የስራ ምስክረነታችን ቀንበር በላያችን ነው እስኪመሰክርልን ድረስ

0
1037

አንድ ብሄርተኛ ስለ እራሱ ያለፈ ማንነት ሲከራከር አይውልም! ብሄርተኛ ከሆነ ዛሬ ቡሌ ሆራ ተማሪዎች ላይ ብአዴን/አዴፓ እያደረሰ ያለውን ስልታዊ ጭፍጨፋ በማጋለጥና ለህዝብ በማሳወቅ ይጠመዳል እንጂ! ብሄርተኛ የራሱ ማንነት ሳይሆን የህዝብ የቀን ተቀን እልቂት ይገደዋል! በትብብር አብረው የሚሰሩ ሁሉ ዝምታን መርጠው ስለ አንድ ግለሰብ ላለፈው የማይፋቅና የማይካድ የፖለቲካ ማንነት ጥብቅና ቆምው ባፋጣኝ ከአጥቂነት ወደ ተከላካይነት አፈር በበላችው ግምቦት ሰራዊት አቧራ እየቃመ ይገኛል:: አሳማ ጭቃውን ይወዳል! አሳማ ጋር ሄዶ የሚላፋ እሱም እንደዛው ሆኗል! አስማው ግን ያለ ምንም ጥያቄ ጭቃው ላይ እየፈሳ በመደባለል ይበልጥኃልና ጭቃ ሜዳውን ትተህ አዳሜ ወደ ትግላችን ማማ ሰገነቱ ላይ ተመለስ! ወርደህ አወራለሁ ካል ጨቅይ! የሚያግዝህ የለም! ሆኖም በብሄርተኝነቱ ፍጥነት ላይ ሀዲዱን እየያዛችሁብን ነውና ትግሉን እፍ ብለን ጭዱን ከምረን እሳቱን ያነደድን ብሄርተኞችን ስንቴ ታደናቅፉናላችሁ?

የፖለቲካ ሀ ሁንም አታውቁም እንዴ? እኔ ስንት ዘመቻ ሲዘመትብኝ በግምቦት ዜሮ ወፈ ሰማይ ዘረ ቢሶች አንድ ቀን ሰው አላገዘኝም! አንድም ቀን እገዛም አልጠየቅሁም! መልስም አልሰጣቸውም ነበር! ግን ሌት ተቀን የማንቃት ስራዬን ነበረ የምሰራው! ሎጎ “ሊዲያ ዘውዱ ነፃ አውጪ” የሚል ሰርተው ሁሉ ብዙ ብለዋል:: ridicule አድርጌው ነው የቀጠልኩት ስራዬን እንጂ ዶሴ አልፃፍኩላቸውም! ለምን? ሰው ያቀኛላ! በግዜ ሰው ያውቅኃል እስከዚያው ማሳመን የለብህም የጠራ ስራን ሰርተህ ማስመስከር እንጂ!

ዛሬ እገሌ እንዲህ ተባለ ብላችሁ እቡር ከማለት ድርጅቱ ስለ ቡሌሆራ ተማሪዎች እተባበረዋለሁ ያለው አዴፓ የሚያደርሰውን ድብደባና ጭፍጨፋ ማውገዝና ህዝብን መቀስቀስ ነው! በእውነት አዴፓነት ያለፈ ማንነት መሆኑን መስካሪው ስራ ነው! በጎንደር ስለሚደረገው ጭፍጨፋ አመፅ መጥራት ነው ከአዴፓ ቫይረስ መፈመውስን መስካሪው! አብረን በትብብር እንሰራለን ያላችሁትን ድርጅት ልትጠይቁና እጅ ልትጠመዝዙና ካልሆንእ constituteአችንን እናስነሳለን ማለት ምነው ተሳናችሁ?! በርግጥ የራሳችሁ ከአዴፓ የተለየ constitutes ካላችሁ ዌል ለችግሮች እልባት ስጡ! የተለያዩ የትግል ስልቶችን የማትጠቀሙበት ምንም ምክኒያት አይኖርም! ግን ያላችሁ ተከታይ የአዴፓ ሰራዊት ከሆነ ብቻ ነው ያላችሁን consensus ላለማፍረስ የምትገደዱት!! ይህ የአብን ትግል organic ከአዴፓ ውጭ ያለ ቅንድጅትና የራሱ ሴል ካለው በአማራ ላይ አስከፊ ጭፍጨፋ በፌደራልና በክልሉ መንግስት ሲደርስበት ስለምን ሰራዊታችሁን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ለአመፅ እንደምትነሱ በማስፈራራት ለቡሌ ሆራ ተማርዎች በሜዳ ፈስሰው ላሉ አማሮች ችግር እልባትን አታስገኙም?

ያለፈው ምንም አያሳስበኝም! ሁሏም የኢትዮጴ ፖለቲከኛ ከእኛ በጣት ከምንቆጠረው ውጪ የብአዴንና የኢህዴግ አጫፋሪ የነበረች ነች! የብአዴንን መርህ አርቃቂ አንዳርጋቸው መሆኑን አንረሳም ዛሬ ዜግነት ፖለቲካ እያለ የሚቀደደውን የእንጨት ሽበታም ፀረ- አማራነት ስራ አንዘነጋም! ፀረ- አማራው ህገ መንግስት ሲረቅቅ ውስኪ እያጣጣ አብሮ ያፀደቀ ያረቀቀ ብርሀኑ መሆኑን ምነው እረሳችሁት?! የብሄር ፖለቲካ እኛ ሳንወለድ ጫካ ገብታችሁ …… በስማችን አማራ ድርጅት ያቋቋማችሁ እነ አንዳርጋቸው ከምባቶቹ መሆናቸውን አንድነት እያለ በየአሜሪካንና በእንግሊዝ ፓስፖርት ተገላባጩ ደጋፊያችሁ በፌስቡክ የራሱን ቅል እራስነት ሲያሳይ ሃይም አትሉት?!! አንድነት የመኃይማን ጎራ! አለማወቅ ignorance is bliss ይላሉ ፈረንጆች እውነትነቱን በእናንተ ተገነዘብኩኝ! ልቀጥል ያልኩኝ እንደው ቀኑም አይበቃ! ሰውም አይተርፈኝ! በሙሉ የግምቦት አመራር ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ አገር ናት ብሎ በብሄር የከፋፈለ ነው! አሁንም በሽፋን የሚከፍል ነው!

ወደ እኛ ትግል ስመጣ አብን ሁን ማንም ትግላችንን የመከላከል defense ማስገባት አቁሙ! አጀንዳ ቅረፁ! በየቀኑ በአማራ ጉዳይ ፃፉ አስገንዝቡ ተሟገቱ! የእናንተን የግል ህይወት የቀን ውሎ የትምህርት ምርጫ ፍልስፍና ፎቶ ገለመሌ ለመስማት ለማየት አይደለም እዚህ ያለነው! ለሱ ከሆነ ሞልቷል ቀና ተብሎ የሚታይ ሊያውም! እዚህ ያለነው በሰላ ብእርና አስተሳሰብ ብሄርተኝነቱን ለማስረፅና ወደ ፊት ለመገፍተር ነው:: ትናንት ከትናት ወዲያ ስትፅፉ ያየሁት ጎንደር የጦር ቀጠና በሆነች ሰአት ሌላ ሌላ ነው:: የእኛን ዋናውን አጀንዳ የምትነኩት በገረፍ ገረፍ ነው ኢሳትን ይመስል:: የእኛን ዋናውን አጀንዳ የምትነኩት በገረፍ ገረፍ ነው ዴፓን ይመስል:: ተባበርን እንጂ አልተቀላቀልንም ካላችሁ መሞናሞኑን ለግል ስብእና በሰራዊት ጥብቅና መቆሙን ትታችሁ ዳይ ወደ ስራ:: ቡሌሆራ ተማሪዎች ከምግብ እጦትና ህመም ባሻገር የትምህርት አመቱ እየተጋመሰና እያለፈባቸው ነው እናንተ ስለአንድ የቀድሞ ብአዴን አባል ስለነበረ ሰው እናንተም ለማትክዱት ሀቅ ስትሟገቱ! ጎንደር በእሳት እየጋየች ነው እናንተ ስለአንድ አባል የፖለቲካ ህልውና ስትዋደቁ መላው አማራ ህልውናው አደጋ ውስጥ እያለ ነው!

የግምቦት ዜሮ ሰራዊት ብሎም አንድነቴው ኢትዮጴ እንደ ስዩም ያሉት ሻኛዎች ናቸው! ጭንቅላታቸው ሻኛ! አስተሳሰባቸው ሻኛ! ሰውነታቸው ሻኛ ብቻ! በላተኞች ናቸው! አገር ይበላሉ! ህዝብ ይበላሉ:: ይበላሉ! ይበላሉ! በላተኝነት የሚጠረቃ አይደለም! እነ ሀብታሙና ኤርሚያስን እዩ ምግብ የሚደፋበት አገር መጥተው ሻኛ ሆነውም ጨርሰው አሁንም ይበላሉ! አሁንም ለመብላት ይገላሉ በአፋቸው ቃል ጦር እየመዘዙ! ሻኛ ማንነታቸውን ያደልባሉ! ሻኛ ማንነት አይጠረቃም! ከመሪዎቻቸው እስከ ተከታዮቻቸው ሻኞች ናቸው!

ፖለቲከኝነታችሁን እስካሁን አልተረገጠልኝም:: ቲዎሪ ማንበብ አንድ ነገር ነው ስልቶ ግን ፖለቲካውን በእለት ተለት ጉዞው በአጀንዳ momentum ሳይቀንስ ይልቁን accelerate እያደረገ እንዲመነጨቅ በነባራዊው ሁኔታ ላት ትኩረት ሰጥቶ ማስመንጨቅ ነው ፖለቲካ ! ወገንና ቤተሰቦቻችንን እንታደግበት አታዘግዩን!

ቶሎ ትኩረት ጎንደር ላይና ቡሌ ሆራ ተማሪዎች ላይ አድርጉና እራሳችሁን ለአማራ መቆማችሁን አስመስክሩ! እስካሁን የምናየው እኛንም እያሰጋን ነውና!

“ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር”

**** ወጥር አማራ*****

**** ጎትት አፋሩም****

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ