ግን ለምን አማራው ተግባራዊ እርምጃ አይወስድም?

0
1409

ሰዎች ለምን ተግባራዊ እርምጃ አይወስዱም ( Why don’t people take action?)

                                            (ኃይለአብ በላይ ዘለቀ)                                                                                                

 

ከአማራ ትግል ጋር በተያያዘ የሚታየው ትልቁ ችግር አማራው ማድረግ ከሚገባውና ከተደቀነበት አደጋ አንጻር ተገቢውን እርምጃ በተገቢው መጠንና ፍጥነት አለመውሰዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል።

ግን ለምን አማራው ተግባራዊ እርምጃ አይወስድም?

በአንድ ወቅት አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የፊልም ምሁርና ባለሙያ “ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሞክሩ ሁሉ ይጠፋሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትጠፋም” ብሎ በሙሉ እምነትና እርግጠኝነት ተናግሮ ነበር። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች የዚህ እምነታቸው ምንጭ ምን እንደሆነ በግልጽ ማስረዳት የሚችሉ አይመስለኝም። ያለ ምንም ጥረት ነገሮች በራሳቸው ጊዜ ይስተካከላሉ ብሎ ማሰብ ግን እጅግ አደገኛ አመለካከት ነው። የቤት ስራውን ሳይሰራ፣ መጻሕፉቱን ሳያነብ፣ ፈተናዎቹን ሳያልፍ ማወቅና አዋቂ ባላሙያ ተብሎ መመረቅ የሚችል ሰው የለም።

Harvard business review በዚህ ጉዳይ ላይ ከአመታት በፊት ባስነበበው ጽሑፍ ችግሩ ሰዎች የአሁኑ ድርጊታቸው በወደፊት ሁኔታዎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ አሁን በአንገብጋቢነት ስለማይሰማቸው ነው ብሎ ነበር።  

ሌላው teachthought የተባለው ድረ-ገጽ ተማሪዎች ለምን የቤት ስራቸውን አይሰሩም ለሚለው ጥያቄ የቤት ስራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ መሆን ፤ የቤት ስራው ዋጋ ግልጽ አለመሆን ፤ የቤት ስራው ለሁሉም ተመሳሳይ መሆኑ ወዘተ የሚሉ ምክንያቶችን አንስቷል።

Titanium የተባለው ድረ-ገጽ በበኩሉ የተግባር እርምጃ የማይወስዱ ሰዎች ዋጋ ሳይከፍሉ ስኬትን ብቻ ስለሚፈልጉ ፤ በኋላ ደስታን ለማግኘት ከመሰቃየት ይልቅ የሚያተኩሩት አሁን ራሳቸውን ከስቃይ መጠበቅ ላይ በመሆኑ ፤ ደህንነት ሁልጊዜም ከፍላጎት ስለሚበልጥ ወዘተ የሚሉ ጉዳዮችን ደርድሯል።  

HUFFPOST በተመሳሳይ ርዕስ ላይ ባቀረበው ጽሑፍ ሰዎች ማግኘት የሚፈልጉትና ማድረግ ያለባቸውን ነገሮች ቢያውቁም ከፍርሃት በመነጨ ነገሮች ግን ያን ያህል የሚያጣድፉና መጥፎ አይደሉም ብለው ራሳቸውን ማሳነፍ ይመርጣሉ ። አያይዞም አንዳንዶች ሃላፊነት ከመውሰድና በራስ ተነሳሽነት ከመንቀሳቀስ ይልቅ ሌሎችን መከተል ቀላል አድርገው ይቆጥሩታል ብሏል።

Schwartz, Tony. Why Don’t We Act in Our Own Best Interest? January 31, 2012. https://hbr.org/2012/01/why- dont-we-act-in-our-own-bes.html (accessed December 19, 2018).

2 Staff, TeachThought. teachthought. June 7, 2018. https://www.teachthought.com/pedagogy/why-students-dont-do- their-homework-and-what-you-can-do-about-it (accessed December 19, 2018).

3 Titanium. n.d. https://titaniumsuccess.com/6-reasons-why-people-dont-take-action/ (accessed December 19, 2018).

4 Kleitches, Kevin. HUFFPOST. August 11, 2015. https://www.huffingtonpost.com/kevin-kleitches/why-we-dont- take-action-o_b_7971788.html (accessed December 19, 2018).

ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በባለሙያዎች የሚቀርቡ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ግን በአማራው ዘንድ የሚታዩትን ፀባዮች ለመረዳት በቂ ናቸው።

ለምሳሌ ጥቂት የማይባል አማራ አሁንም በአንድነቱ ዙሪያ መሰባሰብ የሚመርጠውና የጎላ አስተዋጾም የሚያበረክተው አዲስ የሆነውን የአማራ ብሔርተኝነትን መቀላቀል ትልቅ ኃላፊነት መውሰድ መስሎ ስለሚታየውና ስለሚያስፈራው ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ብዙዎቹም የአንድነት ኃይሎች እርሱን በግል ኃላፊ ከማድረግ ይልቅ አንት የምትችለውን ብቻ አድርግ እኛ በርሃ ወርደንም ሆነ ከየትም ከየትም ብለን ነጻነትን እናጎናጽፍሃለን ስለሚሉት እዚያ የበለጠ emotional comfort ስለሚያገኝ ይመስላል።

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንም አንተ በወር በምታዋጣው ጥቂት ብር መንግስትን በማጋለጥና እረፍት በመንሳት አጣቢቅኝ ውስጥ ከተን አስወገድነው ወዘተ ማለታቸውን መጥቀስ ይቻላል።

የአማራውን ተሳትፎ ለማጠናከር ምን ይደረግ?  

ሁላችንም በግልጽ እንደምንስማማበት በተለይ በባህር ማዶ ያለውን አማራ በሚፈለገው መጠን ከንቁ ተሳታፊነት ያገደው አጠቃላይ የአማራ ብሔርተኝነትን አስፈላጊነት የመገንዘብ ችግር አይደለም።

1. ሁልጊዜም የአማራ ጉዳዮች ሲቀርቡ እጅግ ሰፊና አጠቃላይ በሆነ መልኩ በመሆኑ ሰዎች በቀጥታ አስተዋጾ ሊያደርጉበት የሚችሉበት ዘርፍ ግልጽ አይደለም። ለምሳሌ አሁን በወሎ አካባቢ ባለው ስላለው ሁኔታ ሲገለጽ እየተፈጠሩ ያሉትን ችግሮች በዝርዝር ማቅረብና አማራው ችግሮቹን በቅደም ተከተል ወይም Piece by Piece ምን ምን ተግባራትን በመፈጸም ሊያስወግዳቸው እንደሚችል ማቅረብ።

2. ከረጅም ጊዜ ይልቅ አማራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያሳካቸው የሚገቡ ስትራቴጂካዊ ግቦችን በግልጽ ማሳወቅና እነዚያን ግቦች ለማሳካት የታቀዱ ዕቅዶችን፣ የህዝቡን ድርሻ በማያሻማ መልኩ ማሳወቅ

3. በአገር ውስጥ ትልቅ መዋቅር  የዘረጉና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ ድርጅቶች ፣ ኮሚቴዎች

( እንደ ወልቃይት ኮሚቴ ) የመሳሰሉት ሌሎች ተቀባይነት ሊያገኙ የሚገባቸውን አወቃቀሮችና ግለሰቦች በማስተዋወቅና endorse በማድረግ በየዘፉ የአማራውን ህብረተሰብ የሚያገለግሉ ኃይሎች ተደጋጋፊነት ያላቸው ብቻ እንዲሆኑ ማድረግ። ለምሳሌ በባህር ማዶ ያሉ የአማራ ሚዲያዎችን ማስተዋወቅና endorse ማድረግ። ለአማራ እውነተኛ ጥቅም የተቋቋሙ ስብስቦችና የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን endorse ማድረግ ስብስቦቹና ግለሰቦቹ በቀለሉ የሚችሉትን ህብረተሰብ mobilize በማድረግና በቅልጥፍና አማራውን እንዲጠቅሙ ያስችላቸዋል።

4. በተለይ ስህተቶች ሲሰሩና ችግሮች ሲፈጠሩ ነገሮችን በውስጥ በመያዝ ለአሉባልታና ለሌሎች ጠንቀኛ ሃሳቦች መዛመት ዕድል ከመስጠት ይልቅ ቶሎ ነገሮችን ወደ መገናኛ ብዙሃን በማምጣት ነገሮችን በእንጭጩ በህዝብ ፊት መቅጨት

5. ትልቅ ድል የትንንሽ ድሎች ድምር ውጤት በመሆኑ ከላይ የተጠቀሱት ዓይነት ተቀባይነት ያላቸው ኃይሎች ህዝቡ ያስመዘገባቸውን ድሎች በይፋ ማሳወቅና ማመስገን። የህዝቡን የራሱን ድሎች ማሳወቅና ማስመስገን በግል ለሚንቀሳቀሱ Activists ብቻ የሚተው አይደለም።