የአብይ አማራን የማዳከም ሴራዊ ፖለቲካው

0
4009

አብይና አማራን የማዳከም ሴራዊ ፖለቲካው

እንግዲህ ወለጋ በዳውድ ኢብሳና በከማል ገቹ መኃል ባለ ቁርሾ ይታመሳል ተብለናል:: ትናንትናም በጣም አስቂኝ የሆነ ከመከላከያ አይደለም ከሸምሱ ሱቅ የማይሰማ ቀልድ “መጠነኛ የአየር ድብደባ” አድርገናል ብሏል መንግስት:: የአየር ድብደባ ከመሆኑ ከመመጠኑ እንስካሁን በዳውድና በከማል፥ ኦህዴድና ኦነግ መሀል በተደረገ አለ የተባልነው የእርስ በእርስ ጦር አንድም ተንቀስቃሽም ይሁን ቋሚ ምስል ያየነው የለም! እውነት ቢሆን ኖሮ ፌስቡኩ በእሳት በነደደ ነበር:: ስለ ወለጋው ሲፅፉ በአማርኛ ይፅፋሉ ሆን ብለው በኦሮሞው መካከል ያለው ኮድ አይረቤውንና false flagጉን በአማርኛ መፃፍ ነውና!

እነዚህም ሰለጠኑብን ማለት ነው! ለእኛ ጋብ ባለ ቁጥር ከአብይና ከግምቦት ሰባት ብሎም ከኦነግና ወያኔ ካምፕ አጀንዳ እየተሰላ ይሰጣል የቤት ስራ መሆኑ ነው::

ሽፍታ ተባል እዬዬ ትላለህ:: ነገ ይመጣና ደግሞ ወሮበላ ይላል እሱን ይዘህ ታለቅሳለህ:: ክርስቲያን ታደለ ተነካብን ኡኡ ትላለህ:: ለተወረወረው ጠጠር ሁሉ ትወድቃለህ:: አስር ቪዲዮ እየቀነጫጨብክ እንደ ሎቶሪ አዟሪ ስድብና ምፀትን ታዞራለህ! እንዲህ እንዲህ ስንል እነሱ አገራቸውን ሰርተው እርስታችንን በጫጭቀው እራፊ ላይ ይተውናል ማለት ነው!

የታወቁ ፖለቲካውንም የገሩ leading figure የሆኑ አማራ አክትቪስቶች መቀናጀትና በራሳችን አጀንዳ ላይ ብቻ እናተኩር ዘንድ መናበብና ማናበብ ይጠበቅባቸዋል:: ከአብይ ካምፕ፥ ከብርሀኑ ነጋ ካምፕ፥ ከኦነግ ካምፕ፥ ከወያኔ ካምፕ ከዚህ ሁሉ ጉሮኖ የተለያየ ጠብ አጫሪ ፀረ-አማራ ነገሮች የሚለቀቁት አንድም የአማራውን ብሄርተኝነት በመከላከል ላይ ጥዶ ለማስቀረት ነው:: ሲቀጥልም የኛ ፖለቲካ በልዕልና ከእነርሱ እዬዬ ፖለቲካ ስለሚለይ ወደ እራሳችው ልክ ሊያወርዱንም ነው! አልፎም በዋና ጉዳያችን ላይ ትኩረትን ሲሰርቁ ነው::. ጉዳያችን እንደነ ኦነግና ህውሀት ልብ ወለድ ባለመሆኑ ይህ ብሶትና እራስን መከላከል እያደገ መሄዱና ተጠያቂዎችን ማንበርከኩ ያስፈራቸዋልናም ነው! ሌላው ሸፍጥ ደግሞ በውስጥ የሚደርሱ ተቀናጅቶ ተፅፈው የሚመጡ አጋልጡ የሚሉ መልእክቶች ናቸው የራሳችንን ሰዎች በጠላትነት እንዲፈረጁ የሚያደርጉ የሴራ ፖለቲካቸው ሲሰላብን ነው:: ይኸ የፎቶ መለጠፊያ የሙዚቃ መለጠፊያ አስር መስኮት እየከፈቱ መተርተሪያ ግዜ አይደለምና ይብቃን:: ልብ ገዝተን ቆፍጠን ብለን ከዋና አክትቪስቶች በመናበብ የሚለቀቁ አማራዊ አጀንዳዎች ላይ እንጠመድ እባካችሁ! ጠላት ሞት እየደገሰልን ነውና!

“ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር”

**** ወጥር አማራ*****

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ