ድንበር የለሹ ግብይት፥ ቪዛ የለሹ ጉብኝት

1
1322

ትልቁ ቅዠት የትግሬ ህዝብ እንዲያምነው የተደረገው ደርግን ገርስሰው ስልጣን በመጋደል እንዳገኙ እንዲያምኑ መደረጋቸው ነው:: ስልጣን በውጭ ሀይሎች ተሰጥቶዋቸው እንደተቆናጠጡትና ሰጪው በቃ ሲል ስልጣን ላይ ለመቆየት ለአንድ ቀን ምንም አይነት ሀይል ብቃት እንደሌላቸው የሚያወቁ አይመስልም::

እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በዚህ ቅዠት ዋዣቂ ብዙኃኑም ጭምር ይህንን የተረዳና የተገነዘበ አይመስልም:: ስልጣን በውጭ ሀይሎች ድጋፍ መከዳ ካደረገ ዘመን የለውም::

ሀይለስላሴ በእንግሊዝ ምርኩዝ፥ ደርግ በራሻያ መከዳነት፥ ወያኔ በአሜሪካን ከዘራነት ስልጣን ላይ እንደቆዩ ማወቅ እየተካኃደ ያለውን የሰሞኑን ድራማ ለመከታተልና ጉዞ ወዴት እያመራ እንዳለ ለመረዳት ይበጀናል::

አሜሪካኖች ጵወዛ ላይ ናቸው:: በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ እንዲህ አይነት በፍጥነት ተለዋዋጭ ነገሮች ሲበዙ በስልጣን ግርግር በ60ዎቹ ብሎም በ83 እንደሆነው ሁሉ ዛሬም ዋና የሆኑና የአገራችንን የወደፊት ጉዞ አቅጣጫ ቀያሽና ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ይከናወናሉ:: አሁን አብይን በአክተርነት አወዛዋዡ የውጪው የማይታዩ እጆች የከፋው ለመጨረሻው መጨረሻ እያሰናዳን ያለ ነው፤ ይሄውም ኢትዮጵያን denationalize የማድረግ ሂደት privatisation በሚል ስልት ታክኮ መጥቷል::

ካፒታሊስት አይደለም፥ ሊብራል ኢኮኖሚም አይደለም፥ ሶሻሊዝምም አይደለም፥ ናሽናሊዝምም አይደለም፥ ፌደራሊዝምም አይሆንም …. ይህ ወገኖች ግሎባሊዝም ነው:: ድንበር የለሹ ግብይት፥ ቪዛ የለሹ ጉብኝት፥ ገንዘብ በአብላጫ ለያዘ ብቻ የሚከፈት በር ይሆናል:: ዲናሩን ካሳየ ናይጄሪያ ዋና ዋና ንግድ አውታሮችን እንደ real State ያሉትን ይቆጣጠራል አገርህ ላይ:: አንተ ቺስታው (በንፅፅር ነው ይህንን ስል:: ለምሳሌ የዲ ኤች ገዳ ባለቤት የነበሩ ባንድ ወቅት በምንም መልኩ በንግድ ዘርፍ ውስጥ ከነአልሙዲንና ህውሀታዊያን መፎካከር ስያቅታቸው “ድሀ እዚህች አገር ላይ እንዴት ነው የሚኖረው” እንዳሉት ያለ ችስትነት ነው የማወራው፤ ገንዘብ ያለው ችስትነት፥ ወደ ገንዘብ የለሽ ሊያሽቆለቁል ቁልቁል የተጣደ ቺስትነት) እናም real stateቱ ሲጠናቀቅ ለፈለገውና ጫን ያለ ረብጣ ላሳየው ይሰጣል:: ያ ደግሞ ጋናዊ ወይንም አረብ ይሆን ይሆናል:: እንደነኒዮርክ “አዲሶቹ ከተሞች” አዲሳባ ገንዘብ ለያዘ የግዜው ሰው/ሮቦት የማንም መናኸሪያ ትሆናለች ማለት ነው:: ሲለጥቅም ኢትይዮጵያ! አንተ ኑሮው እንደ ጣፊያ ስጋ ሙቀቱ ኩምትር ሲያደርግህ ለቀህ ርቀህ ከከተማ ጎጆ ትቀልሳለህ ሪል ስቴቱና መንገዱ በመስፋት መስፋፋት ወዳለህበት እስኪደርስ:: የዶሮ እንቅልፍ ይሆናል እንቅልፍ:: ያለቪዛ ሰርቆም ይሁን ገሎ ብር የያዘ ከተማህን ለመጎብኘት ይመጣል:: ይህ ምን ማለት ነው? ሲብራራ እነሲንጋፖርን በsex destination እናስከነዳለን ማለት ነው:: ያገርህ ሴት ልጅ ባይን ቂጥ ታይሀለች ያኔ:: ድቅልቅሎች የወደፊቷ ”cosmopolitan” አዲስ አበቤዎች ልጆች ይሆናሉ ያኔ ጉሮ ወሸባዬህ ወደ ጓሮ መዋያዬ ይሆናል የአገርህ ዜማ!

ዛሬ ምንም ባልተለወጠ ለውጥ ሰልፍ መሰለፍ ስለቻልክና አለአግባብ የታሰሩ ሰዎች ስለተፈቱ ይህንን ከለውጥ ቆጥረህ ልደመር ያልክ ካልኩሌሽን ማሽኑ በደንብ ሊደምርህ ተዘጋጅቷል:: አንተ በዜሮ ቁጥርነት ብቻ ነው የምታገለግለው subservient ሞድ ላይ ተለውጠህ you’ll function at a servitude level, nothing more nothing less.

አንተ የምትተኛ ንቃ! አለም አንድ መንደር ነች እያልክ ስትለፍፍ የቆጡን ልታወርድ ስትንጠራራ የብብትህ እንዳያመልጥህ! ንቃና ይህንን አለም ባንድ እንዝርት ለማሾር ለሚመጣው ስርአት እንቅፋት አቁም! እንቅፋት ሁን! “የእንቅፋት ድንጋይን በፂሆን አኖራለሁ” እንደሚል ቃሉ ማስቆም ባትችል እንኳ እንቅፋት ሁንበት- እምብየው በል!

1 COMMENT

Comments are closed.