ፍርስራሽም ሲገኝ ነው እዬዬም ሲዳላ ነው

0
1350

ፍርስራሽም ሲገኝ ነው እዬዬም ሲዳላ ነው

የተጠና ዘመናት የፈጀው ስልታዊ የ27 አመታት የህውሀት አማራ የዘር ፍጅት በግላጭ ጎንደር ላይ ከተጀመረ ያለፈው ስምንት ወራት ስልት እይለዋወጠ መካሄዱ የሚታወቅ ነው:: ላለፉት ሶስት ቀናት ግን ተባብሶና ተጠናክሮ የመንግስት ሜካናይዝድ ጦር በግላጭ አማራዊ ዘር ፍጅቱን “ሽፍታ” የሚል ስያሜ ዘመቻ በንፁኃን አማሮች ላይ ተከፍቷል:: ገዱም በሩን ይዞ “በዚህ ችግር የፌደራልን እንደ ተቋም ማውገዝ አይገባም” ሲል በሰጠው ጋዜጣዊ ሀተታ ተደምጧል!

ብዙ ግዜ እንደ ተናገርኩት ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ዑደቷን ጨርሳ ስንጥቁ እየሰፋ ወደ ጨርሶ መገመስ ላይ ደርሷል:: ይኸው በፎቶ እንደምትመለከቱትም እኔም ከሳምንት በፊት እንደፃፍኩት ትግሬ ኦልሬዲ ተገንጥሎ ሄዷል:: ኦሮሞ በር ዘግቶ ከምባታን እያረደ ነው ተስፋፊነቱ ላይ ጥያቄ እንዳይነሳ ከወዲሁ ሲገታ! በኦሮሞ ክልል ያሉ አማሮችም እየተፈጁ ይገኛሉ:: ኢትዮጵያን አራት ቦታ የመከፋፈሉ ሴራ በምእራባዊያኑ ከተጠነሰሰ ቆይቷል:: አሁን ግብዐት እያገኘ ነው:: ሶስት ቦታ ሲሰነጠቅ ምስራቅ ደቡብ ሰሜን በመሆን ይከፈላል:: አራተኛ መሆን የሚችል የነበረው አማራ ምድር ጠያቂና ወካይ በማጣቱ ተነስቷል:: ሶስት በዚህ መልክ ይገመሳሉ:-

1. ትግሬ

2. ኦሮሞ

3. ሶማሌ

ሶማሌ ወደ motherland Somalia ይጠቃለል ሲል ከወራት በፊት ኸርማን ኮኸን እንዳዘዘ አይረሳ! ይኽ ምን ያስገነዝበናል? አማራ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አልራመድ ስላልልና በምትፈርስ አገር ላይ አንድነት የሚል መጋኛዊ ጥንውት አገር አልባ እንዲያደርገን ሆኗል:: ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፍላ ባንዲራና ክልሎችን በካርታ መልክ ቀርፃ ለ27 አመት ስታላምድ አማራው ከአንድነት ከሚል መወዛገብ ሊወጣ ስላልፈለገና አውቆ አበድነትን ማቆም እምቢኝ ስላለ በዚሁ 27 አመት ሁሉም የሚፈልገውን አስምሮ በፍርስራሽ ሽርፍራፊና ትራፊ እርስት ላይ ተቀምጠን እንገኛለን:: ይህንን መለካታችንና እኛም ምንም ስላልን አሁን አይን አውጥቶ 70 ቀበሌን ከጎንደር ይዞ ትግሬ ጎጆ ሊወጣ በቅማንት ማሊያ ገብቶና በኦሮሞ ሰልፈኛ ይህን አማራ ክፍል ትንሽም ቢሆን ይታገለናል ብለው የፈሩትን ጎንደር ነበር እርሱም በገዛ ልጆቹ መከዳት ምክኒያት በከባድ ጦር ተከፍቶበት ፈፅሞ እየተፈጀ ይገኛል:: ገዱ የጦር ወንጀለኛ ነው!

የምትመለከቱትም ካርታ በምስሉ ይህንን ያውጃል! 3 ቦታ እንዲከፈል የሆነበትም ምክኒያት አማራ ነኝ ብሎ ቆሞ እርስቱን የሚጠብቅ ምሁርም ደቂቅም ስለሌለ ነው:: ኦሮሞ ደግሞ እስከላይ ወሎ ይገምሳል:: ተሸራርፎ የቀረው ክፍል የኢትዮጵያ ghetto ካደረጉት የቆየው አሁን ትልቁ የአለማችን Auschwitz ይሆናል ማለት ነው! ቆሞ ጠያቂና አማራ ነኝ ያለጠንካራ ማእከል ቢኖር ኖሮ የሚገባንን ድርሻ ወስዶ አገር ሆኖ ለመቆም ምንም ባላነስን ነበር! አማራ ክልል ከሁሉ የተሻለ የተማረ ኃይል የተሻለ የመሬት ይዞታ ያለው የሰው ኃይል እያለው የውሀ ተፈጥሮ ሀብት እያለው ህዝቡ አንገቱን አደንድኖ ለመነሳት ቤት ለቤት መጥታችሁ ቀስቅሱኝ ባይ ስለሆነ ጥፋት በደጁ ቆማለታለች:: ሰው የሚኖርበት ምድር ላይ አልነቃም ለመጠበቅ የሚባል ነገር የለም! ለዛሬው ውጥንቅጥ በግንባር ቀድምትነት ተወቃሹ እራሱ አማራውነው! ኦሮሞው ትግሬው ሶማልው ልጆቹን ስለ እርስትና ሉዐላዊነት እያስተማረ ለራሳቸው ቆመው አገር ሆነው መቆም እንደሚችሉ አድርጎ ሲያሳድግ አማራው ያስተማራቸው ልጆቹ ሳይቀሩ በቁራሽ እየተደለሉ ጡት ነካሽና ሆዳም ሆኖ ቀርቷል:: የዚሁም ማሳያ አሁን መጥታችሁ የምታሳደቡ ሆድ አደር ለቁራሽ የምትተጉ አማሮች ማሳያዬ ናችሁ! እመኑኝ ይህንንም አንብቦ መረዳት ተስኖት የሚሳደብ እርባና ቢስ የሆነው ትውልድ ሊሳደብ ይመጣል ውድቀታችን ከመሬት ወለል በታች ሆኗል!

ካርታውን ተመከቱና እርማናችሁን አውጡ! “ምንድን ነው ታዲያ” የምትል ሰላቂም አትጠፋም!

ይኸ የአብይ አዲሱ ቢሮ በEAU ኮንትራት ተወስዶ የሚሰራው ቢሮ ላይ መሬት ጥለው ከፋፍለው የሰነጣጠቁት ካርታ በመመልከት እጣ ፈንታህን እይ እንግዲህ! ወይ ትወርማለህ ወይንም ትተገርራለህ! በአንድ ፓልቶካቸው ኦሮሞች ሲያወሩ አመታት በፊት የሰማሁት ግዜው ሲደርስ አማራ ወንዶቹን መግደል ሴቱን አግብቶ ኦሮሞ ልጆች ማስወለድ የሚል ፖሊሲ ሲነድፉ ሰምቼ ነበር:: ያንኑም ነው በ14 ቡሌሆራ እንስት ተማሪዎችን በማፈን ያደረጉት!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ