የአስቆርቱ ይሁዳ

2
2324

የአስቆሮቱ ይሁዳ፥ አጥቅሶ አብሮ እየበላ የሚያዋውል፥ስሞ የሚጠቁም፥ ኮሮጆ ይዞ የሚሰርቅ፥ እየተከተለ የሚከዳ፥ ደቀመዝሙር ተብሎ ከፈሪሳዊ የሚውል ዳተኛ! ያጎረሰውን እጅ የሚነክስ፥ እየተማረ ወደ እውነት የማይደርስ፥ በንፋስ የሚወሰድ ውሀ የሌለው ዳመና፥ ፍሬ የማያፈራ ሁለት ግዜ የሞተ፥

ከስሩ የተነቀለ የበጋ የደረቀ ዛፍ፥ የገዛ ነውሩን አረፋ እየሚደፈቅ፥ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀለት የሚንከራተት ኮከብ- አስቆሮቱ ይሁዳ!

የሀያው አመት ቆሞ ቀሩ የራሻ ኢኮኖሚና ሚካኤል ጎርቫቼቭ

——————————————-

ለሀያ መት በኢኮኖሚ ቆሞ ቀርነት የተቸገረችው ራሺያ ተስፋ እንደ ሰማይ በራቃት ግዜና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በምትርመሰመስበት ግዜ ላይ በድንገት ልጅ እግር የሆኑት እንደኛው እንደዛሬው አብይ አህመድ፥ ብዙ ተስፋ ተጥሎባቸው በድንገተኛ በሚመስል ሁኔታ በዋና ፀሀፊነት በኮሚኒስት ፓርቲ ላይ ተሹመው ወደ ስልጣን በመንደርደር መጡ- ሚካኤል ጎርቫቼቭ! 

ጎርቫቼቭ ምንም እንኳ ኮሚኒስት ቢሆኑም ቅሉ የራሳቸውን ሀሳብ በግል የሚያጠናጥኑ እንደሆኑ ይነገርላቸው ነበር:: ልክ እንደ አብይ ኦህዴድ ቢሆንም፥ ከኦዴድነት በፊት የህውሀት ግርፍ ቢሆኑም ግን የለውጥ ሀዋሪያ ናቸው እንደምንለው ሁሉ……..

ጭቃ ነው አፈር ነው ምን ብታላውሰው

ብረት አይላበስ አይዝግም ፈራሽ ነው

ከስሪቱ ውጭ እንዴት ይሆናል ሰው 

ጎርቫቼቭ የራሺያን የሀያ አመት የኢኮኖሚውን ስንቃር የምጣኔ ሀብት መፍትሄዎችን ሊፈቱ ሁለት መላ ባይ መፍትሄ ይዘው ብቅ አሉ:: ይኸውም Perestroika እና Glasnost በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጓሜውም የተሀድሶ (reform/restructuring) እና ግልፅነት (transparency/political openness) የሚል ሲሆን ለዚህም ተሀድሶና ግልፅነት መላ ምት አጋና ተመታ:: ራሺያውኑ ማጨብጨብ ጀመሩ! ከሀያው አመት የኢኮኖሚ ወጠምሻ ድንቃር የሚያወጣቸውን መሲህ እንዳገኙ አሰቡ:: በተሀድሶ ፈረስ የበሰበሰ ስርአታቸውን ሊያድሱ፥ በዛው በድሮው በሬ ሊያርሱ የብሬዥኔቭ መወገድ ብቻውን የችግሩን ስር ቀራፊ አድርገው በምናባዊ ጎርቫቼቭ አፈ ጮሌነት የቃላት ጋጋታ ተታለሉ ልክ እደዛሬው እንደኛው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አይነት ተስፋ ቢስ ባዶ ቃላት ተሸነገሉ:: የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውና ነገሩ……ጎርቫቼቭም አንዳንድ ነገሮችን ዞር ዞር አድርገው ማስቀማመጥ ጀመሩ:: የዛሬይቱ የኛው አገር የወያኔን መዋቅር ይዘን አንድ ሰው “ጌታቸው አሰፋ ይያዝልን” እንደምንለው ያለ ውጥንቅጥ በራሺያም ነበሩ ኮምኒስት በተባለ የሰው ልጅ እኩልነት አንጋች ውስጥ የበሰበሱ ቱጃሮች በሙስናው ጭምልቅልቅ ያሉ ነበሩና:: ጌታቸውና ግብረ አበሩ እኮ የሰሩትን ሁሉ የሰሩት አሁን ኦህዴድ፥ ብአዴን፥ኦህዴን ወዘተ የተባለን ድርጅት መስርተው በዚያውም ውስጥ ከአብይ ጀምሮ ሰዎችን አሳድገው፥ ሆድ አደረሮችን በገዛ ወንድሞቻቸው ላይ አስነስተው ነው እኩይ ተግባራቸውን የፈፀሙት:: በተለይ በተለይ ደግሞ ብአዴን የሚሉት የቤት ባሪያው የብዙ አማራ የስቃይ ሰለባ መሆን ዋናውን ሚና የተጫወተ እየተጫወተም ያለ፥ ትናንት ለህውሀት ዛሬ ለኦነግ ግልገልነት ገብቶ የአማራን እንቅስቃሴ እየመዘመዘ እንደ ምስጥ ከውስጥ በልቶ ሊጥል ሽፋን (front) እያበጀ አማራዊውን ማእበል ለማዳከም ሌት ደቀን ሽር ጉድ እያለ የማይቀዝፍበት መቅዘፊያ የለም!በዚህ ጉዳይ ስናንነፃፅረው ኦህዴድ ምንም ግርድና ውስጥ ቢሆን ኦሮሞአዊ ገረድ ነበር! እዚህ ላይ ይሰመር! በኦህዴድና ኦነግ መሀል ያለው ልዩነትም የዛው የአንዱ ሳንቲም ሌላ ገፅታ መሆን ላይ ብቻ ነው! ኦህዴድ በ”ኦሮሚያ” ላይ በራሱ ጤና ጣቢያዎች ሴቶች ልጆች አምካኝ መርፌ አላስወጋም! ብአዴን ግን አማራ ስላልሆነ በሆድ አደር የቤት ባሮች እጅ ያለ ድርጅት ስለሆነ ልጃገረዶችን በመርፌ ያስመከነ እኩይ ነው! የአስራ ሁለት አመት ልጃገረዶችን ያመከነ ድርጅት ነው! የትናንቱን በጎጃም የተደረገውን ብቻ እንዳታስቡ ዛሬ በሸዋ አማራ ልጃገረዶች ላይ የማህፀን ካንሰር መከላከያ ክትባት በሚል አሁን ይህንን እያነበባችሁ ልጆቻችንን በዚህ ዘር ፅዳት እያስቀጠፈ የሚገኘው ይሄው የቤት ውልድ የቤት ባሪያ ብአዴን ነው:: ብአዴን በስናይፐር ባህር ዳር ላይ ከመቶ በላይ እምቦቀቅላ ልጆቻችን በአንድ ጀንበር ጭጭ አድርጎ የጨረሰ ድርጅት ነው:: ከራሱ ፅህፈት ቤት ጣሪያ ላይ መሽቆ እንደቆሎ የሰው ክቡር ህይወት ሊያውም ያማራውን ደም እንደጎርፍ ያፈሰሰ የቃየልን መንገድ የሄደ የአማራዊያን ደምም ዛሬም ወደ ሰማይ እየጮኸ ይገኛል! በአንድ ጉድጓድ ከሰማኒያ በላይ ልጆችን እየገደሉ ቀብረዋል:: ዛሬም እንደትናንቱ የባርነት ግዳጁን ሲወጣ የአማራን ብሄርተኝነት ሊያዳፍን “አማራ ዘር አይቆጥርም” ይለናል የተሰጠውን ክልል በቅጥ ሳይመራ ዳያስፕራ ሊደሳኮር በየአሜሪካኑ እየዞረ በጀት እውጥቶ ቬኬሽን ሽርሽር ላይቭ ከፍቶ ይወስዳል፥ በተራበ በታረዘ ወገናችን ሂሳብ:: እዚህ ያለንበት ድረስ መጥቶ ደግሞ ያፍ ለከት ባጣ ለበጣ “ችግር አለብን” “መሻሻል አለብን” እያሉ አፌዙብን:: አማራ ተብየውም ቁጭ ብሎ ይህንን ብልግና ይሰማል፥ ይሰደብበታል! አማራ ዘር ካልቆረ ታዲያ አንተ አማራ በሚል አገርና ህዝብ ተሹመህ ስለምን ትሰራለህ? በአማራ ምድር አማራ ርእሰ መስተዳደር በሚል ደሞዙን እየበላ፥ ሰው እንደቅጠል ሲረግፍ ቃታውን የሳበ የቤት ባሪያ “ዘር አንቆጥርም” ሲል ተሰምሯል ባይሆን ትንሽ የውጭውንም አለም exposure አለው የተባለው የማህበረሰቡ ክፍል ዝም ብሎ ይህንን ስድ ቡድን ይሰማዋል:: በጩኸት እንኳን ለአፍ ገደብ ማሰጠት ያቃተው ዳያስፕራ:: “አማራ ዘር አይቆጥርም” ማለት “አማራ የለም” ከሚለው ምፀት የሚለየው ምንም ነገር የለም! እንዴት ይህንን ህዝባችን እየሰማ ቁጭ ብሎ ይሰደባል ብለን ስንጠይቅ መልሱ ፖለቲካችን ሳይንስ ስላልተላበሰ ነው:: አዎን የአማራ ፖለቲካ ሳይንሳዊ አይደለም:: የአማራ ፖለቲካ እድር ቤታዊና እቁብ ቤታዊ ነው:: ሲለውም ፀበል ፀዲቅም ይሆናል:: ልጆቹ እየተቀጠፉበትና ጠላት በምድሩ ተደራጅቶ 70 ቀበሌ አምጣ ሲለው በታቦት ይዳኛል! ወይንም ገንዘብ ይሰበሰብበታል አሊያም አዳራሽ ሞልቶ ድንኳን መስፊያ ዘዬ ይቀየስበታል:: ሰው ሲሞት ማን ጡሩንባ ይንፋ አይነት ጉዳይ ይባባልበታል:: የኢ-ሳይሳዊነታችን ማሳያውም በአዳራሽ እየሞሉና እየተሰበሰቡ ጥያቄና መልስ ከአሳሪዎቻቸውና ከአሳሳሪዎቻቸው ምላሽና መላን መጠበቁ ላይ ነው:: አማራ ሆይ ትግሬው ወያኔ የሾመላችሁን ሰዎች እናንተ ከእራሳችሁ ለማውረድ እስካልቆረጣችሁ ችግራችን መልኩን ይቀይራል እንጂ ችግሩ አይቀረፍም! አንድ ግዜ ነው አሉ ሁለት ጓደኛሞች ጠንቋይ ጋር ይሄዱና የሚሆነውን ነገር ለአንዷ ጥሩ ጥሩ ነገር ነገራት በተራ ቁጥር:: መጀመሪያ ታገቢያለሽ፥ ንግድ ትከፍቻለሽ፥ ከዛ ትወልጃለሽ ቀጣጠለላት:: ለሁለተኛዋ ደግሞ አንድ ነገር ብቻ አሁን ያሰበችው ነገር እንደማይሳካ ነገራት:: ግራ ቢገባት ለኔም ዘርዘር አድርገህ ንገረኝ እሺ ይሄኛው ጉዳይ አይሳካም ሌላው ቀጣይን ስትለው….. እ እ ለዛኛውም ጉዳይ ስኬት አላይም አላት:: እሺ ከዛስ ስትለው ከዛማ ችግሩን ትለምጂዋለሽ አላት አሉ:: አማራም ይህንን ብአዴን ችግሩን ከራሱ ላይ ካልጣለ ችግር በያይነቱ ይሆናል ምግቡ:: እግዚያብሄር ይጠብቀን ከዚህ!

መለስ ዜናዊ እነ ገዱንና ግብረ አበሩን በበረከት ሲሞን አማካኝነት ሲመለምል አጢኖ ነው:: በራሱ መቆም የማይችል ወኔ ቢስ ሆድ አደሩን መርጦ መርጦ ነው:: እንዴት እንደሚመለምሏቸው ባውቅ ደስ ባለኝ ለእኛም ለይተን ከመሀላችን ለማውጣት በረዳን ነበር:: 

The Gorbachev factor

———-///————

 ትናንት እንደተናገርኩት ዛሬም የምደግምላችሁ ተሀድሶ ሲባል ለውጥ አይጠበቅም! ተሀድሶ ሲሉህ የነበረው የገማው ያንኑ ስርአት ሽታው ከዚህ በላይ እንዳይቀረናህ ዲዮድራንት ይቀባል ማለት ነው:: ባልታጠበ ብብት ዴዮድራንት ሲጨመር ደግሞ ቅርናት አይነቱን ይለውጣል እንጂ ንፁህ ንፁህ አይሸትህም:: ያልታጠበውና ዲዮድራት የተቀባው ብብት ቅርናቱ ይበልጥ ይበልጥ ነው፥ ያጥወለውላል:: ለውጥ ይመጣል ብሎ ማንም ተስፋ አልገባልህም አንተ ግን ያው ስለጨነቀህ ልጁ የኔ ነው ብለህ ልታሳድግ እርጉዝ ማግባቱን መርጠሀል እናም አብይ የኦህዴዱ አንበል የወያኔ ጡት ልጅ በራስህ ዘይቤ “ኢትዮጵያ ፌንት አድርጋ ነው እንጂ፥ ኮማ ውስጥ ናት እንጂ እንጂ እንጂ አልሞተችም” የሚል ስላቅን ቀዝቃዛው በድኗን ተሸክመህ እያራደህ በውሸት ተስፋ በዝላይ ትሟሟቃለህ:: ግን በድኑን እስካላወረድክ ድረስ በዝላይ እየተሟሟቅህ በበድኑ ቅዝቃዜ መንዘፍዘፍህ አይቀሬ ነው:: ተሀድሶ ስትባል የነበረውን ያው በጌታቸው፥ በስብሀት ወዘተ ያንገሸገሸህን ስርአትን ማደስ ወይንም በፈረንጄው አፍ facelift መስጠት ማለት ነው::  ጠበቅ ማድረግ!  ትግሬ ፀረ-አማርነትን ወደ ኦሮሞ ፀረ- አማራነት ይቀየራል ማለት ነው ባጭር ቋንቋ! 

እናም የራሺያ ትንንሽ የንግድ ተቋማት ሬስቶራንቶች፥ እህል ገበያው ወዘተ ትንሽ ሞቅ ሞቅ አለላት:: ንግድ አውታሮች የራሳቸውንም ዋጋ ተመን መስጠትና ትርፍን ገደብ ማግኘት እንዲችሉ ንግድ አውታሮች ለጥቂት ተበረታቱ እናም ቀና ቀና ቀና ማለት የሚጀምሩ መሰሉ:: እኛ አገር ፒዛ ሀት እንደከፈቱልን በአብይ መምጣት ማግስት ለራሾቹም ሜክ ዶናልድስ ተከፈተላቸው:: ያይጥ ይሁን የድመት ስጋ የሚሸጠው የማይታወቀው ማክዶናልድስ መከፈት ከለውጥ የቆጠረ አይጠፋል ልክ እደኛ 800 ብር ፒዛ በአገሩ ላይ መሸጥ እንድገት የሚመስለው እንዳለው ሁሉ:: ያው የራበው ህዝብ መሪውን ሊያኝክ ስለሚችል ለጠኔ ማስታገሻ ትንሽ ለቀቅ ለቀቅ አለ:: ሆኖም ግን በብዙ ዋና ዋና በሚባሉ ንግድ አውታሮች ላይ የነበረው የዋጋ ቁጥጥር አለመነሳትና የትርፍ ገደብ አድማስ መከለል ተስፋ የተጣለበትን ኢኮኖሚ በጨቅላነቱ ቀጨው:: የታሰበው ለውጥ አልመጣም:: እንግዲህ ይህ ሲሆን ልብ ልንለው የሚገባ Perestroika ወይንም Restructuring በሚለው ሽፋን አንዳንድ ነገሮች መቀየራቸውን ነው:: እነዚያው ጉበኞች፥ ለራሳቸው ጥቅም የሚቆሙ ፖለቲከኛች መሀል መዟዟር ተደረገ:: እንደኛው የዛሬይቱ ኢትዮጱያ! ለውጡም አልመጣ ግልፅነትና ተሀድሶውም ሳይመጣ ልትወጣ የመሰለችው ፀሀይ ተመልሳ ጥልቅ አለች::  ወደ ለመደው ድድቅ ጨለማ ኩራዙን አብርቶ ሊቀመጥ ህዝበ ራሺያ አዘገመ:: ከፊተኛው ይልቅ ያሁኑ ስብራት ብሷልና አንገት መሬት ነካች:: እነዚህ self-serving ኮሚኒስት ፓርቲ አባላት ሌላ ተስፋ ወረወሩ ዲሞክራታይዜሽን የሚል:: ሌላ ስላቅ! የራበው ምግብ እንጂ በባዶ ሆድ አውራ ብትለው አቅሙስ ከየት ይገኛል?! 

እንዲህ ስፍገመገሙ የነበሩት ጎርቫቼቭ የማሉበትን ለውጥ ማምጣት ቢሳናቸው በዲሞክራታይዜሽንና Glasnost ወይንም openness በሚል ግልፅ ውይይቶችን በማበረታታት እንደዛሬው እንደኛው አገር ያለ ክርክሮችን በምሁራን መሀል እንዲደረጉ ያበራታቱ ገቡ:: ህዝብ በወሬ፥ በሀሳብና በቲዎሪ ተጠፈረ! ተንፍሶ የማያውቅ ህዝብ ደግሞ እድሉን ሲያገኝ አውርቶ አይጠግብም! እኛም ዛሬ የወደፊቱን እንዳናስብ፥ አገር ወዴት እየሄደች ነው እንዳንል ይህ የምናየው ለውጥ ወይስ ነውጥ ብለን እንዳንጠይቅ ብዙ የቲቪ መስኮቶ ተዘጋጅተው በዶክመንተሪና የመሳሰሉት እንደ “አዲሳባ የማናት” የሚሉ የጅሎችና ታሪክና አገር የማያውቁ የአጉራዘለል መድረኮች እየተበራከቱ እያየን ነው ያለነው!አዋቂዎች ሳይሆኑ ተምረው ያልተማሩ ወደ እውነት የማይደርሱ ሰዎች መደረክ ተከፋፍቶላቸው የህዝብ ንቃት ህሊናን እያጋሸቡ ይገኛሉ:: 

እናም ጎርቫቼቭ ያሉትን የምጣኔ ሀብት ለውጥ ማምጣት ሲሳናቸው “radical reform” ብለው ደግሞ ተሀድሶውን አክራሪ አድርገው አመጡት:: ዛሬ ዛሬ እኮ የፖለቲካችሁ አባባ ተስፋዬ ጠ/ሚ አብይ “ዋ ዲክቴር ልታደርጉኝ ነው” የሚል ለሁለተኛ ክፍል ተማሪ የማይመጥን ስላቅ ፖለቲከኞች ነን ባዮችን ሰብስቦ ነው የሚሰለቀው:: ይሄ እኮ አገራችንና ህዝቧ የደረሰበትን የንቃተ ህሊና ዝቅጠት የሚያሳየው እንጂ ሌላ አይደለም! የአምባገነን ሬሲፔ አለኝ እያለህ ነው! አንተ ታጨበጭባለህ! ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እውነት አለው ጭብጨባ ያስብዳል ይላል:: አብይንም በጭብጨባ አሳብዳችሁት አገር ላገር ጭብጨባ ኪኒኑን ፍለጋ ህፃናትን ሳይቀር መጠቀሚያ አድርጎ የፎቶ ሚኒስትርነቱን ተያይዞታል እድሜ ላሳባጁ አጨብጫቢው ህዝባችን! እሱ እንደው ለግለ ስብእና ግንባታ እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ ነው:: ለሶስት አስርታት ግን ፈርሳና አገርነቷ ቀርቶ ብዙ የምእራባዊያን የፖለቲካ ቁማር ያስተናገደች ሶማሊያ እንደገና ተሰርታ ተውተርትራ ቆማ በፖርላማዋ ጠቅላይ ሚንስትሯን መሀመድ ሙርሴልን impeach ልታደረገው እንደምትችል እያርበደበደች ከኢትዮጵያውና ኤርትራው መሪ ጋር የተዋዋለውንም ያደረገውንም ስምምነት ሚስጥራዊነት ባስቸኳይ እንዲገለጥ ብላ ሽንጧን ስትገትር ሳይ ወይ አገሬ አሰኘኝ:: ሶማሊያዊያኑ ማሰብ አላቆሙም፥ ለሰው አይስግዱም ግን በአመክንዮ ይሞግታሉ:: ታዲያ ፈርሳ ለዚህ መጠገን ሶማሌ ስትበቃ አለች የተባለች ኢትዮጱያ ሞታ ከደነዘዘች ምንድነው መኖር አያሰኝምን?! 

ጎርቫቼቭ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድን ሲቀይሱና ሲያወናብዱ ከምእራባዊያኖች በራሺያ ላይ ሲዋዋሉ እራሺያ ልትፈርስ ጀመረች! እንደኛው እንደዛሬው ሊብራል ኢኮኖሚ እሳቸውም ይህንን መሰል ቁማር ጀመሩ! ሀብታም እያካበተ ደሀም እየደከረተ ሄደ::  ራሺያ ተስፋ ወደሰማይ አምጥቃ እንደርችት ልትለኩሰው ብልጭታ ስትጠብቅ እንደኔዋ እንደዛሬዋ ኢትዮጱያ ርችቱ ሳይበራ ጨለማን መሰወሪያው አድርጎ ተውጦ ቀረ!  ጎርቫቼቭ ስልጣን ገደብንና ቅነሳን  በባለስልጣን አመራሮች ላይ አደረጉ:: ይህ ሚሊተሪውንና አዛዦችን ከአገራዊ ህላፊነት ገለል የማድረግ ስራዬ ይመስላል:: ወደፊትም ምርጫ  ብዙ ተወዳዳሪዎችን ያማከለ በሚስጥር (secretive ballot) እንዲሆን አበረታቱ:: እነዳዛሬዋ የአብይ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚውን ለማንሳት ጎርቫቼቭ ነፃ ኢኮኖሚንና በትልልቅ የንግድ አውታሮችን ወደ ግለሰብ ይዞታ ለመለወጥ እቅድ ነደፉ ይኸው እቅድ ግን ራሺያን ኢኮኖሚ ላንዴም ለመጨረሻ መቀመቅ የከተተ ነበር:: ከብሬዥኔቭ ከነበረው ምግብ እና ቁስ እቃ አቅርቦት እጦት በጎርቫቼቭ ባሰ! በነገራችን ላይ አብይ ከመጣ “ዝርፊያ ከቆመ” ኃላ የአንድ ነገር ዋጋ የቀነሰ አለን?!  የደከረተ ስራ ሲፈታ ፖለቲካ ውስጥ የገባ የዲጄዎች ፖለቲከኞችን ወደ አገር በመንግስት አበል እንደተወሰዱና ሆቴሎቻቸውና ምግባቸውን ሁሉ እንደተቀለቡ ግን ሰምተናል:: ለአብይ መንግስት ለራሱ ገፅታ ግንባታ ይህ ሁሉ የአገር ገንዘብ ሲባክን ጉዳዮን ያጤነ የለም:: ጎርቫቼቭ በዚህ በርሊን ግንብ ያፈርሳሉ ያስፈራርሳሉ እዚያ አገራቸው ግን አገር መፈራረስ ጀምራለች:: ልክ እንደኛዋ እንደዛሬው ከኤርትራ ጅቡቲ፥ ሶማሊ ታንዜኒያ እንደሚዞረውና አገርን ድንበር የለሽ ለማድረግ አገራትን እናተልቃለን ዳር ድንበርን በመሸርሸር ተብሎ እንደምንጋተው ጠቅላዪ እየዞሩ የሚፈርሙበትን ሰነድና ውል ባናቅም ቅሉ አገራችን ግን ከትናንቱ ዛሬ በባሰ ሁኔታ አገራችን ውስጥ የዘር ፍጅት፥ በየአካባቢው ግጭት እንደምናይ ሁሉ ራሺያም ሚሊተሪ ስር አትመጣስና አቅሟን የፈተነ ችግርና  ግጭቶች መበራከት ጀማመሩ:: የታሪኩን ሂደት እዚህ በዝርዝር ማስቀመጥ ግዜ ስለማይፈቅድ በግርድፍ ይህንን መሳይ ሂደት “አንድ አገር” በሚል ትርክት ሚካኤል ጎርቫቼቭ አገር እያታለሉ በዚያ በርሊን ግንብን ሲያፈርሱ በዚህ አገራቸውን የምትፈርስበት ገደል ጋር ጥደው ነበር:: ዛሬ ከኬንያ፥ ኤርትራ፥ ሶማሌ፥ ጂቡቲ ጋር ሆነን ወደቡ ግመል ማሰሪያ ከሚሆን አንድ መርከብ ከሚያስተናግድ ይልቅ አንድ ሆነን ብንጠቀምበት” እያለ አብይ እቃ እቃ ይጫወታል በአገርና በህዝብ ላይ በዚያ ግን አዋሳ ላይ ሰው ይታረድል: እዚህ ቤኒሻንጉል ላይ ሰባ ሺህ ሰው ተፈናቀለ እንባላለን:: ሰባ ሺህ ሰው እንዴት ይፈናቀላል ጃል? ሰባ ሺህ ሰው እኮ አንድ ከተማ (town) ነው:: ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ሰው ተነስ ብለህ ሞብላይዝ ለማድረግ በክክል ደረጃ ሳይሆን በፌደራል ደረጃ ያለ ሀይል ተጠቅመሀል ማለት ነው:: ለምን አስፈለገ ከገዛ መተከል ምድሩ አማራውን ማፈናቀል? ሌላው ሸፍጥ! ሚዲያን ተገን ያደረገ በcontroled oppositions መገናኛ ብዙኃን አስተባባሪነት ሲያስለምዱት የነበረ የተሰራም ያለ ሸፍጥ::

ሚዲያ ሸፍጥ (ኢስትና ኦነጋዊ ህውሀታዊ ፀረ-አማራዊ ሸፍጥ)

——————————————

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቃጂራና እነሀብታሙ በትግሬው መንግስት ስር ብዙ ያገለገሉ ናቸው ወደ ዳያስፕራ ከመላካቸው በፊት! ዋና የሀብታሙ ታርጌት አማራ ትግል ነበር ለሚያስታውስ:: የበረከት ሲሞን ቅጥረኞች ሲል አማራዊ ሰደድ እሳት በጆግ ውሀ ሊያጠፋ ሲዳዳው ተላልጦ ጥጉን ያዘ:: በዚያ ግን አላቆሙም ህዝብ ወደ ማደናገር ስራቸው ገቡ የኛን ሰደድ ወላፈን ቢያቅታቸው:: ኤርሚያስ በትግሬው ደብል ኤጀንትነት እንዲኮበልል በተደረገ ማግስት ሰተት ብሎ ኢሳት ነው የገባው:: ምን ኢሳት ያልገባ ማን አለ ዳዊት ከበደም ኢሳቴ ነበር ባንድ ወቅት! ወያኔ ጢባጢቢ የተጫወተችበት ትልቁ ልጅነቷ ወራትን ማን ይዘነጋል:: በደብል ኤጀንቱ ኤርሚያስ መጀምሪያ ያደረገው “የመለስ ልቃቂት” በሚል ያሳተመው መፅሀፍ በስስ በስሱ የኢትዮጵያ ነገር ያለቀለት ነገር ነው የሚል እድምታ ያለው ሲሆን የራሱንም የወንጀል ተባባሪነት ሳያውቅም ይሁን አውቆ ከማሳየት በላይ ፖለቲካውን በሳይንስ ለሚቃኝ ያደረገው ነገር የወያኔን አሰቃቂ ድርጊቶችን normalize በማድረግ ስነልቦናዊ ጦርነትን ነው ያካሄደው:: ኤርሚያስ ዋቃጂራ በዋናነት አዲስባን ከወያኔ ጋር ሆኖ social engineering እንደተካሄደ ሲገልፅልን አልቆላችኃል ሲለን ሲሆን እኛ ደግሞ አልቆልናል በሚል ቁጭ ብሎ የሱን ትረካ ሰሚ የማድረግ ስነልቦናን የማኮላሸት ስራን በስነልቦንችን ላይ ሲሰራ ተስተውሏል:: በመቀጠል አበክሮ የሰራበትና brainwashing ታክቲክ በመጠቀም ኢሳት ሚዲያውን በመደገፍ የሰሩት የ”ታላቋ” ትግሬን እቅድና ካርታ በስልታዊ መንገድ ማስተዋወቅ ነበር::  ልክ ግን ወያኔ ዛሬ በማሊያ ጭልጋ ላይ ጭፍጨፋዋን ስትጀምር ይህንኑ ያስተዋወቁላትን እቅድ ልተገብር ስትነሳ ኢሳት ካሜራዎቿን አጠፋፍታ media blackout treatment ለነገሩ ለግሶን ዝምታ ነው መልሴ ብሏል:: ከዚህም ቀደም በመሰል ጉዳዮች ላይ selectively ለነሱ በሚመቻቸው መንገድ ለግምቦት ዜሮ ፖርቲያቸው ትግል አየር በአየር ሲነግዱ “ዲሽቃና ዳባት” ላይ ነን የሚል በሬ ወለደ ውሸት አይናቸውን በጨው ታጥበው ሲዋሹ ሀፍረት ሳይዛቸው ነው:: ዛሬ ካርታ እያሳየ እስከ ጋምቤላ መውጫ እንዳበጁ የተረከው ይኸው የወሬ ጣቢያ ጭፍጨፋውን ህውሀት በአብይ አፍዝ አደንግዝ ሸፋኝነት ስራውን ስትጀምር አዲስ ቤተ ሰሪነቷን የወሬው ጣቢያ ካሜራውን ሌላ ማጉሊያ አስገብቶ አጥብቦ አጀንዳ የማስቀየስና የማራገብ ስራ ውስጥ ተጠምዷል:: የቤኒሻንጉል ከመቶ ሀምሳ ሺህ በላይ ሰው ባለፉት ስድስት ወራት መባረርና በጎንደር ጭልጋ ድረስ ገብቶ የማፈናቀል ስራ ብሎም በራያ የሚያሳየን ቤተ ሰሪዋ ህውሀት አገር ቆርሳ ልትሄድ ደፋ ቀና ላይ መሆኗን ነው:: አገር የፈረሰች የጆትጅ ሶሮስ ስሪቶች ደግሞ ስለአብይ ሸሚዝና ስለበረከት ሲሞን ፀጉር አቆራረጥ አይነት ወሬ ይሰልቃሉ እሹሩሩ ይሉሀል እንዳትነቃ ከእንቅልፍህ! 

ትግራይ በአሁኑ ሰአት ተገንጥላለች:: ይህንን በጡሩንባ እስኪነገርህ የምትጠብቅ ፖለቲካን በእድር ቤት ትርክት ኢሳት አይምሮህን ያበላሸ ስትሆንና “ኢትዮጵያ ፌንስት ሰርታ ነው እንጂ” የሚል የአብይን ተረት እያነበብክ የምታንኮራፋ ስትሆን ብቻ ነው:: ካልሆነማ እስኪ ወንድ ነኝ ያለ ትግራይ ይሂድና ጌታቸው አሰፋን ያውጣ? ልዐላዊት ትግራይን መድፈር ያቃተው ማእከላዊ መንግስት ማእከላዊ መንግስት ሳይሆን ጥጋዊ መንግስት አድርጋዋለች ህውሀት! 

እናም ልክ እንደዛሬዋ ትግራይ በድብቅ ባይሆንም ሉቴኒያ በግላጭ የመጀመሪያዋ ጎጆ ወጪ ጫጉላ ቤቷን ሰራች! ባይ ባይ ራሺያ ብላ ሄደች! ከተፈራረሙብትን Warsaw pact ጥላ NATOን ተቀላቀለች:: ራሺያ ፈረስ ፈረስ ማለት ጀመረች:: ራሺያ በ1955 በስምምነት በተፈረመው Warsaw Pact የራሺያን የሚሊተሪ መስፋፋትን ገደብ ያደረገ ቀድሞ የተደረገ ስምምነትን እየጣለ ሁሉም በያቅጣጫው ቤቱን እየሰራ መቆረስ ጀመረ:: 

ይህ ሁሉ ሲሆኑ ወደ አምስት አገራት የሚሆኑ እንደ ካዛኪስታን ያሉቱ አገር መፍረሷን የሰሙት ወይንም የታያቸውና የታወቃቸው ሁሉም ተገንጥሎ ሲያበቃ ነው:: አንድነት በሚል ትርክት ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩና እነ አዘርባጃን ካዛኪስታን ታዥኪስታን ኡዝበርኪስታን መጨረሻ ሁሉም ሄዶ የቀሩት የበሩ ናቸው:: ዛሬም አማራው የዚህ አይነት ጉዳይ ውስጥ ያለ ይመስላል:: ትግሬ ከአማራ በወሰደው መሬት ላይ አምቧጓሮ አንስቶ በማናለብኝነት ሲፋንን መሄጃው ስለደረሰ ነበር:: ኦሮሞው ፊንፊኔ እያለ አዲሳባን በአንድ መንደር ስሟ የራሴ ነው ብሎ አገር ይያዝልኝ ሲል ምክኒያቱ ግልፅ ነው:: መቼማንድ ሆኖ አገር ለመቀጠል ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ በአዲሳ የማናት በሚል ጉንጭ ባለፋ ነበር ግን እነሱም እንደትግሬው ይዘው ሊሄዱ ጥሎሽ ስጡን ነው ጉዳዩ! ሶማሌና ኦሮሞ አገር አንድ ብትሆን law of order በቦታው ቢሆን ሞያሌ ላይ ምን ያስጨራርሳል?! የኔ ነው የኔ ነው ድንበር ሲሰመር ነው:: 

ጎርቫቼቭ ባለብዙ ተስፋ ሰጪው የጠነከረ የህዝብ ጉምጉምታን አስመልክተው አገሪቱ ወደ ማትወጣበት ውጥንቅጣ ሳትገባ በፊት ብለው ስልጣናቸውን በውዴታ ለቀቁ:: እውነታው ግን ጎርቫቼቭና የልሲን ህዝቡን አሳውረው የራሺያን መበተን ጨርሰዋል በውስጥና ነው:: አብይም ትንሽ ቆይቶ አገር መረጋጋት አልቻለም እኔም አቃተኝ ይላል ወይን በሌላ ጉዳይ ከስልጣን ዞር ማለቱ አይቀሬ ነው :: ምክኒያቱም በአሁኑ ሰአት እንኳን ዜጎች እርሱ እራሱ እንኳ ወለጋ መሄድ ሞት ሊያመጣበት እንደሚችል ተናግሯል:: ይህ ምንን ያመላክታል? ወለጋ ውስጥ ታጣቂውና ሰውን ቁጭ ብድግ የሚያደርገው ኦነግ መሆኑ ይሰመርበትን ትግራይ ያው ግልፅ ነው ብዬ ነው! ትግራይ ላግዠሪ ላይ ትመስላለች:: ዲሞክራሲ ውገቧን እየፈታተሸችባት ይመስላል: ለኛ ተሰብስበው በአማርኛ ይደሳኮራሉ:: ለወትሮው እኛ ስናቅ ስብሰባ ሁሉ በትግርኛ ነው:: በአማርኛ የሆነ ስብሰባ ይህ ነገር ለኛ ነው ብለን እንሰማ ዘንድ ነው:: ሶማሌም ዛሬ በነበረ በተባባሰ የፀጥታ ችግር ምክኒያት ወጣቶቿን እንዲደራጁ አዝዛለች! የተሾመባቸውንም ሰው ጥበቃ አላደረግህልንምና ከዚህ ኃላ አንተን አንፈግም ብለዋል:: አብዲ ኢሌ በዚህ ጨዋታ የተበላ ይመስላል! ኦሮሞዎቹ በስልት እጃቸው አስገቡት:: የራሳቸውንም ሰው ሶማሌው ላይ ሾሙ ጎጆ ውጪ ላይ ችግር እንዳይገጥማቸው!  ኦጋዴንን ያለ መሪ ያስቀሩት ይመስላል:  

አማራ ሆይ ኢትዮጱያ በመስጠም ላይ ያለች መርከብን ትመስላለች! አሁን አብይ፥ አንድነት፥ ገለመሌ እያልክ አገር አልባ ሆነህ እንዳትቀር በቶሎ እራስህን ከምናባዊ አለም አውጣና ዝዙሪያ ገባውን ቃኘት ቃኘት አድርገው:: ይታያል ብዙ ሳታተኩር! 

አገራችን በመፍረስ ላይ ያለች አገር ነች! ልትፈርስ ነው አላልኩም! በመፍረስ ላይ ነች! 

የጂፕሲነትን እጣ እንዳይደርስብህ መሳሪያህን ቶሎ ወልውል:: በመገናኛ ብዙኃን አፍዝ አደንግዝ ዜና አትጠመድ:: እራስህ ቃኘው አገሩን ነገሩ ግልጥ ነው! 

አብይ የኛ ጎርቫቼቭ መሆኑ ነው! ምእራባዊያኑ ጎርቫቼቭን ብዙ ውዳሴ ቸረዋቸው ነበር ልክ ዛሬ ለአብይ እንደሚያደርጉት ሁሉ….. 

መሳሪያ ልመዝግብ ይላል በዚህ ሁሉ መሀል ካፖው ብአዴን! እኛ አማሮች ደግሞ ሁለት ጎርቫቼቭ ያለን ይመስላል:: 

ሰአቱ ረፍዷል! ጎበዝ አልቆች በቦታ ቦታ በውስጥ ለውስጥ ተሰለፍ ቶሎ:: እስኪነቃ እያሉ ማንኮራፋት አንድም ለመጥፋት ነው አሊያም አንገትን ጎንበስ አርጎ ለመገዛት ነው! 

እናም “አሁን ከማእዱ አምብሮኝ እጁን የሚያጠቅሰው አሳልፎ የሚሰጠኝ እርሱ ነው” አሁን እጁን እያጠለቀ ያለው አሳልፎ አገርህን የሚሰጠው ነው:: ቴሌኮም ተሸጠ ብለን እሪ እንቧ እንላለን ጦሱን ስላልተረዳን! ቶሎ ይህን እጅ ቆርጠን ካላሳጠርን እኛም በሰላሳ ሚሊየን ይሁን ቢሊየን እንሸጣለን:: 

ሊዲያ ዘ ጊዮን አማራ

2 COMMENTS

  1. ሚካኤል ጎርቫቾቭ ዘሩሲያ vs አብይ አህመድ ዘ ኢትዮጵያ
    መደራጀት ቁልፉ ነገር ሲሆን ማስተማሩና ማሳወቅም መቆለፊያው ይሆናል። እናመሠግናለን ሊዱ

Comments are closed.