መበታተን ጎዳና

0
1371

የአብይ መንግስት መጠናከር እንዳቃተው ለማሳየት ብዙ መዳከር ኣያስፈልገንም። በየአካባቢው እንደ ፈንዲሻ የሚፈነዳዳው ያለ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ መፈናቀሎች ማየትና ማጤኑ በቂ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በኣሁኑ ሰአት ከሶስት በላይ መንግስታት ኣሉ ብል ማጋነን አይሆንም።

የአብይ መንግስት የሚሆነው የዙማ መንግስት ነው ብዬ አብይ ወደ ስልጣን ለመምጣት ባኮበኮበ ማግስት አስነብቤአለሁ፤ አገራችንም ያለችበት ሁኔታም ይህንኑ ገላጭ ነው። መንግስት ገንዘብ እርጥባን የሚለምንበት አገር ከኤርትራ መንግስት በኃላ የኢትዮጵያው የመጀመሪያው ነው። ኤርትራስ ተገንጥላ አዲስ ጎጆ ወጪ ሆና ነው ብትለምን ብትለቀት፤ የእኛ ግን ግራ የገባው ነው።

ህውሀት የዘረፈቺውን ገንዘብ መልሶ በእጁ ማድረግ ያቃተው ደሃው የዙማ የአብይ መንግስት በአጣብቂኝ ውስጥ ይገኛል። ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ላይ ያለ ገንዘብ ተያዘ ይሚል ቀጭን ውሸት መንግስት በተቀነባበረ ሴራ ማሰራጨቱን ተያይዞታል። ጠሚዶኮ አቶ አብይ ዶላር መልሱ ብሎ በመንበረ ስልጣን ላይ ከተፈናጠጠ በኃላ ቢለምንም ምንም ምላሽ ሲያጣ ጥቁር ገበያ (black market) ቆማሪዎችን በማሰርና በማንገላታት የጀመረው ሂደትም ሳይሳካ ቀረ።ከዛም በውጪ ዳይስፕራውን ለማናገር በሚል ካቅም በላይ የሆነ በጀት መድቦ የራሱን ተክለ ማንነት ለማግነን ዙረቱ ተጀመረ። ዳያስፕራው በቀን አንድ ብር እንዲያዋጣ የሚል እጅግ አሳፋሪ መንግስታዊ አርጥባን ልመና ተለመነ ስደተኛው ኢትዮጴ። እነሶማሊያ እንኳን በዌስት ሴራ ፈርሰው ዳግም ሲሰሩ ልመና አልገቡም የነቃ ዜጋ አላቸውና። ኢትዮጴው ግን በስደት ተንከራቶ ከሰራው ላይ ቆንጥሮ አገር መስራት የሚችል የሚመስለው ነፈዝ ሆኗል። በቀን አንድ ብር አይደለም አሰር ዶላር ሰጥተን አገራችን ከገባችበት ፋይናንሺያል ውጥንቅጥ ልናወጣት አንችልም፤ በቻይና እና በምእራብ አገራት እዳ በመዘፈቋ የቀራት ብቸኛው ዐማራጭ የነ ኬንያን አይነት አጣ ነው። ኬንያ ሞንባሳ ናይሮቢ ሬልዌይ ካቅሙ በላይ ተበድሮ በሰራው ዛሬ ”The government borrowed the billions to construct the Mombasa-Nairobi standard gauge railway (SGR), against opposition that the project by China Roads and Bridges Corporation (CRBC), a Chinese State-owned company, could become a white elephant. The country’s sovereignty is now at stake.” https://afrikan-daily.com/hua-chunyingour-decision-to-take-over-mombasa-port-is-only-a-favour-kenya-owes-china-a-lot/amp/?__twitter_impression=true

አፍሪካን ዴይሊ እንዲህ አስነብቧል፤ የአገሪቱ ሉዐላዊነት ከጥያቄ መግባቱን ያሳያል፤ ይህ በኢትዮጵያም እየሆነ ያለ ሀቅ ነው። በቻይና ብድር የምሰራዋ ኢትዮጵያችን በመለስ ዜናዊ ብድር ተፈራራሚነት ብድሩን በታሰበው ሰዐትና ግዜ ለመክፈል ባትችል የተሰሩት ነገሮች፣ተቋራጭ መንገዶች ይሁኑ አገር አቋራጭ የባቡር ሀዲዶች ወደ ቻይና ይዞታነት ይቀየራሉ ማለት ነው። አዎን ከዚህ ቀደም እንዳስነበብኩት ኢትዮጵያ አገር ለመሆን የሚያችላትን መስፈርቶች አሟጣ ወደ ኮርፖሬሽንነት ተቀይራለች። ምን ማለት ነው? ኢትዮጵያ ባለቤቶች አሏት እነርሱም አበዳሪዎቿ ናቸው! ሉዐላዊነቷ በልጆችዋ አልተከበረምና ይህ ይደርስባት ዘንድ ከስልሳው ትውልድ አጉራ ዘለል ፖለቲካ ቀደምም ሲል ከንጉሱ የንግድ ፖሊሲ የውጪ ሀይሎችን እንደፈለጉ በኢትዮጵያ እንዲሰሩ ማድረግ ጀምፎ አልፎም ተቋማትን የማዘመን ተግባር ለዛሬው ምስቅል በትልቁ አዋጥቷል፤ መለስ ዜናዊ ደግሞ ይህንን ሂደት በአስራ አንድ ደብል ዲጂት አስፈንጥሮ ለዛሬው ምስቅልቅል ፍጠነቱ እንዲጨምር አድርጓል።

እናም ዛሬ ህውሀት በእጅዋ ያለውን ገንዘብ ለማውጣት ያልቻለው አብይ መንግስት ገንዘብ ኖትም የመቀየር አቅም ያለው አይመስልም፤ ካልሆነ ይህንን አጋጣሚ በቶሎ በመጠቀም ህውሀት ላይ ያለውን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማቀዛቀዝ ይቻል ነበር። ህውሀቶች የያዙትን ገንዘብ በዚህ መልክ ከጥቅም ውጭ ማድረግ ያቃተው የዓብይ መንግስት ባጋጣሚ አይመስልም፤ ነገር ግን አገራችንን በለሆሳስ አየፈትዋት ወደ ለየለት ውጥንቅጡ ወደ ጠፋው የመበታተን ጉዞ ላይ በመሆኗ ነው። እያለማመዱን ያለው ስርአት አልበኝነት አየወሰደን ያለው መንገዱ ዲሲንቲግሬሽን ይባላል።

ይልቅ መዘጋጀት ወሳኝ ነው! ከነፍጥ እና ኮንቬንሽላል ጦርነት በላይ ይህን ንቃት ህዝባችን ቶሎ ሊሰጠው ይገባል:: አገር በመፍረስ ሂደት ላይ ነች! ምንም አይነት ሴፍቲ በኢትዮጱያ የለም እንደ ዜጋም ሆነ እንደ አንደ አማራ!

የዜግነት ፖለቲካ ብለው በተለዋጭ ገብተው ይህንን ማዘናጋት ስራ እንዲሰሩ የተቀጠሩ ደግሞ ያው የአየር በአየር መርካቶ ቁጭ ይበሉዎች እነ ብርሀኑ ነጋ ናቸው!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ