አፓርታይድ አማራ

0
1139

አማራነት በሐረር ከተማ

============================

ዘመናትን በጉያዋ ውስጥ ደብቃ በ19 ቀበሌዎች የተከፋፈለች ከተማ ነች። የከተማው ህዝብ በአመዛኙ አማራ እና ኦሮሚኛ ፣ አደሪኛ ፣ ሶማሊኛና ጉራጌኛ ተናጋሪዎች ይኖሩባታል። በአዲሱ የወያኔዎች ካርታ ሐረር ቻርተር በሚል ተከለለች። ብዙም ሳይቆይ ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ክልል 13 ትካለል ተባለ:: ይህም የቆየው ለወራት ብቻ ነበር። እንደገና ሀገሪቷ በ9 ክልል ስትከለል የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ተብላ በምድር ላይ ጩጬ ክልል ሆና ተወለደች። ህውሀት ሰራሽ ሆና:: ከክልል ወደ ክልል መዘዋወር በሚል ህግ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወደ ክልላቸው እንዲሄዱ ሲደረጉ ሌሎቹ ደግሞ በጊዜው አነጋገር ኃላቀር ወደሚባሉት ክልሎች እዲሄዱ ተደረገ ። በሌላ ክልል የነበሩ የሐረር ተወለጆች በብርሃን ፍጥነት ከከተማዋ ወጡ። የሐረሪ ክልል 18 ቀበሌ የኦሮሞ ገጠር ቀበሌዎችን 7 የሐሪሪ ከተማ ቀበሌዎችን 12 የአማራ፣ የጉራጌ ብሄር ተወላጆችን አዋቅራ 36 ወንበር ያለው ምክር ቤት አዋቀረች። 19 ወንበር ለሐሪሪ ብሄር የተከለለ ማንም ሰው ሊወዳደርበት እዳይችል ተደረገ::18 ወንበሩ ለ18 ገጠር ቀበሌዎች እና 12 ከተማ ቀበሌዎች ሲሰጥ ከኦሆዲድ በስተቀረ ማንም ሊወዳደር አይችልም ተባለ። የክልሉ የስራ ቋንቋ የሐረሪ እና የኦሮሞ ቋንቋ ብቻ ተደረገ። አማርኛ ተናጋሪዎች ያለውክልና አንዲቀር ሆን ተብሎ ተደረገ። ግላጭ ፀረ አማራው አፓርታይድ በይፋ ስራን ጀመረ::

ንግድ*

የመጀመሪያ የተመታው የንግድ ሴክተር በኮትሮባንድ ስም በዘረፋ አና በቃጠሎ እንዲወድም ተደረገ። ብዙዎች ተፈናቅለው ለስደት፣ ለረሃብና ለእርዛት ተዳረጉ። በነገራቸን ላይ ይህ ኦፕሬሽን አጋአዚ (አለበል ያቋቋመው ኃይል) የተባለው ሰው በላ ኮማንዶ የተሰማራበት እና የምስራቅ እዝ ደህንነት ሃይል በመታገዝ ያከናወነው ነው።

በመንግሥት ስራ ለይ ተሰማርተው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች 40/25 በሚል ህግ በጡረታ እንዲወገዱ እንዲባረሩ ተደረገ ። አማራ የሆነ ሰው በመንግስት ስራ ላይ ላለመቀጠር በግልፅ ተግባራዊ ተደረገ። ፀረ አማራ አፓርታድ ግብአት ቁጥር ሁለት:: ኦሮምኛ እና ሐረሪ ቋንቋን እንኳን ቢናገሩ በኃላፊነት ቦታ እዳይመደቡ አደረጉ። “ሂድ አትበለው እንዲሄድ ግን አደርገው” በሚለው በወያኔ ስልት እንዲህ ተደረገ።

የደሴ ላኮሞልዛ ሆቴል ባለቤት ላይ የተፈፀመ ግ

================================

አቶ ደጀኔ በሐረር ከተማ የእውቅ ሆቴል ባለቤት ነበሩ አሁንም አሉ። ደጀኔ ከተራ ሽንኩርት ነጋዴነት ተነስተው በብዙ ላብና ደካም ሃብት አፍርተው ቤተሰብ መሰርተው ሶስት ወንዶች ልጆች ወልደው በላባቸው ጥረው ግረው የሚኖሩ ሰው ናቸው።

ወያኔዎች በሐረር እና በኦሮሚያ ውስጥ አማራ በፖሊሲ ደረጃ ትምክህተኛ ነው ብለው አቋም ስለያዙ ይህንን ትምክህት ከስራ በማባረር ብቻ ማጥፋት ስለማይቻል የማፈናቀል ስራ ወይም እንደተስፋዬ ገብረዓብ አገላለፅ ማስደንበር ( በነገራቸን ላይ የደጀኔን ታሪክ ፅፎታል) አዲደረግበት ሲወሰን ለዚህ ክፉ ዓላማ የታጩት እኚህ ጎልማሳ ከነቤተሰባቸው ነበር።

የታቀደው አማራው ህዝብ በስፋት ሊያውቀው እና ሊሰማቸው በሚችልበት ቀን ነበር። ጥር 11 የጥምቀት ቀን ተከናወነ። አቶ ደጄኔ ለብዙ አመት በቤታቸው በአሰተናጋጅነት ሲሰራ የቆየውን አለሙ የተባለ በብዙ የሃረር ነዋሪዎች የተወደደ ሰው ገድለው ሚካኤል ቤተክርስቲያን በር ላይ ፊቱ አዳይታወቅ በድንጋይ ቀጠቅጠው ጥለዋል ተብሎ ሆቴሉ በኮማንዶ ተከቦ ለእስር ተደረጉ።

ሆቴል ወስጥ አልጋ ይዞ የነበረ በአጠቃላይ ወደ እስር ቤት ለምርመራ በሚል ለእስር ተደረገ። ሕዝብ አማራ አንገቱን ደፋ ታታሪው ፣ ሠራተኛው ፣ የእመነቱ ሰው ከልጆቹ ጋር በመሆን ያወም ቅዱስ ሚካኤል በር ለይ በንግሱ ቀን ….ህዝብ ጠላው ፀሀፊውም እኔም አብሬ ጠልቻለሁ አይ እኔ ።

ልጆቹ በተለያየ እስር ቤት እዲታሰሩ ተደረጉ ሲደበደቧቸው ሚኪ የሚባለው ልጁ ጆሮው ደንቁሮ ቀርቷል:: ደጀኔ አልቅሶ ለመነ አኔ ሰው አልገደልኩም ልጆቼ ንፁሐን ናቸው ቢል ማን ሰምቶት የፖለቲካ የጥላቻው ፖለቲካ ሰለባ መሆኑን ማን አውቆት?! የዚህ ጉዳይ አስፈፃሚዎች ሰለሞን ሃይሉ የተባለ የድሬደዋ አሰተዳዳሪ አሁን የሰራው ግፍ አሸመደምዶት የጣለው አኩይ ጌትነት የተባለ ፍልጥ መሀይም አሁን ድሬደዋ ቤቶች ልማት የሚሰራ ከተማ የሚባል የቀድሞው መቶ ዓለቃ አሁንም የአማራን ህዝብ በማስቀጥቀጥ እና በማፈናቀል የችርቻሮ ለቋሚ ባንዳ የብአዴን የሐረሪ ካድሬ ሲሆን ኮማንደር ሙራድ ከክልሉ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ነው።

አምስት አመት አካባቢ ሲሆን ደጀኔ ሚስቱን አጣ ለመቅበርም አልታደለም:: ለሰራው ማስፋፊያ ተብሎ ከባንክ በተበደረው ብደር ምክንያት ለዘመናት የኖረበት መኖሪያ በባንክ እዳ ምክነያት ተሸጠ:: ወደ ባህርዳር የተቀየረ የፖሊስ መኮንን ፍቼ ለጥምቀት አውድ አመት ማታውን ጥምቀቱን ለማየት ሲዘዋወር በአቶ ደጀኔ ተገድሏል የተባለውን የኦሮምኛ እሰክሰታውን እየደቃ አለሙን እያየ ነፍሱን እሰኪስት ሲያቀልጠው ያገኘዋል።

አሁን ደሞ ሐረር በአዲስ ዜና ተናወጠች ከወያኔ ማንም አንደማያመልጥ ፍትህ ትዘገያለች አንጂ አይጠፋም ተባለ። ደጀኔ በአለሙ ሞት መታሰሩ አግባብ እንዳልሆነ ተናግሮ ተለቀቀ።

ግን ሲለቀቅ ሚስት የለውም:: ሃብቱ አንደጉም በኖዓል:: ልጆቹ ከጥቅም ውጨ ሆነዋል። አንድ ሰሞን ታዋቂ በነበረው የታገደ የሙሉጌታ ሉሌ መጽሔት ላይ ታሪኩ ታትሞ ነበር።

ደጀኔ አሁኑም ሐረር ደሴ ሆቴል ዘመን ባለፈበት ወንበርና ጠረቤዛ ለእለት ጉርሱ ይታትራል። ይቅርታ ያለው ሰው የለ፣ ካሳ የከፈለው ሰው የለ ፣አማራን ለማስደንገጥ በተጠነሰሰ ሴራ ሰለባ ሆኖ ይኖራል። ወገኖቼ አማራነት ጥቃት ነው አማራነት ወጥመድ ነው። ብሔረተኛ አልሆንም ብትል ነህ ይሉሃል።ፖለቲካ አያገባኝም ብትል ጥለቻ ያሳረረው እስካለ ደረስ ያጠፉሃል።

ባለፉት 27 አመታት አማራ በሃረር አንዲህ ኖረ:: ዛሬ ለይቶላቸው ገጀራ ይዘው ወጥተዋል:: ነገ ይህንን አይነት ድርጊት በአዲስ አበባ አዋሳ ሻሸመኔ ናዝሬት ወዘተ ላለማየታችን ምን ማረጋገጫና ተስፋ አለን? ሀረር ላይ የሆነ ሁሉ በነዚህና መሰል ከተሞች ተፈፅሟልና!