ዛሬም እንደ ትናንቱ ህዝቡ ብቻውን ነው!

0
1052

እንግዲህ ይህንን ህዝብ mobilize የሚያደርገውም ሆነ direction የሚሰጠው የለም:: ድርጅቶች አሉ ግን ምንም በገጠመው ተግዳሮቶችና ክስተቶች ላይ ስልት ነድፎ የሚያታግለውና ስልት የሚያቀብለው የለም:: ህዝቡ ግን ዛሬም እንደ ትናንቱ እራሱ ይበጃል ያለውን እርምጃ እየወሰደ አመፅ በራሱ ተነሳሽነት በሸኸንዲ አድርጓል:: አዴፓ አይጠብቀውም:: አልፎም በር ዘግቶ ያስደበድበዋል:: አብንም ምንም አይልም ያለው:: አመፅ መጥራት አቅም የሌለው ድርጅት በኢትዮጵያ ናሽናል መድረክ ላይ ተወዳድሬ አሸነፋለሁ ቢለኝ ዘበት ነው የሚሆነው:: ይኼ ወርቃማ ግዜ ነው እራስን ለመፈተሽ:: የአኽንዲ መተማ ጉዳይ፥ የቡሌ ሆራ ጉዳይ፥ ከቤንሽንጉል ተፈናቃዮች ጉዳይ ወዘተረፈ ለአብን ገበያ ላይ ነገሩን ሲሸጥ ማሳያ የሚሆነውን ተጨባጭ ክስተት ሊሆን ይችሉ የነበሩ ነገሮች ላይ ባለመስራት ምክኒያትና ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ ገዢ አያገኙም:: ምርጫ በኢትዮጵያ መድረክ ላይ ማሸነፍ እንደማይቻል እየታወቀ አንገብጋቢ የህልውና ጉዳያችን በምርጫ በሚልና ጌታቸው አሰፋ በሚል አንድ ሰው ጉዳይ እየደነቆርን ህዝባችን ግን እንደቆሎ እየረገፈ ነው:: መረጃውች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከአማራ ተጋድሎና ኦሮሞ ተጋድሎ በተደረገው ጥናት የአማራ ህዝብ በእጥፍ ድርብ ከውስጥም ከውጭም ባሉ ሀሎች እንዳለቀ ያሳያል:: መሞት ላይቀር አላማ ሳይነገብ ሆነብን!

ማንም ይህንን ህዝብ ሊያገለግለው የሚፈልግ እንደሌለ ነው የምረዳው:: ስልጣን ፥ ስም ፥ ዝናን ነው ሁሉም የሚፈልገው ያሳዝናል! የአዴፓ ካድሬ ላይክ እየለቀመ አዴፓንና አብንን እያሽሞነሞነ በካድሬዎች ላይክ አብዶ sense ያለው ነገር የተናገረ ይመስለዋል አዳሜ! አብን ይሁን አዴፓ እህ ባለ ቁጥር የሚገጩ ላይኮች ክፍተን አይዘጉም! ይዋል ይደር እንጂ ህዝቤ ይባንናል!

ማቧደንና አመፅ መጥራት የትግል ሀሁን ካልቻልክ የትግል መጨረሻውን ስልጣን እያልክ ብትቋምጥ ኢትዮጵያ መድረክ ላይ ለመራመድ ትልቅ ጡንቻ ይፈልጋል! PR stunt ሁለት ወር አታዘልቅም እንግዲህ ወዲያ ጭቃ ጅራፉ እየመጣ ነውና! እንደ ጭቃ ሹም ጀጃጅ እምሩ መጡ ሲባል ለይስሙላ ሸንጎ እንደሚቀመጥ መሆን ነው:: እሳቸውም ነበሩ ይባላል ብሎ ሹመቱን ሊያፀና! የፎቶ ፖለቲካ ፎቶ ላይ ነው የሚቀረው:: አመፅ ያቀጣጠሉ ዛሬ አዲሳባ ቁጭ ብለው ሁለተኛ መንግስትነትን ውስደው ወለጋ ላይ ያፋልማሉ ሰራዊታቸውን::

“ቆይ ይጠንክር ድርጅታችን” “ቆይ ህዝብ በደንብ ይንቃ” የምትባል ማታለያም እየነጋባት ነው:: በጄሶ አንቀባውም እናጠንክር ብለን መቼም:: ነገር ግን የነቃንና የገባን ቁጥራችን አያሌ ነው:: በሰልፎች የወጣ ሁሉ የገባው ነው:: እናም የገባውን ሰው ማጠንከር፥ ማያያዝ፥ ማናበብ ነው አለቀ:: በብዙኃን ትግል የትም አገር ተደርጎ አያውቅም! ጥቂት በቆረጡ ነፃ ይወጣል እንጂ! አማራን ህዝብ ሙሉ ማንቃት የሚባል ብሄር ንቅናቄ የለም! ትግሬ እንኳን ሙላዋን አልነቃችም:: በነቁ ጥቂቶች ነው “ነፃነት”‘ያለችውን የጨፍጭስፊ ስርአት ያቆመችው:: እናም “ቆይ ህዝብ እስኪነቃ”

የምትባል ያረጀች ብሂል ትብቃን!

ህዝቡ ነቅቷል! መመሪያ የሚሰጥ፥ የሚያታግለውና የሚያናብበው አንድ አካል ነው ታጣው::

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ