በቡሌ ሆራ አማራ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በብአዴን ቸልታ ምክኒያት ተማሪዎች በከፋ ሁኔታ ውስጥ እስከሞት እየደረሰ ጥፋት እየደረሰባቸው ይገኛል!

0
1080

በቡሌ ሆራ ዪኒቨርስቲ በኦሮሞ አክራሪዎች በአማራ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞትና እንግልት ብሎም ወደ መጡበት እንዳይመለሱ በእገዳ መያዝ (hostage) የክልላቸው መስተዳደር- ብአዴን ልጆቹን ከhostage ለማስለቀቅ ምንም አይነት ጥረት ስላልተደረገላቸው ተማሪዎች በመሞት ላይ እንዳሉ እስካሁን ወደ 10 ተማሪዎች እንደሞቱና ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታና ከዶርም በመታገታቸው በሜዳ ላይ ፈስሰው ውርጭና ረሀብ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ:: አማራ ተማሪዎች ተገድለዋል፣ ሴት ተማሪዎች ተጠልፈው/ታፍነው ተወስደዋል፣ አማራ ተማሪዎች ምግብ ይከለከላሉ፣ ንብረታቸው በሙሉ ተዘርፏል ፣ የትም እንዳይወጡ ታግተዋል ። ይሄ በቀጥታ ከዚያው ከስፍራው የተገኘ መረጃ ነው።

ብአዴን/አዴፓ ዝምታን መርጧል ዛሬም! የተማሪዎች ቤተሰቦች በትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሲሆኑ የሞቱ ተማሪዎች አስከሬንም የደረሰው ቤተሰብ እንደሌለም ለማወቅ ችለናል! ያም ማለት የተማሪዎች አስከሬን በሜዳ ለአራዊት ተሰጥቷል ማለት ነው!

የጠሚዶኮ አቶ አብይ መንግስት ለሚቀጥለው የኢትዮጵያን መበትን ስራ በዋና ተዋናይነት የተመለመሉ የነ ያማማቶ ድጋፍ ያላቸው መሆኑና ወደ ስልጣንም በነዚሁ የውጭ ሀይሎች ድጋፍ ወደ ስልጣን መምጣታቸው የሚታወስ ነው:: አጀንዳ 21 በመፈፀም ያለባት ኢትዮጵያ ኦነግ የራሱን አገር ቆርጦ ድንበር እስኪያካልልና ሚሊተሪ አቅሙን እስኪያጎለብት የሚቀጥለውን አንድ አመት ከስድስት ወር አብይ ይህንን በሽፋን አንድ አገር በሚል እያታለለ የአክራሪው ኦነግን ትልም እውን ያደርጋል ማለት ነው! ከዚህ ቀደም ባስነበብኩት ፅሁፍ ትግሬ መገንጠሉን እና በአሁኑ ሰአት በራሱ መንግስት ሚሊተሪ በሁሉም ዘርፍ የተደራጀና ወደ አገርነት ለመምጣት ያለውን መስፈርት ያሟላ ሲሆን የሚቀረው የራሱን ብር ማተም ብቻ ነው:: ያም ብዙ የሚቸግር አይሆንም ጥሩ የወርቅ ሪዘርቭ አላቸውና!

አሁን አገር አልባ ሆኖ ድንበሩ ተቆራርጦ የሚወረወርለት አማራው ሲሆን አብዛኛው የአማራ ህዝብ ከብአዴን ስር አልወጣም በማለቱና ለነፃነት ሳይሆን ብአዴንን ወደ ማሻሻል የሚል የጥፋት ጎዳና ላይ መጣድ ምክኒያት ብአዴን/አዴፓ የኦሮሞንና የትግሬን ትልም ገብአት እስኪደርስ የአማራውን አይኑን በሻሽ አስሮ ይዞላቸዋል::

እንደተለመደው ሁሉ ከሆነና ምናልባትም ዳክመንተሪ ከተሰራ በኃላ ይገባው ይሆናል አማራው! ይህ ሁሉ ሲድርስ ግን ማንንም ላይ ማመኃኘት አንችልም! እራሱ የአማራው ህዝብ ድንዛዜና በይበልጥም ከማህበረሰቡ ውስጥ ትምህርት የቀሰሙት የሚባሉት ናቸው የራሳቸው ህዝብ ላይ የሚቆምሩ ያሉት! ከብአዴን ስር አንወጣም ብለው ለትርፍራፊ ስልጣን ይጠጋጋሉ እንጂ ለህዝባቸው ጥቅም አይሰሩም!

በቡሌ ሆራ የተያዙ ተማርዎች ባስቸኳይ ይለቀቁ! አማራ አክትቪስቶች ዝምታችሁን ስበሩ! ማጎብደድ አቁሙ!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ

#Bringbackourkids