችን አንደ ኦሮሞው ትግል ፊት አቁመን ሌሎች ከኃላ እንስራ ወይንስ ሁላችንም ስንለፈልፍና ስንጽፍ መርህ አልባ ሆነን መናበብ አቅቶን ኅልውናችን ደግሞ ባለመናበብ ጥያቄ ይግባ? ወገን እንኳል ለሌሎች እኛንም ግር ያሰኛል የልዩነታችን ብዛትና ስፋት፣ ቶሎ ተሽመድማጅነት፣ በአላማ አለመክረም፣ ላለፈ ላገደመ ለተሰራ ለተፈሳው ሁሉ ማጨብጨብ ጥያቄ ያስገባል፤ እረ በስነልቦና ይህንን ያህል መተጣጣት ያስነወረናል። ጠላቶች በሰሩልን ብአዴን ገብተን የነሱን ሹም ሽር ስናጽድቅ ስለታሰረ ሰው ስናሞግስእንዳንናበብ የሰሩብን ሴራ ተከናውኖ ዛሬም ዳግም አንድ ህዝብ ሆነን አስር ሀሳብ ሲወጥረን፣ አንድ ኅልውና ይዘን አስር መንገድ ስንሮጥ እንኳን ለጠላት ለገዛ ልጆቻችንም ግራ ይገባል።

በመርህ ልንደራጅ ግድ ይላል። መርህ አልባነት ወደ ባቢሎኒያንነት አየለወጠን ከጥያቄ አያስገባን ዛሬም አማራ የሚል ኃይል ተነስቶ ግን መናበብ ስላልቻለ በስነልቦናችን ላይ ያለ ትልቅ ክፍተት ለጠላቶች በመሳሪያነት እያገለገለ እንዲቀጥል ያደርገዋል። ኣንድ ቀን ብአዴንን ይኮንኗል በተነገው ያሞግሷል ምን ያለ ኣዲሳባ ነው አለች ከጎጃም የመጣች ዘመዴ ድብልቅልቁ ግር ቢላት። ምን ያለ ትግል ነው አንድ ቋንቋ የማያናብበው ጃል?

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ