ዘመን መቀየሩን ነጋሪ

0
988

አዲስ አመት አሉ በድቅድቅ ጨለማ

ፀሀይ ርቃ ልትመጣ ገና ሳታቅማማ

ዘመን ሲቀየርም ይሁን ቀናት ወራት ብሎም ሌሊት ከንጋቱ ለሁሉም የሚለይበት ለእኛም ይታወቀን ዘንድ ጠቋሚ ነጋሪ የሆነ ስርአት እንዲኖረው አድርጎ ነው አምላካችን በይሁን ቃል አለምን የፈጠረልን:: የእሱን ግዜ እናውቅ ዘንድ:: መፅሀፍ ቁዱሳዊ (scriptural calendar) ዘመን አቆጣጠር ነበረ አለምም:: የዚህች አለምን የሚገዛውም ይህንኑ ከአለም ውልደት ጀምሮ የነበረውን ሀቅ ሊያጠፋ አለምን አስተባብሮ ሆን ብሎ ይህንን አሁን ያለውን የዘመን መቁጠሪያ ግሪጎሪያ (ጎጋዊያን) ዘመንን መቁጠሪያ ብሎ በአለም ላይ ያሰራበታል ::

ከሰባቱ ፍጥረት ከተሰራበት ቀን በአራተኛው ቀን የወራት ፥ አመታት ፥ ወቅትን የምንለይና የምንቆጥርበት፤ ዘመንና የወራት ብሎም የዘመናት መቁጠሪያ መለያ የተሰጠበት ቀን ነበር::

“እግዚአብሔርም አለ፡— ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።” ዘፍጥረት 1:16

እነዚህ ታላላቅ ብርሀናት ስነፍጥረት The celestial bodies የተቋቋሙት ግዜና ወቅት ብሎም ዘመንና ዘመናትን ለማስታወቅ ነው:: The celestial bodies are elements for establishing and measuring time: ፀሀይ ቀንንና ሰአትን ስታስታውቅ፥ ጨረቃ ወቅትንና ወራትን ስታስታውቅ፥ ከዋክብት ዘመናትን አመታትን ያስታውቃሉ ማለት ነው::

እናም በዚሁ መሰረት ከጥንት ጀምሮ ያሉ ማህበረሰቦች ይህንን የዘመን መቁጠሪያ ከምድር መሰራት ጀምሮ የጠበቁ አሉ አንዱም የአማራ aka ኢትዮጵያ ዘመን መቁጠሪያ ነው:: ያው ኦሮሞ ካሌንደሩ ሌላ ነው:: ጭንብላላም እንዲሁ ለወላይቶች ነው:: እናም አማራ ተባለ ብሎ እምቡር ማለት አላዋቂነትን ማጋለጥ ነው::

ወደ ነገሩ ስንመለስ አሁን በዚህ በረዶ መካከል ፀሀይ እርቃ በመስኮቶችዋ በምትገባበትና የአዲስ ጨረቃም ውልደት በሌለበትና የከዋክብትም ምንም አይነት ምልክትን በማይሰጡበት ድቅድቅ ባለ ጨለማና አንድ ወቅት ውስጥ ከገባን ከወራት በኃላ ስለምን ፈረንጄው አዲስ አመት እንደሚለው ግራ ያጋባል:: አዲስ አመት አንድ ወቅት(season) አልቆ ፀሀይ ከራቀው መስኮቷ በቀረቡት መስኮቶችዋ እየተሽሎከሎከች ስትቀርብ፤ አበቦች በምድር ላይ ሲገለጡ፥ ወቅቱ ሲቀየር፥ ጨረቃም አዲስን ውልደት ስታገኝ፥ ከዋክብትም አንዱ ከሌላው ርቆ ሌላው ወደ አንዱ ሲጠጋና ሲወለድ ዘመን ይለወጣል:: ይሄ የፈረንጆቹ አዲስ አመት ግን እልም ባለው ጨለማ እና ምንም እንቅስቃሴ በሰማይ መስኮቶች አዲስን ነገር በማያመላክቱበት ወቅት ዝም ብለው በዘፈቀደ ይለወጣል! ይህ መፅሀፍ እንደሚል

“ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ፡ አሉ።” ይላል በሌላም ስፍራ

“አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው፡— ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር፡ አሉ። ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?” መዝሙረ ዳዊት 74:7

የሆነው ይሄ ነው የእግዚአብሄርን አውደ አመት ለመሻር ብሎም ምልክቱ እንደይታይ ለማደረግ ይህ ሁሉ ተደረገ:: በሌላም ስፍራ እንዲህ ይላል:-

“ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ። አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።” መኃልየ ማህልይ 2:10

የዘመን መለወጥ ክረምቱ ከማለፉ አበቦች መገለጡ አመላካች ናቸው እና:: ስለሆነም ምንልባት APRIL/MAY ላይ አዲስ አመታችን ቢሉ ፈረንጆቹ ትርጉም ይሰጣል እናም “እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰሽ” ስትሉኝም ዝምታዬ ከመንቃት የተነሳ ነው ልላችሁ ፈልጌ እንጂ ምኞታችሁን በምኞት ባጅበው ደስ ባለኝ ነበር::

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ