ከባርነት በላይ የባሪያ አእምሮ መያዝ የከፋ ነው!

0
1066

አራት መቶ አመት እስራኤል በግብፅ ባርነት ሲገዛ በየቀኑ እየተነሱ ጡብ ሲጠበጥቡ ጭቃ ሲያቦኩ ይውላሉ:: ማታ ማታ የሆነባቸውን ያወራሉ:: ከንፈር ይመጣሉ:: አንድም ቀን ግን እንዴት ከባርነት እንደሚወጡ ስልት አይነድፉም:: ሁልግዜ ግን ያጉተመትማሉ:: አሁን እጅ እግራቸው ብቻ ሳይሆን አእምሮዋቸውም በባርነት ውስጥ ገብቷልና! በዛሬው አነጋገር ፌስቡክ ላይ ፎቶ ይለጥፋሉ:: ይነጫነጫሉ:: የመከራ ብዛት ያወራሉ:: ያወራሉ!

ሙሴ ሲወለድ የእብራዊያን ወንዶች ልጆች እንዲገደሉ አዋጅ ነበርና ሙሴን እናቱ ሲሞት አልይ ብላ በቅርጫት አድርጋ በውሀ ላይ እንዲሰፍፍ ተወችው (ናይል አባይ ወንዝ ላይ ማለት ነው እንግዴህ) እናም እናቲቱ ከሩቅ ስታይ ቆማ የልጇን ሁኔታ…..በውሀ ገንዳ እየታጠቡ ይሞላቀቁ የነበሩ የነገስታት ልጆች መሀል አንዲቱ ንግስት ቅርጫቱን ከሩቅ አይታ ወደ እሷ አስመጣች:: ቅርጫቱንም ሲከፍቱ መልከ መልካም ህፃን አይኑን ሲያቁለጨልጭ አይታ ወደደችውና ሰው ሳያይ በቶሎ ልጇ ተብሎ እንዲያድግ ስትል ልታሳድገው ወደደችና ወሰደችው:: የምታጠባ ሴትም ትፈለግ ተባል:: እናቲቱም ቀርባ እንደሞግዚት ተቀጥራ አሳደገችው:: እናም ሙሴ ያደገው የእብራዊ እናቱን ጡት በሞግዚትነት እየጠባ ነበር ነገር ግን የንግስቲቷ ማደጎ ልጅ መሆኑ ተደብቆ እንደ ልጇ በልዑል ክብርና አእምሮ ነበር እንክብካቤ የሚድረግለት የነበረው:: አእምሮው የነፃ ሰው ሆኖ አድጓል:: ምንም እንኳ ከባሪያይቱ እናት እስራኤል ቢወለድም ቅሉ:: እናቱም ዋዛ አልነበረችም አጥብቃ ስለማንነቱ ጥንቅቅ አድርጋ ትነግረው ነበር:: ዕብራዊነቱን አውቆ ታሪክ፣ ወግ፣ ስርአታቸውን ሁሉንም ጠንቅቆ፣ በወገኖቹ ላይ የሚደርስባቸው ጥቃት ቁጭት ሰንቆ፣ ቁጭቱን በከንፈር መጠጣ ባለፈ ያንገበግበው ነበር:: ማንም ግን አያውቅም! እንዴት ይህን ህዝብ ልታደግ እያለ ያስባል:: ሄዶ ስለችግራቸው ባሮቹን እንዳይነግራቸው እነሱም ማታ ማታ በኩራዝ ስር ሆነው ቂጣ እየቆረሱ የሚያወሩት ጉዳይ ነው:: ዘርፈ ብዙ ችግር ልክ እንደ ዛሬው አማራ ገጥሟቸዋል:: ወንድ ልጆቻቸውን ግብፆች በስይፍ ይቀላሉ:: ልክ አማራው በመርፌ እንደ ሚያመክኑት ሁሉ…

እናም አንድ ቀን ባደባባይ አንድ እብራዊና ግብፃዊ ሲጣሉ ድብድብ ላይ ደረሰ:: ማንነቱ በውስጥ የጠዳ ዕብራዊ ነውና በእናቱ ምክር ጉልበት፣ ደሙ ፈላ የወንድሙ መንደብደብ አይቶ:: በቀጥታ ሂዶ ግብፃዊውን አንገቱን ብሎ ገሎ አሸዋ ውስጥ ቀበረው:: የወድሙንም ደም ሳይፈስ የጠላቱን ደም አፈሰሰው! እኛና ትውልዳችን ብንሆን ኖሮ ፎቶ አንስተን ድብድቡን እንፖስትና ወደ ኑሯችን እንመለስ ነበር:: ድብድቡን ደብዳቢው “ከበባ ነው” አለ ቅብርጥስም እንላለን:: ለመመከት አንነሳም! አንድ ጥጋበኛ ወልዋሎን እንኳ ደፍሮ አንገት የሚል የለም:: ግን እንፖስታለን! ለምን ስንባል ሰው ያነቃል እንላለን:: በመደብደባችን መንቃት የሚባል ነገር አለ እንዴ ግን? ወንድምህ መደብደብ ስታዲየም አፍርሶ መሀል ሆ ብሎ ካላዳነህ ትልቅ የስነልቦና ችግር ላይ እንገኛለን::

በነጋው እንዲሁ በአደባባይ ሲመላለስ ሁለት እዕራዊያኖች ደግሞ ሲደባደቡ ደረሰ ልቡ ተሰበረና ተቆጣ:: ሊገላግል ሀይ ቢላቸው አንዱ ዕብራዊ ዘወር ብሎ “አንተ ደግሞ ግብፃዊውን እንደገደልክ እኔንም ልትገለኝ ትሻለህን?” አለው:: ሙሴ ክው አለ! ደነገጠም! ባጭር አነጋገር የሙሴን የማንነት ህልውና ትግል ያ ዕብራዊ የባሪያ አእምሮ ነበረውና ወደ የዲሞክራሲና ፍትህ ሊያደርግ ፖሰተው ማለት ነው:: እስራኤል ህልውናውን መታደግ እንጂ በግብፅ ያለ ፍትህ እና ዲሞክራሲ አይደለም ይፈልግ የነበረው:: ሙሴም አዘነ! አሁን ይህ የተሰማ እንደሆን ግብፆች እንደሚገሉት ተረድቶ ወደ በረሀ ኮበለለ:: በወንድሙ slave mentality ተጠቂነት የተነሳ እንዲሰደድ ሆነበት! አርባ አመት ከኢትዮጵያዊው በዮቶር ክህነት ትምህርትን ወሰደ:: ከአሮን በፊት የነበረ ክህነት እንደሆን የዮቶር ክህነት በዚሁ ልብ ይባል::

እስራኤል አሁንም በግብፅ ባርነት ቀንበር እየተገረፈ በፈርኦን ቀንበር ስር ይማቅቃል! የጤና ጣቢያ ሳይኖረው በወሊድ ብዙ እናቶች እየሞቱ ብሎም ትምህርት ቤቶቻቸው ነቅዘው ሳለ የፍትህ ጥያቄ እየጠየቁ እራሳቸውን ነፃ ማውጣት መሪ የሚሆናቸው የሚያደራጃቸው አጥተው አሁንም በፈር ኦን ዋይፋይ የበደላቸውን ብዛት በፎቶ ያስደግፉ ነበር:: እንደ ሙሴ አንዱን አንገት ብለው በርሀ መግባት ድፍረቱም ጠፍቶባቸው ነበርና:: ህዝብ አንዳንዴ ይደነዝዛል! በዛውም ላይ አደንዛዥ ይላክበታል ችግሩን ብቻ የሚያወራለት! ችግር ማውራት ችግርን አይቀርፍም:: ችግሩን ስር ምንድነው ብሎ መክሮ መፍትሄውን ካላመጡ ችግር ቢወራም ባይወራ የታወቀ ነው:: ችግረኛው ደግሞ ችግር እንዳለበት ያውቃል:: ያንን ችግርን ደጋግመህ ብትነግረው ሱሰኛ፣ ተበሳጭ፣ ተስፋ ቢስ ነው የሚሆነው::

ሙሴም ከአምላኩ ተማክሮና ታዞ እስራኤልን ነፃ እንዲያወጣ ወደ ግብፅ ተላከ:: አርባ አመት ስልጠና በኃላ! ሙሴ ነፃ ሊያወጣቸው እንደመጣ ለእስራኤላዊያኑ ሲነግራቸው አብዛኛዎቹ “አንተ ደግሞ ቁጡ ፣ ታገስ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን አትበል፣ ገንዘብ አሰባስብና ከመጣህበት ዳያፕራ እርዳንም የሚሉ አይጠፉም….”. እያሉ ነፃ ሊያወጣቸው እቅድ ነድፎ ከመጣው ሙሴን ልታስጨርሰን ነው ሂድልን አሉት:: በዛሬው አነጋገር “ጠላት አታብዛብን” አሉት::

ሙሴ ግን በቀጥታ ወደ ፈርኦን ያስገባው proposal “ህዝቤን ልቀቅ” የሚል ነበር:: ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ “ህዝቤን ልቀቅ” ካልሆነ በሽመል ሀይ! እስራኤሎችም የራሳቸው የሆነ ብአዴን መሰል ድርጅት ነበራቸው ጡብ ሲያንስና ለጭድ በጀት ከንጉሱ የሚጠይቅ:: እናም አንዳንዶች በዚሁ ድርጅት እስራኤልን ወክለው ስለጡብና ጭድ ማነስ፣ ቤተ ትምህርት መሰራት ወዘተ በግብፅ ባርነት ውስጥ ፍትህና ዲሚክራሲ ብለው የሚንቀሳቀሱ ገዱዎች ነበሯቸው::

የሙሴ ጥያቄ ህዝቡ መሰረታዊ ልማት የሚያደርግበት ጡብ አነሰው የሚል አልነበረም! የሙሴ ጥያቄ የጭድና ጭቃ ተገናኝቶ የሆስፒታል መሰራት የግብፅ ባርነት ውስጥ አመቻችቶ የመቀመጥ ስልት አልነበረም የነደፈው:: መሴ ህዝቡን በcollective consciousness አንድ ሀሳብ አስይዞ፣ የችግሩን አይነት እንደ ባፌ ምግብ የሰቆቃ ኤግዚቢሽን ማሳየት ሳይሆን ጥያቄው ግልጥልጥ ብሎ “ህዝቤን ልቀቅ” የሚል ነበር:: ድርድር የሌለው፣ ግን የሌለው፣ ነፃነት ብቻ ላይ የተማከለ ጥያቄ! Free my people!

ሙሴ ይዞ የመጣው ነፍጥ መጀመሪያ የግብፅን በኩር ቀርጥፎ በልቶ የግብፅን እናት በተራዋ ልጅ አልባ ያደረገና በእስራኤል ላይ ለፈፀመችው መከራ የቅጣቱ መጀመሪያ ነበር:: ቀጠለ ውሀ ወደ ደም ተለወጠ! ለጠቀ ጥይት ናዳ ወረደ በጊንጥ መልክ:: እስራኤል ግን በደም ተከለለ! ግብፆች ተደናገጡ ፈርኦን ብርክ ያዘው “ውጡልን ካገራችን ሂዱ” ብለው በልመና እስራኤል ከመካከላቸው ሳያልቁ እንዲወጣ ለመኑ:: መች እንዲህ በዋዛ! ቀጠለ ጥቃቱ ግብፆችም “ወርቅ ብር ሀብታቸውን ሁሉ አውጥተው ይኸው ያለንን ሁሉን ውሰዱ ብቻ ከመካከላችን ውጡልን ሳናልቅ ብለው ለመኑ! እስራኤልም የግብፅን ሀብት በዝብዞ አፀፋ መልሶ ካሳውን ተቀብሎ ነፃ ወጣ!! ነፃ ህዝብ!

እኛም ዛሬ ህዝቤን ልቀቅ ስንል በመሰረታዊ ልማት ጥያቄ የሚያትተው የብአዴን ክንፍና ግርፎቹ ሊረዱ የሚገባ ነገር ምንድን ነው ችግር ማውራት ሳይሆን የህልውና ትግል ችግሩን መፍታት ነው:: ነፍጥ መነሳት አለበት! ጎበዝ አለቃ በየስፍራው ውስጥ ለውስጥ በየመንደሩ ማሰለፍ፣ ወጣቱን በሚሊታንት መልክ መመልመል:: እሺ ካለ በውዴታ እምቢኝ ካለም በግዴታው ለአባት አገሩ አማራ መነሳት ግድ ይለዋል:: እናቱ ኢትዮጵያ ምንም አትሆን ብዙ ልጆች አላትና ጡቷን የሚነክሷት!

እናም አመክንዮ ያነከሰባችሁ ሆዬ አንድ ኢንጂኒየሪንግ ኮርስ የሚወስድ ሰው ኮርሱን ሲያጠናቅቅ በቀጥታ ኢንጂኒየር ይሆናል:: የሚለምነውና የሚጠይቀው ጉዳይ አይደለም ነገር ግን በሚያጠናው መስክ ላይ የቤት ስራውን በደንብ ሰርቶ ውጤቱን በእጁ በማድረግ ብቻ ማእረጉን የሚቀበለው በመብት ደረጃ በይገባኛል የሚወስደው ነው:: እንዲሁም አንድ ሰው የክህነት ትምህርት መውሰድ ከጀመረ ቄስ ልሆን “ቄስ አድርጉኝ” ብሎ የሚጠይቀው ሳይሆን የክህነቱን ትምህርት ሲያጠናቅቅ የሚወስደው ነው ይገባኛሉ ነውና! ሞኝ ባገኝ አንሁን! ፖለቲካንም እንዲሁ አንድ አካል ፕሮግራም አውጥቶ ንድፈ ሀሳቡን በህዝቡ ካሰረፀና ማደራጀትና ምሪት መስጠት ከቻለ ወደ ስልጣን እርከን ላይ ለመምጣት የሚለምነው ሳይሆን በብልጫ አይሎ የአመራሩ ስፍራ መዳረሻው ይሆናል! ተረት ተረት አናድርገው! አመክንዮን እንኳ በቅጥ ሳንረዳ ብዙዎች ፊት ፊት ላይ ለመውረር አንድክውም:: ፖለቲካ ጠንካራ ቆዳን ይፈልጋል::

እናም ሙሴ እየመራ ያወጣው ህዝብ ገና ቀይ ባህርን ተሻግሮ ብዙ ሳይርቅ ጀመረው የድሮ አመሉ:: ድርጭት ሳይሰራ ከሰማይ እየወረደለት መናን ቢመግበው አምላኩ፣ ልፋት ድካም ቢቀርለት ያ ብአዴናዊ አመሉ ምንም እንኳ አካሉ ከግብፅ ቢወጣም ያ የባርነት አስተሳሰቡ ከውስጡ አልወጣምና “መናው ሰለቸን የግብፅ ሽንኩርት ናፈቀን” እያሉ ሙሴን ያማርሩት ጀመር:: አያችሁ ከነፃነት እንኳ በኃላ ይህ የባርነት አስተሳሰብ ገና የሚያስቸግረን ጉዳይ ነው:: መልሰን ወደ ግብፅ ሁሉ አሉት::

የባርነት የተጠቂነት አስተሳሰብ እንዲህ በቀላል ከውስጥ የሚወጣ አይደለም:: ማርያምና አሮንም “እንዲያውም አንተን ማንስ በላያችን ሾመህ? በኛ ላይ የምትሰለጥንብን እንዴት ቢደረግ ነው” አሉት:: እራሱ ማኒፌስቶ ፅፎ፣ ነፃ አውጥቶ ገና ዮርዳኖስን ተሻግረው ሳይወርሱ በመንገድ ላይ ያ ብ አዴናዊ አስተሳሰብ፣ ያ በወያኔያዊው ፈርኦን slave mentality እየተንፀባረቀ ጉዞ መተጓጎል ጀመረ!

እግዚያብሄርም የሙሴን ልፋት አየና እንዳዘነም አወቀና ልክ እንደዛሬ ፌስቡከሬው ፎቶ እየለጠፈ “ይህችን ልጅ አንድ በሏት” እያለ እንደሚያላዝንብኝ የሙሴንም ፎቶ እየለጠፉ ይሰድቡት ጀምረዋልና:: ” እሱ እኔ እኔ ነው የሚለው (ያላለውን) እሱ እራሱ ወደ ላይ ሊያወጣ ነው (ባሪያ ህዝብ ምናል አንድ እንኳ ሰው ወደ ላይ ቢወጣለት ምን ገደደው ግን) እሱ እኔ ያልኩት ካልሆነ ይላል” ወዘተ እያሉ ፌስቡካቸው ሞልተው በፕስት…. ጠዋት ሲነሳ ሙሴ የሚያየው ይህንን ጉድ ነው:: ልክ ዛሬ ስነሳ ስንቶች በስድብ በፎቶዬ አስደግፈው እንደሚፈራገጡት ማለት ነው:: ከባርነት የከረፋው የባርነትን አስተሳሰብ ተሸካሚ መሆን ነው!

ስለሆነም እግዜሩም እንዲህ አለው ሙሴን “ሙሴ ባሪያዬ ሆይ ይህ ህዝብ አንገተ ደንዳና ነው:: ወደ እረፍቴ እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልኩ” ብሎት ያንን የባሪያ አስተሳሰብ ተሸካሚ ትውልድ እዛው በረሀ አራገፈውና በአስተሳሰብ የተራመደውን አዲስ ትውልድ እነ እያሱና ካሌብ ህዝቡን አሻግረው እስራኤል ያባቶቻቸውን ምድር ከኢናቅ ልጆች ከረጃጅሞቹ ተዋግተው አሸንፈው ድል ነሱ!

እንደ እያሱና ካሌብ በነፃ አእምሮ ሆነን የባሪያ አስተሳሰብ ተሸካሚነትን እምቢኝ ብለን፣ ደፋር ሆነን፣ እንነሳ!

ከባርነት በላይ የባሪያ አእምሮ መያዝ የከፋ ነው!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ