መረጃ

0
1489

12/31/18

የአብይ መንግስት አገርን ማረጋጋት እንደተሳነውና በየቀኑ ስርአት አልበኝነቱ ቅጥ እያጣ ህዝቡ በከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛል! በተለይ በተለይም አማራው!

በአዲስ አበባ በህውሀት ስርአት ውስጥ በተለያየ ሙያ ላይ የሚገኙ ጠበቆች ፋይናንስ አማካሪዎች ሚስጥር ያውቃሉ ተብለው የሚታሰቡ ግለሰቦች ሞተው መገኘት የለት ተለት ትእይንት ሆኗል ሲል የደረሰኝ መረጃ ያሳያል::

በአዲስ አበባ ከለገጣፎ አልፎ አካባቢ በሚገኝ አዲስ ሰፈር ህንፃ ሰርተው ሱቆችን ከፍተው የሚተደዳሩ አማራ ቤተሰቦች ኦሮሞ ቄሮ ጎረምሳዎች ወደ ንግድ ቤታቸው በመምጣት “ደሞዝ ቁረጡልን መሬቱ የኛ ነው” በሚል ቤተሰቡን ሲያስቸግሩ ቆይተው ምንም እንደማያገኙ ሲነገራቸው በለሊት በመምጣ የቤተሰቡን መኪና ሰባብረው ተሰወሩ:: በሌላም ግዜ ተመሳሳይ ጥያቄ እየገፋ መጣ ቤተሰቡም ወይ ፍንክች አላቸው:: አሁንም ጨለማን ተገን በማድረግ መጥተው የህንፃውን መስኮቶች ሰባብረው ተሰወሩ:: ከዚህ በኃላ የቀን ተቀን ኑሯቸው አደጋ ላይ የወደቀው የዚህ አማራ ቤተሰብ መንግስትም ምንም ሊያደርግላቸው ባለመቻሉ ለነዚህ ወጠምሻ ዱርዬ ስራ ፈቶች ደሞዝ ለመቁረጥ በመገደዳቸው አሁን ይኸው ለነዚህ ፀረ-አማሮች ቄሮ ስርአት አልባ ዱርዮዎችን አበል ይቆርጣሉ::

በተመሳሳይ ሁኔታ በለገጣፎ በሚባለው ሰፈር ነዋሪ የነበሩ ብዙ አማሮች ከስፍራው ላይ ቤቶቻቸውን እየቆለፍ ለቀው ለመውጣት በመገደዳችው ጥለው ወጥተዋል! ማታ ማታ የኦሮሞ አክራሪ ቄሮዎች ድንጋይ እየወረወሩና እያስፈራሩ ነዋሪዎቹን ስላወክዋቸው ነዋሪዎች ምን የመሳሰለ ዘመናዊ ቤቶቻቸውን በብዙ ገንዘብ ወጪ አድርገው ሰርተው ዛሬ በቤታቸው መቀመጥ አልቻሉምና ትተው ቤቶቹን ለመሰደድ ተዳርገዋል::

በደረሰኝ የውስጥ አዋቂዎች መረጃ እንዲሁ በዘፋኙ ቴዲ አፍሮ ላይም እስካሁን ሶስት ግዜ የግድያ ሙከራ በመደረጉ መኖሪያውን በመቀያየር ላይ ነው የሚል አሉባልታ አለ:: ዘፋኙ በፅንፈኛ ኦሮሞዎች ጥርስ የተነከሰበት ሰው መሆኑ ይታወቃል!

እንግዲህ አገር ጨርሶ የመበተኛውን ጎዳና ይዛ ሽምጥ እየጋለበች መሆኑን እንገንዘብ!

በአገሪቱ ላይ ዋና ዋና የሚባሉ ትልልቅ የትምህርት ተቋማት ተዘግተው እንዳሉም ማጤን ያስፈልጋል!

በተመሳሳይ ሁኔታም ከቡሌ ሆራ የተባረሩ አማራ ተማሪዎች የሞቱት ሞተው የተጠለፉ እህቶች ያሉበት የደረሱበት ሳይታወቅ የተረፉት ባህርዳር ገብተዋል! የባህርዳር ነዋሪዎች ቁርስ ምሳ እራት እያበላ ለግዝውም በስታዲየም ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል! በዚህ አጋጣሚ ጨዋው አማራ ምስጋና ይድረስህ! ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ከመስጠት ሙሉ በሙሉ ማቆሙንም ዘገባዎች ያመላክታሉ::

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ