የኦሮሞ ኢሊቶች ትግል ከወያኔ ስር መቼም አይወጣም!

0
1017

ኦነግ ትግላቸው ጥያቄው የሚያጠናጥንበት አጀንዳ ግቡን ስናይ ባቋራጭ ወደ አገር ባለቤትነት መምጣት ነው:: ይህን ከዚህ ቀደም በሰፊው አትቼበታለሁ:: ባንዲራ፥ ካርታ፥ አዲሳባ ኬኛ”፥ በሚል ታጅቦ በየቦታው የቂም ሀውልት በማቆም ተደርቦ አማራን ሲከስ ሊኖርና ልክ እንደ ትህነግ (ህውሀት) አማራን በማጥፋት ወይንም በአማራ መርቃብር ላይ ቤታቸውን ሊሰሩ የተማማሉ ናቸው::

እናም አማራ በህልውና ትግሉን ጀምሮ በስር ነቀል ለውጥ ብቻ ትግሉን ሊደመድም በተነሳበት በዚህ ወቅት ብዙ ታዝበናል:: በሶስት አመት ግዜ ከሀምሳ አመት ትግላ ጋር ትግላችሁ እኩል በማወዳደር ለምን ትግላችሁ አልተናበበም፥ በእኩል ፍጥነት ለምን አልተጓዘም እየተባለ በሀሳዊ አንድነቱ ቡድኖች፥ በሚዲያዎቻቸው፥ በየድህረ ገፆቻቸው ብንታማም ዳሩ የትግላችን መነሻም ሆነ መዳረሻ አይታጣቸውም::

አማራ የሚታገለው አዲስ ባንዲራ ሊተክልና እሱን ሊያለማምድ ወይን ደግሞ ጥንጥዬ አገር ስምን ማስተዋወቅ ስራ ላይ አይደለም ያለው:: የኮራ የደራ ማንነት፥ ታሪክ፥ ግዛት አለንና! ስለሆነም አማራ ማንነቱን፥ ታሪኩን፥ ዳርድንበሩን ያስከብር ዘንድ ነው የሚታገለው:: አዲስ የምንሰራው ማንነት ሳይሆን ዝንት አለም የኖረን ማንነታችንን የማስቀጠል ያባቶች አደራን ግዳጅ ለመወጣት ነው የተነሳነው!

እና ግቡ “ኦሮሚያ” የምትባል ጢቢኛ አገርን ለመገንባት የተነሳው ኦሮሙማ ትግል አዲሱን ማንነቷን ለማስረፅና ለማላመድ መድረኮችን አዘጋጅተው በነጋ ጠባ ይህንን ይደሰኩራሉ::

አገር፥ ባንዲራ፥ ቋንቋ ላቲን ፊደልን ባስደገፈ ጉዞውን አስጀምረውታል:: አማርኛን በመፋቅ ላቲን ሊያቆሙ፥ ኢትዮጵያን በማፍረስ ኦሮሚያን ሊገነቡ ነውና ጥንስሱ ከጥንት ጠዋት በዚህ ባሳለፍነው ሁለት ወር እንኳ አማርኛ በድንገት ትክክል ሳይፃፍ አገኝተን (የማይመስል ነገር ለሚስት አትንገርን ረስተው) ነው በሚል የውሸት ሰበብ ታፔላ ሲያወርዱ አይተናል:: “አባን ቢያ ኦሮሞዳ” ሲተረጎም “የአገሩ ባለቤት ኦሮሞ ነው” የሚል ፍከራ “አዲስ አበባ ኬኛ” አዲስ አበባ የኛ ናት የሚል ምፀት ብሎም “ኦሮሞ ልዩ ጥቅም” በሚል ብዙ ትግል ላይ ጋሬጣ እየጣሉ ትህነግ (ህውሀት) ትንፋሽ ሲያጥራት እየመጡ CPR እየሰጡ ነፍሷን ስንት ግዜ መለሱላት::

አማራ ተጋድሎ ስፋፋምና አገረ አማራ የጦር ቀጠና በሆነበት ግዜም ኦሮሞ ፕሮቴስት ፈፅሞ ሙሉ በሙሉ አቆመ:: ለምንአማራን ብቻውን ትተውት? ግልፅ ነው አማራው በብረት ይዞታልና ብረቱን ይዞ ወደ ስልጣን ሊመዘዝ ነው ተብሎ በዝግ ተመክሮ አማራውን ማገዝይሆናል በሚል ስልታዊ ማፈግፈግ ማድረጋቸው ነው:: ኦሮሞ ደግሞ ትህነግ (ህውሀት) ካልቆመላቸው ደግሞ አማራን ፊት ማየት ያፍራሉም ይፈሩታልም!

የውጭውን አለም በማሳተፍ የምሩን አቤት ያለው የአማራው ትግል በHR 128 ሲሆን ብዙ ለውጥ በአጭር ግዜ አስመዝግቧል:: እስረኞችን ማስፈታቱና ለሌላም ድምፅ እተተጠባበቀ ያለ ጉዳይ ነው::

በዚህ የሞት የሽረት ግዜ ውስጥ ወያኔ አቅጣጫ ለማስቀየር ጠቅላይ ሚኒስትሯን አወረደች:: ስልጣን እንደ ውሀ የተጠማው፥ የማያውቀው አገር የናፈቀው ኦነግ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በዚህ ጉዳይ ላይ አደረገ:: ወያኔ ማካቬሊያዊ ስልት ተጠቅማ ባመጣቻቸው ሰዎች ለማና አብይ ብሎም ሊተኩ የሚገባቸው ህገ መንግስትን በተከተለ ሰዎች መሀል አደረገችው ጭቅጭቁን:: አብይንም እንደማትፈልገው አብጠለጠለችው ያው እሷ የጠላችውን መውደድ ነውና የዳያስፕራና ኦነግ ስልት:: አንድ የቦክስ ሪንግ ውስጥ አስገባችንና ዳኛዋ እራሷ ሆና በዝረራ ይውጡ ያለችውን አዘረራ በድምፅ ብልጫ ተብሎ አዲስ ጠቅላይ እነሆ አለቻቸው….

በዳይስፕራ እጅና እግር የሌለውን ክርክር ለሰማ የኦህዴድ ማቭሪክነትና ብራቫዶ ሲተነተን ስናይ በዳያፕራ ማን በማን ካባ እንዳደፈጠ ቁልጭ ብሎ እናየዋለን::

የኦሮሞ ጥያቄ እንደ አማራው ተጋድሎ የነፃነት ቢሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትር እገሌ ይሁን እገሌ ውስጥ አይገባም ነበር:: ቲም ለማ ቲም አብይ ብሎ ከዝንጀሮ ቆንጆ መረጣ አይገባም ነበር:: በሩን ከርችሞ ውይይቱን ቆጥ ላይ ሰቅሎ እንደ አማራው ትግል መዳረሻውን ማሳየት በቻለ ነበር ነገር ግን መነሻውም መድረሻውም በአማራ መቃብር ላይ ቆሞ ባለአገር መባል ነውና እራሱን ሰማንያ ግዜ እየፈጠፈጠ ስንት ግዜ እራስ የማጥፋት ሙከራ እያደረገ ስንቴ ሞቶ ስንቴ ተበሳ?! ለዝንትም ደግሞ ዛሬ እነሆ ሞተ:: ያለ ምንም ምክኒያት ማቭሪክ ያደረጉት ኦህዴድ በመጭው ሰኔ ወር በተዋህዶ ኢሀዴግ ታድሶና ሟሙቶ ሲገባ ኦህዴድን ከናካቴው ደህና ሰንብት ትለው ዘንድ ግድ ነው:: ኦህዴድም ነፍስ አወቀ ኢህዴግም ሆነ! እንባ ስንቅ አይሆንም ግን ሰንቅ ካሁኑ ይሄ መርዶ ከሆነብህ:: ቲም ለማን ቡን አድርጋዋለች ኦልሬዲ::

ትግርኛ ተናጋሪው ዶ/ር ሌተናንት ካርኔል አቦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን በተሳካ ለመፈፀም በቂ የኢንሳ ልምድ አላቸው:: በተዋጣለት ቴክኖሎጂ ላይ በተመሰረተ የስለላ ግብረ ሀይል crackdown ይጀምራል:: ኦህዴድ ወላ ቄሮ እያለ ከዚህ ቦኃላ ማንም ጤና አያጣም! መዋቅር በተዋህዶ ስም በማፍረስ አደረጃትህን እንደገነቡት “ቢቲኒ ጀዴ” ያደርጉታል ማለት ነው:: አንተም “ኢትዮጵያ ካልፈረሰች እኛ የምንፈልገውን አናገኝም” እንዳልክ እሷም ኦህዴድን ካላፈረሰች ጤና አታገኝም:: ….”ይጥፉ ወይንስ እንጥፋ” የሚል መስቀለኛ መንገድ ላይ እራሷን አግኝታለችና “እንጥፋ” እንደማትል አንተም ተወዲሁ ታውቀዋለህ::

ግቡ አገር ከማፍረስና ሞጋሳን በመጫን የሌሎችን ባህል ከማጥፋት ያለፈ ቢሆን ኖሮ ኦሮሞው ትግል ቀርቅሮ ዘግቶ ማንም ይውረድ ማንም ይውጣ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ነው የምሰራው ቢል ኖሮ በመሀል ገብተው ሀይ ያሉት ነጮች ፈረጆቻችሁም ይሄ ተሀድሶ (reform) ሳይሆን ስር ነቀል የስርአት ለውጥ ካላመጣን አካባቢው የጦር ቀጠና ይሆናል ብለው ባሰቡበት ነበር:: ያለው demand ስር ነቀል ለውጥ የማምጣት ነው የሚለውን መልእክት አልሰደዳችሁም!

የኦሮሞው በረከት ሲሞን አቦይ አብይ ቴክኖሎጂን አዋቅረው በጨረሱት ኢንሳ ተገን አድርገው ኦህዴድ የሚልን ትርክት በነበር ያስቀሩታል:: ትህነግ (ህውሀት) ኦህዴድ ኦብነግ ወዘተ በውህደት እንደሰም ትቀልጣለህ በቅርቡ:: ያው ትህነግ (ህውሀት) ህያው ነች! አንድም አስርም እየሆነች ትገለጣለች::

ስልት የጎደለው አካሄድ አለና ፓለቲካውን አሁንም በበላይነት የምትቆጣጠረው ትህነግ (ህውሀት) ሆናለች:: ኮማንድ ፓስት ብላ በመላው በአገሪቱ ግዚያዊ አዋጅ ስታውጅ አገር ይበልጥ በማረጋጋት ታሳጣታለህ እንጂ ቦቴ ኢንባርጎ አታደርግም:: ያማ በውነትም የህጉን አሳፈላጊነት ይመሰክራል:: ለውጭውም ለምትለምነው ፈረንጅና አፈ ቀላጠው አሜሪካን ኤምባሲም ተቀምጦ ለሚታዘብህ ኮማንድ ፓስቱን እንዲያቆላምጥ ነው ያስገደድከው::

ጥያቄውን ከአሻንጉሊት ልውውጥ ባለፈ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ቢሆን ኖሮ የአብይ ወይ የለማ መመረጥን የኦሮሞ ትግል ውጤት አስመስለህ ባልደሰኮርክ ነበር ስልት ቢኖርህ ኖሮ …ግብ አበጅተህ ቢሆን ኖሮ የተነሳኸው በአሻንጉሊት በክር ተስቦ ወደፊት መጥቶ መደቀን ባልፈነጠዝክ ነበር:: በክር ተስቦ ወደ ኃላ በሄደውም አጉል ጀብድ ባልሰጠኸው ነበር::

ትህነግ (ህውሀት) አቦይ አብይን እድሜ በሁለት አመት መጥና ያስቀመጠችውን ሰው ዘላቂ የሆኑ ዋና ዋና መሰረታዊ የአገራችንን ችግርም ይፈታል ተብሎ በዚሁ “ተቃዋሚ” ነኝ የሚል ሀሳዊ አንድነቱና ኦሮሙማ እንቅስቃሴውም ያስባል:: በጣት ሰማይ መንካት…. “አይ ምድር ላይ ያለ ሰው” አለ:;

ከዚህ ህግ ያልተከተለ መተካካት ድል ነው ብሎ ማለት የሚያሳየው ለጌቶቻችሁ ለነጮቹም ቢሆን ወያኔ ህግን ሊያስተገብር እንደሚጥርና ኦሮሙማ እንቅስቃሴው ግን ገና የህግን ቅደም የማይገነዘብና እኔ ያልኩት ካልሆነ ብሎ የሚያለቅስ የፖለቲካ ህፃንነትን ያሳያቸዋል:: ያ ብቻም አይደለም ይሄ የፖለቲካ የ50 አመት ህፃን ኦሮሞ ካልነገሰ በሚል የተጠመደ አጓጉል ትግል መሆኑን ብሎም አክራሪ ዘረኝነትን ሲያሳይ ከዚህ ፖፖ ላይ ይሄ ህፃን ተቀምጦ አልነሳ ማለት ለመጪውም የፖለቲካ ሂደት ግማት ተደርጎ ይወሰዳል::

ከዚህ ሁሉ ምርጫ ከጠፋ ከጠፋ ጥሩ መሪ በማዘጋጀት በስልታዊነት ትግል ቅርፅ አስይዞ ለሚቀጥለው ምርጫ መዘጋጀት ነበር መላው በወያኔ ስር እንዳኝ ካላችሁ ካላችሁ ዘንዳ:: አሁን ግን ወያኔ የአቦይ አብይን እድሜ በግዚያዊነት ስም በማራዘም ብዙ ሸፍጥ ሰርታ ትጨርሳለች:: እንዳልኳችሁ ፖለቲካ ጥበቧን አለማድነቅ አይቻልም!

እኔ እንደውም እሷን ብሆን “ኦሮሚያ” የሚለውን ክልል አሟሙቼ ባሌ አርሲ ወዘተ ብዬ ገላግልህ ነበር! ህብረተሰባዊነት ወደሚል በማላቅ ማለቴ ነው:: ብሎም ያገሪቱን ቋንቋ ለዘመናት ተሰራውን አማርኛ ልክ በትግራይ እንደሚያስተገብሩት ሁሉ በባሌ በአርሲ ኢሊባቡር ወዘተ ትምህርት ገበታውን አምጥቼ እመግብህ ነበር:

የአቦይ ዶ/ር ሉቴነንት ካርኔል አብይ ኦሮሞ ዝምድና ግን ብዙ ወሀ አያነሳም:: እሳቸው ግማሽ ኦሮሞ ሲሆኑ ግማሽ አማራ ይባላሉ  በሀይማኖት በአባታቸው የሞስሊም ስም የወረሱ ከእናታቸው ኦርቶዶክስ የሆኑ በራሳቸው ፍቃድ እየሱስ ብቻ (only Jesus) ሲሆኑ በሚስታቸው ትግሬ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ይነገራል:: ሚስታቸው ጎንደር ተወላጅ ትግሬ መሆናቸውን አንዳንዶች ያወሳሉ:: የጦር ዘብም ናቸው ይባላል:: ይባላል ነው እንግዲህ….

የአቦይ አብይን ዘር ካነሳሁ አይቀር አንድ ነገር ለማመላከት በ80ዎቹ በነበረው ረሀብ ትግሬዎች በደቡብ አገራችን እንዲሰፍሩ ሲደረጉ በውስጥ የተሰጣቸው ትእዛዝ ልጆቻቸውን በኦሮሞ ስም በመስጠት ማስመዝገብና መታወቂያ መውሰድ ነበር:: ይህንን በጣም ጓዴ ለሆነ ሰው አንዱ የትግሬ ኦሮሞ ሰፋሪ የሆነ ያጫወተው ነው:: ስሙ ደቻሳ ነው ግን ዘሩ ትግሬ ነው:: ኦህዴድ ሆይ ተቀበይኝ ቢላት ታዲያ ኦህዴድ እንዴት በሯን ትዘጋ ነው?!

እናም ኬኛ ኬኛ ጩኸት በአቦይ አብይ ተጠናቋል::

የኛም የህልውና ትግላችን እስከ ነፃነት ቀን ይቀጥላል ማለት ነው::

“የምትለምኑትን አታውቁም” አለ ጌታችን በእውነት የሚለምኑትን አያውቁም! አማራ ርስት ላይ እጁን ሊያሳርፍ “ኬኛ ኬኛ” ጩኸት ከንቱ ሆኖ ቀርቷል!