ምን እየተካሄደ ነው?

1
1555

ምን እየተካሄደ ነው??

ሊገባኝ ያልቻለው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ተኩሶ ንፁሀን አማራወችን መግደሉ አይደለም ….ይህ ለ3 አስርት አመታት ሲደርስብን የኖረ ነው። አልገባህ ያለኝ እየተካሄደ ያለው የታቀደ ጨዋታ መሆኑ ነው። (it seems that there is some controled game).

—————————

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ትግራይ ውስጥ መሽገዋል የተባሉትን ወንጀለኞች ወደህግ ለማቅረብ ይፈልጋሉ ወይ? ይህንስ ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው ወይ? ይህን ለማድረግስ ተሞክሯል ወይ? የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ወይ? ማዘዣውን ማን ወሰደ? ማዘዣውን ማን አልቀበልም አለ? ደብረፅዮን? ይህ ሁሉ ከሆነስ መሆኑን ህዝቡ እንዴት ይወቀው?

በአማራው ደም መፅናት የሚያስብ ካለ እሱ ፈፅሞ የተሳሳተ ሀይል ነው። ሰራዊቱ ትግራይ ውስጥ መታገቱን በሰማን ቅፅበት ሰራዊቱ ሀይል እንዳለው ለማሳየት እንዲሁ አማራን መግደል ይችላል ማለት ነው?? ከድርጊቱ በላይ ይህንን ማሰብ ብቻውን ሀገር ሊያፈርስ የሚችል ሀሰብ እንደሆነ ይታወቅ? የአማራ ህዝብ ራሱን ከመከላከል አልፎ ብዙ ጀብዱ እንደሚፈፅም ዙሪያ ገቡ ያውቀዋል!

ጉዳዩን ተራና በአጋጣሚ የደረሰ ብለን አንወስደውም! ሱር ኮንስትራክሽን የተባለን የሽብር ድርጅት ለማጀብም ተፈልጎ የደረሰ ጥፋት ነው ብለን አንወስደውም። ሱርን ይጠብቅ ዘንድ የሚያዘው ህገመንግስታዊ ማእቀፍ የለም! ይልቁንም ከዚህም ወሰብሰብ ያለ በአማራው ላይ እየተቆመረ ያለና ክልሉን ወደ አጠቃላይ ሁከትና አለመረጋጋት ለመክተት ከፍ ያለ ፍላጎት እንዳለ እንገነዘባለን፤ የተባበረ ስራም እየሰራ እንደሆነ እየታዘብን ነው። ይህንንም ስንታዘብ ከህወሓት በዘለለ የሌሎች “ጠላት” ብለን ያልፈረጅናቸው ሀይሎች ጭምር እጃቸው እንዳሌለበት ማሰብ አስቸጋሪ እየሆነብን ነው። የቃላት አጠቃቃም በራሱ የሚሸከመው ስሜት አለ ….ስሜትም ፍላጎት ነው!! በዚህ ረገድ ምክትል ኢታማጆር ሹሙ ሁኔታውን የገለፁበት መንገድ አማርኛ ቋንቋን በደንብ መናገር ስለማይችሉ ብቻ የፈፀሙት የቋንቋ ግድፈት ነው ብለን አንወስድም። እንዴውም ንግግራቸው እንደ አማራ እንነቃ ዘንድ ደወል ሆኖ እናገኘዋለን።

———————

ይህ ይታወቅ….ይህችን ሀገር ለማፍረስ ብዙ ሀይሎች ጥልቅ ፍላጎት እንዳላቸው እናውቃለን፤ ሀገሪቱ እስከዛሬ ካልፈረሰች ለዚህ ዋናው ምክንያት ሌላ ሳይሆን የአማራው ህዝብ ነው። “የለውጥ ወኪል” የሚባለው የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ መንግስት መንበር ላይ ለመውጣቱ ብቻ ሳይሆን እስከዛሬ መንበር ላይ መቆየት መቻሉም በዋናነት በአማራ ህዝብ ድጋፍ እንጅ በሌላ በማንም አይደለም….ይህንንም እኛ የምናውቀውን ያህል እሳቸውም ያውቁታል!!

—————

ይህም ይታወቅ….በመሰረቱ የአማራ ህዝብ መንግስት ሳይኖር እንኳ ስርአት አክባሪ ህዝብ እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው፤ አማራዊ ውስጠ-ስሪቱ እንዲህ እንዲሆን አድርጎታልና። መንግስት ቢወድቅ እንኳ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚችል ህዝብ ነው። ይህንን እሴቱንና ዝምታውን ባልተገባ ተርጉሞ ራሱን መከላከል እንደማይችል ህዝብ ተደርጎ ከተተረጎመ ይህ ትልቅ ስህተት ነው!! ሰላም ወዳድ መሆኑንና ራሱን መግዛት የሚችል ህዝብ መሆኑን እንዲያረጋግጥ የሚጠበቀው አማራው ሳይሆን ሌላው ነው!!

—————–

ይህ በህዝባችን ላይ የደረሰው ፍፁም አረመኔአዊ ድርጊት እንዲሁም የጀኔራሉ አማርኛ የሚሰጠን ትርጉም አንድና አንድ ብቻ ነው፤ ይሄውም አማራው በዚህ ሰአት ምን ያህል ራሱን መከላከል ይችላል የሚለውን ለመመርመር የተወሰደ ነው። ይህ አይደለም ብለን ለማሰብ እንቸገራለን። አማራው ራሱን መከላከል አይችልም የሚለው ግንዛቤም ከተወሰደ ቡሀላ ይህንኑ ተከትሎ በህዝባችን ላይ አጠቃላይ ወረራ ለመፈፀም የተዘጋጁና ለዚህም ሚስጥራዊ ትብብር ያላቸው ሀይሎች መኖራቸው ዛሬ በጥርጣሬ ብቻ የምናልፈው አይደለም!!

ተፃፈ በበለጠ ሞላ ጌታሁን

1 COMMENT

Comments are closed.