ዘርፈ ብዙ የአማራ ጠልነት ስልቶች

0
1281

ቀንደኛ የአማራ ጠልነት ስልቶች:-

1) ዘር አጥፊነት ( Genocidal)

ክህደት— አማራ የለም! ማንኛውም ዘር አጥፊ መነሻው የአንድን ህዝብ ህልውና መካድ ነው። ክህደት የህላዌ አደጋ ቅድመ ሁኔታ ነው። የሌለ ነገር አይሞትማ!

2) እርኩሰት (Rubbishing)

ማጣጣል— ኤጭ! የአልቃሻ ፖለቲካ በዛብን ይልሃል።እሱ ግን ለ50 ዓመት “ምኒልክ አያቶቼን በድለዋል” እያለ በእኝኝ አርጅቷል።

መቀባት— አማራነትህን ስትቀበል ዘረኛነት ወይም በትህትና ማዳላት/ወገንተኝነት ነው ይልሃል ። እሱ ግን ብሄረሰቡን ለማሳየት ስሙን እስካያቱ ይፅፋል። ወይም ቡልቻ ዲ. ዴነቢ ነኝ ይልሃል አማርኛውን ለማጥፋት።

3) ማሸበር (terrorizing)

ሟርት:- ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ፣ ህዝብ ለህዝብ ይጋጫል ፣ እሳትና ድኝ ይዘንባል አማራ ከተደራጀ።

ማስፈራራት:- እረ እባካችሁ ከክልሉ ውጭ የሚኖረው አማራ ይጠቃል ይላል ቅቤ አንጓቹ ደግሞ። እዚህ ቤት እሳት የለም?

4) መረምረም (neutralizing)

አማራ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ተበድሏል፣ የስርዓት ችግር ነው። ለአማራ የተለየ ጭቆና አልነበረም የለምም የሚል ጥቅመኛ ዴሞክራት ቢጤ ነው። ራሱ ያመረተውን ስታቲስቲክስ እንኳን ይረሳዋል።

5) ቀላማጅነት (double standard)

“ህወሃትና ትግሬ አንድ አይደሉም” ይልሃል ጮክ ብሎ።ከላይ ስታየው ትክክል ነው። ትናንት ግን “አማራ በደለኝ ፣ስሜን ለወጠ ፣ አፍንጫዬን ደፈጠጠ” ብሎ ሲጮህ የነበረ ነው። ለአማራ ሲሆን ሚዛኑ ሸቃባ ነው!

6) መቀየድ (Diversion)

ለአማራ ህዝብ መብት ስትቆም ፣ አማራ ካላችሁኝ እውነት ነው ስትል ፣ ይሄ “የአማራ ባህሪ አይደለም” ይልሃል ተንቀዥቅዦ። ወያኔ በቀደደው ቦይ ፈሰስክለት ብሎ ይመፃደቃል። ወይም “ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው” እያለ ራሱን ያሞኛል።

ተፃፈ ቴወድሮስ ሃይለማሪያም.