ብአዴን በአርበኞች ሳንባ ለመተንፈስ መፍጨርጨሩን ያቁም!

0
1690

ብአዴን በአርበኞች ሳንባ በመተንፈስ ህይወቱን ሊያስረዝም እየተጣጣረ ይገኛል።

የአርበኛ መሳፍንት እና የጓዶቹን ወደ ከተማ ጉሮ ወሸባዬ ተብሎ ሲገባ ስለትግሉ የድል ግብአት ለሚጨነቁ ጥያቄን ማጫሩ አልቀረም። ልንፋለመው ያለ ትልቅ ፍልሚያ ትግል ገና በፊታችን ነውና!

ብአዴን እንኳን ህዝቡን እራሱን መከላከል የማይችል ከምድር እንስሳ ሁሉ ተለይቶ እንደተረገመው እባብ በደረቱ አየተሳበ ባገኘው ዛፍ ተንጠልጥሎ ለማስካድና ሀላፊነትን ላለመወጣትና ትንሽም ብትሆን ወኔን ላለመታጠቅ ዛሬም አርነኞችን ታክኮ ለወደረኞቹ ማስፈራሪያን በማስተላለፍ ላይ ያለ ይመሰላል። ፖለቲካዊ ግልሙትና! በሰሜን አሜሪካን ቆይታው ህውሀት ጋር ለማይቀረው ፍልሚያ ዝግጁ ናችሁ ወይ ተብሎ ለተጠይቁት ጥያቄ በተደጋጋሚ ከገዱ አፍ የተነገረች አንድ ሰንካላ መልስ አለች “መግባቱን ይገቡ ይህናል ልንከለክለው አንችልም ሆኖም ግን አይወጡም” የምትል የሰነፍ የመሪ ሳይሆን የባሪያ መልስ መልሶ ብዙ ዳያስፕራ አማሮችን አማልሎባት ሄዷል። ይህንን ሊል የተገደደበት ምክኒያት “ዝግጁ ነን” ማለት አይችልምና ነው። ዝግጁነት እንዴት አይኖራቸውም ስንል ደግሞ አንደኛውና ዋነኛው እክል ወኔቢስ መሆኑ ላይ ነው። ሲለጥቅም ብአዴንን ትግሬ ጠፍጥፋ የሰራችው የአማራን መብት ለማስጠበቅ ሳይሆን አማራን ረግጣ ልትገዛበት ያሰለፈቻቸው የቤት ባሮች የበረኛነት ስራ ማስፈፀሚያ ስለሆነ ነው:: ሲቀጥልም በአገሪቱ ካሉት ክልሎች ልዩ ሀይል የሌለው ክልል በብአዴን ጠባቂ እጅ ተላልፎ የተሰጠው አማራው ክልል ብቻ ነው። በልዩ ሀይል አሰላለፋቸው የተጠናከሩ የሚባሉት አንደኛ ትግሬ ክልል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ሶማሊ ኦጋዴን ክልል ነው። ብአዴን ብቸኛው መተማመኛው ገበሬው ነው። ገበሬው ጀግና ነው ምንም ጥርጥር የሌለው ሆኖም ሜካናይዝድ የሆነ ጦር ይዞ ለሚመጣበት ግን ብዙ ደም ገብሮ ብቻ ነው በድል ሊወጣው የሚችለው። ከሚያስፈልገው በላይ ደም ገብሮ ብዙ ልጆቹን ሰውቶ ብቻ ሊቋቋመው ይችላል በቅጥ ያስታጠቀው የለምና:: የታጠቀውን ግን የሚያስፈታው ብአዴን የሚባል በረኛ አለበት::

እናም ዛሬ አርበኞችን ስፖንሰር በማድረግ በከተማ የሚያንጎማልላቸው ብአዴን በለሆሳስ መልእክትን ለነደብረጺሆን ሲልክበት ነው። ዋ ለማስፈራሪያ። ሆኖም ገበሬውም የአማራውም ህዝብ በጥቅሉ ልንረዳው የሚገባው በአኛ ትከሻ ላይ ተነጠልጥሎ ምላሱን እያወጣ “እስኪ ትነካኝና” እያለ ብአዴን እባቡ በእኛ ጫንቃ ላይ ማንጠላጠል ዋጋ ያስከፍለናል።

አርበኞች ከዚህ ብአዴን ከተባለ ቁማርተኛ ድርጅት ስር በመውጣት ለራሱ ለብአዴን እራስ ምታት መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ ብአዴን በዚህ “ይገባሉ ግን አይወጡም” የምትልን የባሪያ ስላቁን እየሰለቀ በዚያ ደግሞ አማራ ምድር ላይ መሳሪያ ሲመዘግብ ይውላል። በደንብ ካሰብንበት የመሳሪያ ምዝገባው በዚህ ሰአት ምን ይሁን ሲባል ተደረገ? አገር ሙሉውን በታጣቂ ሀይሎች በምትታመስበት በዚህ ወቅት ለምን አማራ ክልል ብቻ ወደ መሳሪያ ቆጠራ ተገባ? መልሱ ግልጽ ነው። የመሳሪያ ምዝገባው አላማው በቤት ውልዶች አማካኝነት ጠላት ስልቱን ለመንደፍ ስትራቴጂውን በሰላ መንገድ ግቡን በሚመታ መልኩ ይነድፍ ዘንድ መረጃ ነው የሚተላለፍ ያለው። “ይገባሉ ግን አይወጡም” የምትለዋ የባሪያ ስላቅም “ገቡ ማስወጣት ግን አልቻልንም” በማለት እንደተለመደው “ችግር አለብን መሻሻል እንዳለብን እናምናለን” የምትለው ዲስኩር ማሰማት ይቀጥላል ማለት ነው። ሰልጥነህ እንጂ ልትሰለጥንበት ስላጣን ላይ እንዳይወጣም ይህ ግልጽ ነው መቼም። ግን ይሄው የእኛ ማህበረሰብ ብቻ በዚህ እድር ቤታዊ ቅርጽ ባለው ፖለቲካ እየናወዘ በጣም ከተደራጁ ጠላቶቹ ጋር አብሮ ለመሄድ በማይችል መልኩ እንደ ኤሊ ብአዴንን በመከትል አዙሪት ገብቷል።

በዚያ መሀል አገር ደግሞ ያለው በአማራ እጅ ያለው መሳሪያ ቁጥር በእጁ የገባችለት ጽንፈኛ ደግሞ ደመቀ በተባለ ጋኔን ከሱዳን ምንም አይነት የመሳሪያ ልውውጥ እንዳይካሄድ የሚልን ሰነድ ይፈራረማል። ይህ ምን ያመላክታል? እየተከበብን ነው፤ እንደ ትናንትናው ከበባው ያው እኛኑ ነው። በኢትዮጵያ የተነሱ የብሄር ድርጅቶች ግብዐት አማራው መቃብር ላይ የራሳቸውን ስም በመፃፍ ላይ እንጂ ዲሞክራሲና እኩልነትን በማስፈን ላይ ያለ አይደለም።

ከላይ ለማሳየት የፈለግሁትን ገሀድ የወጣ ግን የሚያስተውለው ያጣ ሀቅ ሲጠቃለል፦

፩)አማራው ያለው የትጥቅ ልክና ብዛት ለጠላቶች በመረጃ መልክ ቀርቧል፤ በስልት ጥይት ሊያስጨርሱንና በባዶ እጅ በግላጭ ሊያገኙን ይችላሉ ማለት ነው::

፪)አማራው ትጥቅ ፍጆታውን ከሚያገኝባቸው እንደ ሱዳን ባሉ አካባቢዎች የመሳሪያ አቅራቦት እንዳያገኝ ተደርጓል፤ በቀጣይነት እራስን የማስታጠቅ ባህሉንም ሆነ እራሱን የመከላከል አቅሙን ሲያቀጭጩ ነው::

፫) አርበኞችን በከተማ በማስገባትና ግዜውን ያልዋጀ አላስፈላጊ ትሪቶችን ብአዴን በስውር እንዲቀነባበር በማድረግ የገበሬው አቅም እያስለካና አርበኞችንም እያስገመገመ ይገኛል፤

አማራ ገበሬና ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ሚሊሻን በፍጥነት እያደራጀ መሄድ ዋናው ተግባሩ መሆን ይገባዋል። አይቀሬው ፍልሚያ ገና ነውና ትሪኢቶችን በማስወገድ በዝግታና በዝምታ ሊሰራ ይገባዋል፤ የብአዴን የፖለቲካ ቁማር መቆመሪያ መሆንን አርበኞች ልብ ሊሉትና ከዚህ አይነት የፖለቲካ ደላላዎች እራሱን በማራቅ የሚሰራውን በህቡዕ ማድረግ መቀጠል ይጠበቅበታል፤ በተጨማሪም የማንም የድርጅትም መጠቀሚያ መሆንም የለበትም ትግሉ። ግልጽ የሆነ ትግሉ እና አክትቪዝሙ የተለያዪ ናቸው ሆኖም ተቀናጅተው በየራሳቸው መንገድ ይጠበጥቡ ዘንድ ይገባል።

በመጨረሻም ገዱ ሰሜን አሜሪካ መጥቶ አማራ አክቲቪስቶችን ሰብስቦ ኢቶጵያዊያኒስቶችን ሾሞላቸው መሄዱን ስንሰማ በጥርሳችን ብቻ ሳይሆን ባይናችንም ልንስቅ ተገደናል። አክቲቪስቶች ከሚታገሉለት ህዝብ ፈቅ ብለው ህዝባቸው ላይ ከተሾመ ጨቋኝ ጎን ቆመዋል ማለት አክትቪስም የሚለውም መጠሪያ አውርደው የብአዴን ካድሬንትን በመቀበል ከህዝብ ሳይሆን ከመንግስት ወግነዋል ማለት ነው፤ ግን ያው የእድር ቤት ፖለቲካ ነገረ ስራው እንደዚህ ነው። አብይ ታማኝን ቆንጮውን ይዞ ጫማ አስሞ ከግምቦት አክትቪስትነት ወደ መንግስት አሽቃባጭነት ለውጦ ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ በዚህ የአማራው አብይ ገዱ ደግሞ የአክቲቪስቶችን ቁንጮ ይዞ ብአዴን አድርጓቸው ሄዷል፤ ተጠሪነታቸው ለገዱ የሆኑ የአማራ አክቲቪስቶች ካድሬዎች እንጂ የህዝብ መብት ተሟጋቾች አይደሉም እንግዲ ወዲያ። ለማናቸውም ከይ ቀደም እንዳስታወቅሁት እኔ አክቲቬተር እንጂ አክትቪስት አይደለሁም ስለሆነ መሟገቴም ሆነ ተጠሪነቴ ለአማራው ህዝብ ብቻ ይሆናል። አገር አምሮባት ነፃነት ቢሰፍንባት እንኳ ከመንግስት ጎን የምቆምበት ግዜ አይኖርም ከህዝብ ጎን እንጂ። I am a vigilant fighter! ለገዱ አክትቬተሮች እንደሆንን የመብት ተሟጋቾቹ አድርሱለት:: ይህንን ትግል በጣሳው ውስጥ አስገብቶ ክዳን ያደረገለት መስሎት እንደሆን አትጃጃል በሉት:: ትግላችንን አጠናክረን የቤት ባሮችን ከንብለን እስክንጥል እንቀጥላለን!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ