ኢትዮጵያ በተሀድሶ ላይ ወይንስ በመፍረስ ላይ?

2
3211

እንደምንከታተለው ኦነግ በ”ኦሮሚያ” በተባለው ከወረራ በፌት አማራ ምድር ላይ ትጥቅ ሳይፈታ ገብቶ ምንም እንኳን በሽፋን የሚሰሩላቸው ጠሚዶኮ “ታጥቆ የገባ ሀይል የለም” ሲሉ ያስተባበሉ ቢሆንም መረጃዎች ግን ወለጋን ሙሉ በሙሉ ኦነግ በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን ያሳያሉ:: ስለዚሁም ጉዳይ ጠሚዶኮ ወደ ወለጋ ና ቢባሉም “ብትገድሉኝስ ደግሞ መሞቱንስ ልሙት ግን ኦሮሞ on ለኦሮሞ crime ከሚሆን ትግራይ ሄጄ አጋዚ ይድፋኝ አይነት ስላቅ፥ በሞቴም ቢሆን ኦሮሞ ይተባበር” የሚል እድምታ ያለው ፅንፈኛ ኦሮሞ ብሄርተኛ ንግግርም ባሳለፍነው ሳምንት ተናግረዋል:: ንግግሩ ሌላም እድምታ አለው “‘ወለጌዎች’ ደም ታፈሳላችሁ ያላግባብ” ሲል በሌላ እድምታው ያማቸዋል! ማስተዋል ይጎድላችኃል የሚልም ሽንቆጣም አለው:: ከሁሉ በላይ ግን by all means necessary የኦሮሞ ትግል ሞቼም ተፈገምግሜም ይቀጥል ይላል! … “ታማ ነው እንጂ አልሞተችም አገሬ” እያለ አንድነቱን የሚያታልለው ሀሳዊው አንድነት መሪው!

እኛም ታመመች ነው ያልነው! በሽታዋ ደግሞ ፅኑ ነው Terminally ill ነች ነው ያልነው እናም ሞት ደግሞ አይቀሬ ነው! ከዚያ ማን ይቀራል የሚል ተሟጋች አላጣም መቼም ፈርዶብኛልና!

አዎ ኢትዮጵያ ታማለች ፈፅማ ግን አልሞተችም ገና! መዳን አላት ወይ ስንል ፀረ- አማራ ነቀርሳ በልቶ ጨርሷት ባለመድሀኒቱ ሁሉ አቅቶታል:: ምናልባት ምናልባት የአማራ መንሰራራት ትንሳኤዋን ሊያደርግ ይችል ይሆናል:: እንዴት ሲባል ጥንትም ድሮ፥ ዛሬም ነገ ኢትዮጵያ አማራ እንጂ ሌላ ሆና አታውቅም! አዎ ኢትዮጵያ አማራ ሆና ከሶማሌው ወረራ፥ ከኦሮሞው ወረራ፥ ከቱርኩ፥ ጀዝዊትሱ ሁሉ የተለያየ ዘርፈ ብዙ ወረራ ሁሉ በፊት ገና ማንም ሳይመጣብን በፊት ኢትዮጵያ ተብለን፤ ሙሴን ተከትሎ አለም ፈጣሪውን ሳያውቅ ሙሴን ቅስና ያስተማርን፥ የሙሴ ቃልኪዳን (Mosaic covenant) በፊት በኪዳነ አዳም ለጥቆም በኪዳነ መልከፄዴቅ መስዋእት ያሳረግን፥ እጣንን አንድ ለሆነው አምላክ ያጠንን፥ በዮቶር ክህነት ትምህርት ሙሴን ያጠመቅን ነን! አማራው ኢትዮጵ የነገሰባት ስያሜዋንም በዚያው ያገኘች የአማራ ስሪት ነች:- ኢትዮጵያ! ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች አልፈታ ሲላችሁ ስናይ ብዙ ልናስረዳ ሞክረን ነበር:: ግን ቅኔ ነውና አይፈታላችሁም!

ይህንን በውስጥ ታዋቂነት የሚያውቁ እነ ለገሰ (መለስ) ዜናዊ ደግሞ “አዲሲቱ ኢትዮጵያ” ብለው አማራውን ሳያስደነብሩ ቀስ ብለው አዲስ ድር ሊያደሩ እውነተኛው ኢትዮጵያዊነት ግማድ አማራው ላይ ጥቃት ፈፀሙ:: ጥፋታችን ነባርና የኢትዮጵያ የምትባል አገር ባለቤትና የህሳቤዋ አፍላቂ መሆናችን ላይ ብቻ ነው! ይኸው ነው በደላችን! ዛሬ ዛሬ አንድነት ውስጥ የሚዳክረው አማራ እራሱ ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ህሳቤና ማንነትን በኦሪጅናል ትርጉሙ አያውቀውም:: ብዙው ዘመነኛ አንድነት ነኝ ባዩ የሚያጠነጥነው ክሯ እንዲበጠስ ወደ አደረገው ከአፄ ሚኒሊክ ወዲህ ያለውን ኢትዮጵያ ህሳቤ ነው:: የአፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ እራሷ ቀዳማዊ አዲስቷ ኢትዮጵያ ነች ብል አልሳሳትም! አፄ ሚኒሊክ በአማራው ስርወ መንግስት ላይ ሲሰየሙ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር አማራነትን በማንነት (identity) ደረጃ ቢያንግቡትም ፍፁም ግን አማራ ስለሆኑ አይደለም! አፄ ሚኒሊክ የ”ተዋልደናል” ፖለትካን በስፋት በማራመድ የሁሉንም ባህልና ቋንቋ በመጠበቅ በግርድፍ አንድነትን በማምጣትና በማቻቻል አብሮ የገብረኝ ፖለትካን ነው ያካሄዱት:: ለግዜው በጣም ተራማጅ የሆነ ፖለትካዊ ስልት ነው ልንለው እንችላለን ሆኖም ግን የግድ አማራውን ጠቅሞታል ማለት ግን አይደለም! እንዲያውም በእኛ ኪሳራ ነው ሚኒሊክ ቀዳማዊ አዲሲቱን ኢትዮጵያ ያቀኗት! ያ ደግሞ ለኦሮሞውና ለህዳጣኑ እጅግ ጠቀመ እንጂ ለአማራ ኪሳራ ያለው ስልት ነበር::

ማሳሰቢያ:- ይህ ፅሁፍ በፖለትካና ታሪክ እውቀት አጉራዘለል ለሆኑና ገና ጨቅላነትን ላልተው አይደለምና ካልተስማማን ገፁን በመተው መሄድ ብልህነት ነው:: ከአዋቂነት የሚወሰድ ብልህነት!

እናም ይህች ዘማዊ እና ዘመናይ ሆና ስልክ እያስገባች ሰለጠንኩኝ ብላ በሌላ እጇ ሳታጤን የፈረንጅ ትምህርት አግበስብሳ ግጥም አድርጋ ልትግት የራሷን የትምህርት ተቋማት ባይን ቂጥ እያየች የፈንጅን ትምህርት እያስኮመክልመች እራስ ጠል ኢትዮጵያዊያንን የምታመርተው ኢትዮጵያ በአማራ ኪሳራ ላይ በዘመናዊነት ስም በፀረ- አማራ/ትክክለኛው ኢትዮጵያዊነት ላይ ትጎነጎን ጀመር:: ምኒሊክም ሰው ነበሩ! ያላጤኑት ችግርም ነበረው “ተጋብተናል ተዋልደናል” የማይፈታው የማያቀራርበው ትልቅ ችግር እያለ ምንጣፍ ማልበሱ ችግሩን አላጠፋውምና:: ዛሬ አፄው በዘር ፅዳታ በባርቤሪያኒዝም ሊታሙበት ስንት ዋጋ ከፈሉ::

እራሱ ትምህርት አቀመስኩት ባለችው ራስ ጠል አማራ ጀምሮ በአማራዊው/ኢትዮጵያዊው ህሳቤ ላይ ዘመቻ በረቀቀ ስልት ውጊያ ከፈተች::

የሚኒሊክን ቤተ መንግስት ኦሮሞዎችና ትግሬ ያጥለቀልቁት ገቡ:: ይታያችሁ ስርወ መንግስቱ አማራዊ ሆኖ ሳለ ግዛትን በማስመለስ ሰበብ የተነደፈው ”ገብረኝ” ፖለቲካ ልክ እንደዛሬይቱ ኢትዮጵያ በስም ብቻ ኢትዮጵያ እንደምትባለው ስርወ መንግስትም በስም ብቻ አማራዊ እየሆነ ሊቀጥል ሀ ብሎ ስራዬው ተጀመረ:: ሚኒሊክ ብዙ አማካሪዎቻቸው ትግሮች እንደነበሩ ስንቶች ታውቁ ይሆን:: ያው እሳቸውም እንደዛሬው አይነት የአማራ ኢ-ሳይንሳዊውን ፖለቲካ “በቀለ ገርባ ደሜ ነው” እያለ ደሙን ጅማ ላይ እንደሚጠጣው አይነት ፖለቲካ ነው ያራመዱት:: በደፈናው አንድ ነን ማለት በደፈናዊ ያስጠቃናል ዛሬ!

አዎ ብዙ ግዜ ይህ ህሳቤ አንድነትን ፈጥሮ ምናምን ይባላል:: ልክ ነው በካርታ ላይ ፈጥሯታል ነገር ግን ታች ድረስ ወርደን ስናይ ምንም አንድ ሊያደርገን የሚችል የአፄው ፖለትካ ምንም ትርክት ስላልነበረ ያው ያችን ግብሩን እየገበረ ኖረ ሁሉም ቀን እየጠበቀ:: የአፄ ሚኒሊክ አንድነት ፖለቲካ በግርድፍ ከገብረኝ ባለፈ ህሳቤ ባለማስረፁ ትልቅ ዋጋን አማራውን አስከፍሏል እያስከፈለውም ነው! አፄው ኢትዮጵያዊ አማራዉን ህሳቤ ይዘው እስከታች ወርደው ቢሆን ዛሬ አንድም ሌላ ቋንቋ በኢትዮጵያ ባልተገኘ ነበር:: አንድም ሌላ ባህል ባልተረፈም ነበር:: ሆኖም እሳቸው በግዛት ተስፋፊዎች ዘመን ግብዳ ዲሞክራሲን አምጥተው ነው ያሸከሙት:: ትልቅ ስህተት ነበር! ከባርነት አስተሳሰብ ሳይወጣ ዲሞክራሲን ለአንድ ሰው መጋት ትርፉ ምስቅል መፍጠር ነው:: ዛሬ ኦሮሞው ከማንም በላይ ሊያከብራቸው ሲገባ በነእርሱ ብሶ እኝህን ትልቅ ውለታን በአማራ ትከሻ ላይ ላደረጉላቸው ሰው ትልቅ ሀውልት መስራት ሲገባቸው፥ ጡት ቆርጧል ሲሉ ያሟቸዋል ይወነጅሏቸዋል! ያበላን እጅ መንከስ ምን ይሉታል?! አማራው ደግሞ ባላየው ባልበላው ሲሞግት ይውላል! አዙሪት!

በአማራው ኪሳራ ነው ዘማዊትና ዘመናይ ኢትዮጵያ የተሰራችው ስንል ብዙ ማመሳከሪያ ስላለን ነው:: አፄው አባጂፋርን ሰው አትሽጥ እያሉ የሰውነትን ሀሁ ከሚያስተምሩ እኮ ባህል፥ ቋንቋን፥ ወግን ሁሉ ጨፍልቆ ኢቶጵያዊ ህሳቤን መጋት ይችሉ ነበር:: ዛሬም ላይ ይሄ ሁሉ እምቧከረዮ አይተርፈንም ነበር ለእኛም!

እናም if anything አፄው በአማራው ሳይሆን ይበልጡን በኦሮሞና በህዳጣኑ ሊከበሩ ይገባ ነበር:: ካኮረፍንም እኛ አማሮቹ ነበርን ማኩረፍ የነበረብን ወደ ኃላ ተጎትተናልና! በእኛ ደንደስ ስንቱ ተወድሶበታልና! በእኛው ማእድ ልብ ልቡን አጥተናልና!

ዛሬም ይህ ጦስ መትረፉና ይበልጡንም በኃይለስላሴ የዚህን ህሳቤ በእጥፍ ድርብ ማስኬድ ስራ ኤርትራዊያኑን፥ ኦሮሞውን፥ ጉራጌውን በላያችን ብልጫ እንዲያገኙ እኛ ወደ ኃላ መገፍተራችን ታሪካዊ ሀቅ በስፋት በማመሳከር ልናቀርበው የምንችለው አይኑን ያፈጠጠ ጥርሱን ያገጠጠ እውነት ነው::

እናም ወደ ዛሬው ጉዳይ ስመልሳችሁ ዛሬ በምክር ቤት ፀደቀ የሚሉን አዋጅ ተጠሪነቱ ለጠሚዶኮ የሆነው ይህ አዋጅ ለአማራዊው ድንበር ችግር ምንም አይነት ፋይዳ የሚያስገኝ አይደለም ብዬ አምናለሁ! በብረት የተወሰደብህ ነገር በወረቀት ይመለሳል ማለት ማሞ ቂሎን መሆን ነው! ምናልባት ይህ አዋጅ እየገፋ ያለውን ኦነግን ጥያቄ ወደ ጠረጴዛ አምጥቶ ህጋዊነትን በግርግር በአማራው ርስት ላይ ለመስጠት ይሆናል የሚል ግምት አለኝ:: ያው ትግሬ ተገንጥሏል ብያለሁ በበቀደሙ ፅሁፌ ላይ ማሳያውንም አስፍሬአለሁኝ…. እናም በሞያሌ ያለው ሶማሊ ጭፍጨፋ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ሚዲያ በቂ ሽፋን ባይሰጠውም ቅሉ ችግሩ የሚያሳየን ሞያሌንም ከሶማሌ ማፅዳትና ክልሉን ወደ እራስ ለመጠቅለል የሚካሄድ annexation ነው:: በራያ፥ ወልቃይት፥ መተከልና ሸዋ በዚህ ፀደቀ በተባለ አዋጅ ይፈታል ብሎ ተስፋ ማድረግ ሞኝነት ነው::

የችግራችን ስሩ ጥልቅ ነው! የዛሬው የአማራው ትግል መመሰቃቀልና መናበብን ማምጣት ሂደቱ አዳጋች የሆነው የተሰራብን ስራዬ ዘመናትን ይሻገራልና ነው:: ስለሆነ እኛም ሊመጣ ያለውን ሀምሳ አመት ለትግል ለማዋል መሰናዳት ይጠበቅብናል!

እንዲህ በአምስት አስር አመት የሚፈታ አይደለም የኛ ትግል:: ሂደትን ይፈልግል! በሂደት ብቻ የሚፈታ ግዜ የሚጠይቅ ብሎም የማያቋርጥ ትግልን ይሻል:: እርግጠኛ ሆነን ከሀምሳ አመት በኃላ የምንፈልጋትን አገር ማግኘት ወይንም እንዲሁ እየባከኑ እየተሰደዱ እኛ ወደ ኤመሬት፥ ሱዳን፥ አውሮጳ ሌሎች ወደ አገራችን እየገቡ በባቢሎን ስር እንደወደቁ እስራኤላዊያኖች መበተን ይሆንብናል እጣ ፈንታችን! ይሰውረን እላለሁ! የተነሱብንን ተግዳሮቶች ሳንፈታ መሳሪያ ከትከሻ ማውረድ ዋጋ በእጅጉ ያስከፍለናል! ለምሳሌ በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሰው የትግሬ ማሊያ ለባሽ እርቅ በሚል ስም ወይንም ነገሩ ጋብ ስላለ ከተውነው ፍምን በቀሚስ ስር እንደማቀፍ ነው! ላንዴና ለመጨረሻ ነገራችንን እያፀዳን ልንሄድ ይገባናል!

እና በአባትህ እግር ተተካ! ለሀምሳ ካሻውም መቶ አመት እቅድ ንደፍ! እነኝህ ኦርጂናል ኢትዮጵያ ህሳቤ የማያውቁ ሆኖም በአዲሲቱ ፀረ- አማራ ኢትዮጵያዊነት አንግበው ኢትዮጵያዊነትን ሳያውቁ ብሎም ስለ ሆዳቸውና ስማቸው ሲሉ ፖለትካዊ ውስልትና ውስጥ የሚገቡ ከመሀላችን በማስወገድ ትግሉ መጠናከር አለበት! አማራዊ ካባቸውን አሰወልቀን እዛው “በተጋብተናል ተዋልደናል” ፖለትካቸው ደቡብ መኸድ ይችላሉ::

እኛ ከዚህ ኃላ በእነ አፄ ቴድሮስ፥ በነአፄ አምደፂሆን፥ በነአፄ ልብነድንግ፥ በነአፄ ሰርፀድንግ፥ በነአፄ አዲያምሰገድ ወዘተ ያለችን አማራነትን ህሳቤ ብቻ ልናነግብ ግድ ይለናል! አደራ ነውና!

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ

2 COMMENTS

  1. ሀይ ሊዲያ

    በጣም ጥሩ ፅሁፍ ነው! የኛ ችግር ስሩ ጥልቅ ነው! ይህች አገር በእኛ ሂሳብ እየናጠጠች ለእኛ ግን ጠላት ከሆነችብን ቆይቷል! እናመሰግናለን እህታችን!

  2. ምን አይነት ችግር ነው በናታችሆ ይቅርታ ባባታችሆ እንደ አማራ!!! ሳላስበው አስተሳስቤ ሆሉ ማለቴ እንደ አማራ ሳስብ በተወስነ ደርጃ ሌድያን እየሆንኩ ተቸገርኩ ወይስ copy አደረገችኝ::ይህን ለማለት የተቸገርኩት እሱ የምትጥፈው ፁሆፍ ሳይንሳዌ ማህበራዌ አማራዊ ስነ ልቡና ያለው አለም አቀፍዊ በጣም ምሆር አዘል ነው ይህን ለማለት ያስገደደኝ እንደ ልድያ ልሆን ይቅርና የእሱን lecture የምትፅፈውን እንብቡ መረዳት እንዲት ይከብዳል
    ወጣም ወረድም ምነው ምን ሆንከ እንዳትሉኝ እሱ የፃፈችውን ሳላነብ አብይንና ኦነግን ስገመግም ህውሀትን እና ?ብአዲንን( አዲፓ) ስገመግም የእኛውቹን activists አማራወችን ስገመግምና ለምን ብየ ስጠይቅ መልሱ ይከብደኛል እስኪ ብየ social media ስዘዋወር ሀሳቤን ሆሉ በልድያ ፁሆፍ ውስጥ አገኘውት አወ ከሱሰት አመት በፊት አማራነቴን እንዳውቅ ያደርገችኝ ረቤ(መምህር) ሆና አግኝቻታለሆ እ/ር አምላክ እንኩንም እንዳንች አይነት እህት ስጠኝ::አስራት ነት ጉቤነት በልባችን አይጥፈ

Comments are closed.