ኢትዮጵያ መፍረሷ አይቀሬ ከሆነ ራሳችን አፍርሰን ትልቁን ስባሪ እንወስዳለን!

0
1580

አማራ የራሱን መንግስት ለመመስረት ጊዜው ያስገድደዋል፡፡

***************

በመጀመሪያ የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው፡፡ እኩልነቱ እንደ ሰው የመኖር መብቱን ባስመለከተ ነው፡፡ የሰው ልጅ እኩል ነው ማለት ግን አንድ አይነት ነው ማለት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ በባህልም፣ በሞራልም፣ በጸባይም፣ በታሪክም አንድ አይነት አይደለም፡፡ ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ ጠበብ ስናደርገውም ኢትዮጵያ የምትባል ፖለቲካዊት ስያሜ በውስጧ የተለያዩ ብሄሮች ይዛለች፡፡ እነዚህ ብሄሮች በቋንቋ፣ በባህል፣ በእምነት፣ በባህርይ፣ በታሪክ፣ በሞራል እሴት፣ በፍላጎትና ግብ፣ በአኗኗር ፍልስፍና እና ነገረ እሳቤ የተለያዩ ናቸው፡፡ የአንዳንዶቹ ልዩነት የማይታረቅ ቅራኔ ያለው ነው፡፡ ቅራኔውም አንዱ አንዱን እንዲያጠፋው የሚያደርስ ነው፤ ሲሆንም የኖረ ነው፡፡ ይህ ሁሉ መረን የለቀቀ እና ከሰው ልጅ የማድረግ አቅም ያለፈ የብሄሮች ቅራኔ ለዝቦ ለሁሉም የሰው ልጅ የሚሆን አገር መፍጠር አይቻልም፡፡ የሚቻለው የአማራ መንግስት መስርቶ በዚያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአማራ ባህልና ባህርይ እጅግ የቀረበ ስለሆነ ብዙ የሚከብድ አይደለም፡፡

እነዚህ እስከ መጠፋፋት የሚያደርስ ቅራኔ ያላቸው ብሄሮች እስካሁን በሀይልም በምንም ተይዘው ቆይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ጨርሰው ሳይጠፋፉ ቆይተዋል፡፡ ሩቡ የጠፋ፤ ግማሹም የጠፋ አለ፡፡ ወደሩቁ ዘመን ከሄድን ጨርሶ የጠፋም አይጠፋም፡፡ ይሁንና እነዚህ ብሄሮች ከአጼ ምኒልክ ወዲህ እርስ በእርስ የመገናኘትና በአንድ ፖለቲካዊ አስተዳደር ስር የማደር እድል ተፈጥሮላቸው ነበር፡፡ እስከ ቀኃሥም ድረስ እንደ አንድ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ እንዲኖሩ ተሞክሯል፡፡ ሙከራው ግን አላዋጣም፡፡ ይሄው ከንጉሱ መውረድ ጀምረው በነፍጥ ብዙ ህዝብ የጨረሱ አካላት ስልጣን ላይ ቆይተዋል፤ አሁንም ትግራይ ላይ ሆነው ግድያውን ቀጥለውበታል፡፡ በምትኩ ሰው ከማረድና ከመግደል ቦዝኖ የማያውቀው ሌላኛው ጨካኝ የኦነግ አካል ግማሹ ስልጣን ላይ ወጥቷል፤ ሌላው በጫካ ይፋለማል፡፡ የሁሉም አላማ ግልጽ ነው፡፡ በአንድ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጥላ ስር መኖር አይፈልጉም፡፡

ሁሉም ብሄር ኢትዮጵያን እስከጠቀመችው ድረስ ነው አገሬ የሚላት፡፡ ካልተመቸቸው ሊያጠፋት ይፈልጋል፡፡ አማራ ብቻ ነው ይህችን አገር ያለቅድመ ሁኔታ አገሬ ሲላት የኖረው፡፡ እንደ ጉራጌ፤ ጋሞ፣ አፋር፣ ሀድያና ከምባታ ያሉት በዚህ ይካተታሉ፡፡ ከእነዚሁም የተወሰኑቱ ኢትዮጵያን አገሬ ሲሉ በሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ አንደኛ ደረጃ ብሄራቸው ነው፡፡ አማራ ግን ከአንድ እስከ ፐ ድረስ አገሬ ሲል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ሊያበቃ ግድ ነው፡፡ ግድ ነው ግድ ነው ነው፡፡ ሌላ ንትርክ አያስፈልግም፡፡

ምክንያቱ አንድ ኢትዮጵያ የተባለ ትልቅ አገር የማቆም የአማራ ፍላጎት በገቢር የሚጨበጥ አልሆነም፡፡ ዛሬ ኦሮሞና ትግሬ የአማራን መሬት ቀምተው የየራሳቸውን አገር ሊያቆሙ ጫፍ ላይ ደርሰዋል፡፡ አማራ ግን ይሄንን ገና አላወቀም፡፡ ያወቁትም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙው ሰው አሁንም ድረስ የኢትዮጵያ ባል የኢየሩሳሌም እጮኛ የሚለውን ዜማ ያጎራጉራል፡፡ ይህ ዜመኛ የህበረተሰብ ክፍል ግን የአማራ ማህጸን በታሪክ ካፈራቸው ሰነፍ ሰዎች ዋናው ነው፡፡ በአፉ እወዳታለሁ የሚላትን ኢትዮጵያን ለማዳን ምንም ጥረት አያደርግም፡፡ የኢትዮጵያ ነገር አብቅቷል፤ በቃ ራሴን ላድን በሚሉ ጥቂት አማሮች ላይ ግን ከየተደበቀበት ጉራንጉር ሆኖ ድንጋይ ይወረውራል፡፡ ሰነፍ፤ ራስ ወዳድና ሆዳም ነው፡፡ ለራሱ ድንቁርና፣ ፍርሀትና ጥቅም የአማራን አጠቃላይ ህዝብ መያዣ አድርጎ የመስዋእት በግ ለማድረግ ይሰራል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን የዚህን ክፍል ድምጽ መስማት አያስፈልግም፡፡ ከፈለገ ከየተወሸቀበት ጉረኖ ይውጣና ኢትዮጵያን ያድን፤ ከየተወዘፈበት የምቾት ወንበሩና የሞቀ ቤቱ ይውጣና ኢትዮጵያን ያድን፤ ከሆዱና ኑሮው ቀነስ አድርጎ ኢትዮጵያን ለሚያድን ነገር ይስራ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ቁጭ ብሎ ለአማራ መጥፋት ተባባሪ ሊሆን አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ እንደ አንድ ፖለቲካዊ አገርነት አብቅታለች፡፡ ተፈጥሯዊ እድገቷን ጨርሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ አጉል ደም መፋሰስ እንጅ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ የሚቻለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ የራስን ካርታ አስምሮ አገር መካፈል፡፡ ከዚያ ወዲህ ይህንን የምታተርፈውን አገር ኢትዮጵያ በለው፡፡ ትልቁ ማድረግ የሚቻለው ይሄንን ብቻ ነው፡፡ ባለፈው የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ኢትዮጵያ ብትፈርስ የመጨረሻው ፍራሽ አማራ ላይ ነው የሚቀረው ብሎ የተናገረው አስተሳሰብ ስህተት አለበት፡፡ መሆን ያለበት ኢትዮጵያ መፍረሷ አይቀሬ ከሆነ ራሳችን አፍርሰን ትልቁን ስባሪ እንወስዳለን ነው፡፡ ትልቁም ስባሪ በታሪክ የእኛ የሆነውና የሚገባን ነው፡፡ ስለሆነም እኛ ላይ ከመፍረሷ በፊት ሰባብረናት ድርሻችን እንወስዳለን፡፡ እያንዳንዱ የየራሱን ስባሪ ወስዶ እኛ ለምንድነው መጨረሻ ላይ ትራፊ የምንወስደው? አይሆንም፡፡ ስለሆነም የአማራ ህዝብ ከዚህ በኋላ ከሌሎች መንግስታት ለመሆን ጫፍ ላይ እየደረሱ ካሉ እንደ ትግራይና ኦሮምያ ካሉ አገራት ጋር ተናጥቆ የራሱን መንግስት ለመመስረት መስራት አለበት፡፡ ምናልባት እንደ ሁለተኛ ነገር ሊያጋጥም የሚችለው እድል እነዚህ የማይታረቅ ቅራኔ ያላቸው ብሄሮች እንደ አገር ከቆሙ በኋላ የኮንፌዴሬሽን ስምምነት ሊያደርጉ ነው የሚችሉት፡፡ አማራ በዚህኛው ውል ለመግባት የራሱ የእግሩ መቆሚያ አገር ያስፈልገዋል፡፡ አለበለዚያ ግን ከፊሉ በትግራይ፤ ከፊሉ በኦሮሞ፣ ሌላውም በሌላ ኮንፌዴሬት አገሮች ተበታትኖ መቅረቱ ነው፡፡ ይህ አልገባህ ብሎ እኔ ላይ የምትጮህ ትኖራለህ፡፡ ጩህ! ይውጣልህ፡፡ እውነታውን ግን አትቀይረውም፡፡ ምናልባት ተጨማሪ አማራ አስበልተህ እንደ ኩርድ ታደርገን ይሆናል፡፡

ከላይ የተነሳውን ሀሳብ ለመፈተን እንዲህ እንመልከት፡፡ እስኪ አማራ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኖር ስንት ቀን ነው እነዚህ ቅራኔያቸው እስከመጠፋፋት የደረሱ ብሄሮች የሚፈቅዱለት? እያንዳንድህ አስበው፡፡ በአሁኑ ስርአት እንኳ ደመቀ ነበር ጠሚ መሆን የሚገባው፡፡ ገና ለገና ትግሬና ኦሮሞ አገር ያፈርሳሉ ተብሎ አብይ በህገወጥ (በራሳቸው ህግ) መንገድ ጠሚ ተደረገ፡፡ ኦሮሞም ትግሬም እስካሁን ትንሽ ጋብ ያሉት አማራ ጠሚ ባለመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ አማራ ጠሚ መሆኑ ብቻው ለዚህ አገር ቀጣይነት ስጋት ነው፡፡

ሌላውን እንይ፡፡ ዛሬ የአብን አመራር አቶ በለጠ ሞላ መተማ ላይ ጠሚ አብይ እና አቶ ገዱ በጋራ ባቀነባበሩትና በመሩት የአማራ ዘር ጭፍጨፋ ጉዳይ ላይ አንድ ቁም ነገር ተናግሯል፡፡ ይሄውም ተራ ጭፍጨፋ ሳይሆን የአማራን የመከላከል አቅም ለመፈተሸ እና በቀጣይ ሙሉ ወረራ ለማድረግ ለመዘጋጀት እንደሆነ የሚጠቁም ነው፡፡ ትክክል ነው፡፡ ስለህወሀት የጦር ዝግጅት እስካሁን በፕሮፓጋንዳ ብንሸፍነውም አሁን ለአማራ ህዝብ እውነታውን ማሳወቅ አለብን፡፡ ኢትዮጵያን የመውረር አቅም አለው፡፡ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የሰለጠነ ከመቶ ሽህ በላይ ጦር አለው፡፡ አብይ ምእራብ ወለጋን ለኦነግ አሳልፎ ከሰጠ ሰነባበተ፡፡ ኦነግ አሁን ግፊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አብይ የሚያዘው የመከላከያ ሰራዊት በተደጋጋሚ አማራ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሟል፡፡ የዘር ጭፍጨፋ ከማድረግም አልፎ ራሱ የሾመው ጀኔራል በአማራ ሞት ላይ እንዲሳለቅ አድርጓል፡፡ አብይ ከዚህም አልፎ ምንም አይነት የተጠያቂነት ስሜት እያሳየ አይደለም፡፡ ይህም የሚያመለክተው አብይ ራሱ አማራን በማጥቃት ስራ ላይ መጠመዱን ነው፡፡ ስለዚህ ነገ ከነገ ወዲያ ትግራይ ከላይ፤ ኦነግ ከታች ሆነው አማራን ያፍናሉ ማለት ነው፡፡ አብይም በኦሮሞነት ምህረት አግኝቶ (ወይም ለአገልግሎቱ ተሸልሞ) ወደአገሩ ኦሮምያ ይሄድልሀል፡፡ አቶ ገዱም ከተቀረው አማራ ጋር ሆኖ እንደ ኩርድ ቅልና ቋንቋራውን ይዞ ወይ ወደ ኦሮሞ አገር ወይ ወደትግራይ አገር ይሰደዳል፡፡ መሀል ላይ ያለውም በኢትዮጵያ አንድነት ስም አማራን የሚያጠቃው የእስስት ቡድን ከወዲሁ ራሱን ለሞጋሳነት አዘጋጅቷል፡፡

እኛ ግን ለምስኪኑ አማራ መቆምና እውነታውን ማሳወቅ ይገባናል፡፡

የነቃህ አማራ ለራስህ ነጻ መንግስት መመስረት ስራ፡፡ ያልነቃውን እርሳው፡፡ ወይ መከራ ያነቃዋል፤ ወይ በሳንጃ ወግተህ ታነቃዋለህ፤ ወይ ሳይነቃ ወደማይቀርበት ይሄዳል፡፡

ቡሌ ሆራ፤ ገንዳውሃና መተማ ላይ በዘራቸው ምክንያት የተረሸኑትን አማሮች ነፍስ ይማር!

መለክሐራ አንዱዓለም፡፡