እይታ እይታ እይታ… (ሊዲያ ዘ-ጊዮን አማራ)

0
1022

እይታ እይታ እይታ (perspective perspective perspective)

አዎ እኛ ካላቦካነው አንበላም! The fool can know. The point is to understand” አለ አልበርት አይንሽታይን!

ሰሞኑን በአማራ ብሄርተኝነት ዳያቆንነት ላይ እንኳን ያልደረሱ እምቦቆቅላዎች… የኔ እምቦቀቅላዎች “ ‘እኔ ካላቦካሁት አይሆንም’ አይነት ነገር ይቅር” እያሉ ይህችንን ቃል ሲደጋግሙ አይቼ ዝም እንዳልል ስተው ሲሄዱ እንዴት አስችሎኝ ፣ ፈጥኜም እንዳልገፅፃቸው ያልቀጡት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል ነውና ልቅሶ ፈርቼ ነበር:: አሁን ግን ትንሽ ማረሚያ ልስጥ ለዚህች ግልብ ንግግር ግልብ ሆና መግለብለቧን ታቆም ዘንዳ! መታረም በቃል ለሚገባው ነው! በእብሪት ለሚነፋ ግን ልምጭም ሲያንስ ነው:: በብሄረትኝነት ውስጥ ገብቶ አልታረም ማለት ግን ቅጣቱ በጋለ ብረት ይሆናል!

አዲስ ብሄርተኛ ችኩል ነው! እናም ችኮላውን እረዳለሁ አልታረምም ባይነትን ግን ከአፍራሽነት አይተናነስምና በቶሎ አራሙጃውን እንነቅላለን!

አዲስ ብሄርተኞች ሆይ:- በመጀመሪያ ችግር ውስጥ ያስገባን እኮ ማንም አብኩቶ የጋገረውን መብላት ላይ በመጠመዳችን ነበር:: ኢትዮጵያ አንድ እስከሆነች የሚል የሞተ ፈሊጥ ይዘን ማንም ያቦካውን እንኩሮ መብላትም አይዶል የገደለን? አያችሁ እኛ ብሄርተኝነቱን ስናቀጣጥለው መጀመሪያ ትግሬም ይሁን ኦሮሞ፣ ኦሮሞም ይሁን አንድነት የጠፈጠፈውን ቂጣ አንበላም ብለን ጦም አድረን ነው ጉዞው የተጀመረው:: ማንም ያቦካውንና የጋገረው ተገኘ ብለን የምንበላ አግበስብሴ አይደለንም ብለን ከማነታችን አንፃር የጋገርነውን ብቻ ልንበላ ወስነን ነው የተነሳነው:: ነፃነትን የምንቸረው ሳይሆን የምንናጠቀው መሆኑን አስምረንበት ነው ብሄርተኝነቱን የመተርነው:: ማንም ሳይሰጠን ነፃነታችን በኛው እጅ ልትመጣና እኛን ከእኛ ውጭ ማንም እንዳያስተዳድረን መክረን ነው:: ስለሆነ የተጋገረውን እንጀራ ጤፉ የት ተገዛ? በማን ተቦካው? በማንስ ተጋገረ? ብለን ጠይቀን አንበላም ከሚል ያደምነው:: አንበላም ብለን ደግሞ አልተቀመጥንም እንደ አንድነት ጎራ አኩራፊ ፖለቲከኞች ነገር ግን አንበላም ካል በኃላ እራሳችን ጤፉን ገዛን ዳሩ እኛም አይደለን የጤፍ ጌታ?! አቦካን አቦካን አቦካንና ጋገርነው:: አማራ ብሄርተኝነትም ተወለደ- ሀሌሉያ!

እና ይህንን የጋገርነውን አይኑ ልቅም ያለ እንጀራ እያበላን ብዙዎችን እራሳችን ያቦካነውንና የጋገርነውን ብቻ መብላት ብለን አገጋገሩን፣ አሰነዳዱን፣ እርሾውን እንዴት እና እንዴት ሆኖ ቆንጆ አማራዊ አይን ያለው እንጀራ አገጋገርን አስተምረንና ጋግረን እራስን በራስ ማስተዳደር፣ አባት አገር ምስረታን አስተማርን:: እና ዛሬ አንዳንዶች እርሾ ከብአዴንና አንዴንዴም ከአንድነት እራስ ጠል አማሮች ሲላቸውም ከሰፈር በተገኘ ቡድናዊ እርሾ ለማስገባት ሲጣጣሩ ተው recipe አታበላሹ ብለን ኦሪጅናል የrecipe ባለቤቶች ልንመክር ልናቃና ስንል እነዚ ጥቂት እርሾ ይዘው እንጀራውን ሙላ ሊያበላሹ ፍንጥር ፍንጥር የሚሉ ቀላዋጮች ሆነው “እኔ ያላቦካሁትማለት ምንድን ነው” እያሉ ካልጋገርኩ የሚሉ ባላቦኩት ሊጥ ባደባባይ ቀለው ይታያሉ:: አላዋቂነታቸውንም እንዲሁ በገዛ እጃቸው ወደው ያሳያሉ::

ተማሪ ካስተማሪው አይበልጥም እንዲል ቃሉ ተማሪው ወደፊት ይማር:: እንደ አዲስ ክርስቲያን በትእቢት መነፋት እንዳይሆን አገልጋይ አይሁን እንደሚልም አዲስ ብሄርተኝነትም እንዲሁ ልምራ ላስተምር ላስተምር አይበል ስል ህገ ድንጋጌውን ለማሳወቅ እሻለሁ::

መሪዎች የሚወጡት ለመመራት የተዘጋጀ ህዝብ ሲኖር ነው:: ትግል አቀጣጥለን አስነሳን:: አስተማርንም ሌት ተቀን ሳንል:: አስበንና አውርደን አውጥተን የሚበጀውንም እነሆ አልን:: አሁን ይህንን ጥሪ ሰምቶ መምጣት የተመሰገነ ሆኖ ሳለ በሁለት ቀን ብሄርተኝነት በሀምሌ አምስት ጥምቀት “እኔ ልምራ ልምራ” ፣ “እኔን ስሙኝ ስሙኝ” ማለት አሸገረን!! ለተንሻፈፈው ጉዳይ ምሪት ስንሰጥ “እኔ ያላቦካሁት” ትላላችሁ እያሉ ኢሳይንሳዊና የፖለቲካ ሪዮት የሚጣረስ አባባል እንዲያስቅባቸው ሆነባቸው:: አሰላለፍን በተነደፉ ሪዮቶች መቃኘት ግድ ይላል::

የብሄርተኝነቱን ትግል ያስጀመርነው አለን:: ትግሉ መሪዎች አለው:: ትግሉ ሪዮት ጨብጧል:: ትግሉ መነሻና ግቡን ጠንቅቆ ያውቃል::

የአዲስ ብሄርተኝነትን ፍንዳታውን ብንረዳውም ብሎም እኛም ያለፍንበት ቢሆንም ቅሉ ፍንዳታው ነገር ሁሉ እንዲያፈነዳ አይሁን:: እና በትግላችን የብሄርተኝነት አፍላነት ፍንዳታ የቄሱን መፅሀፍ እንዳያሳጥበን እንጠንቀቅ::

እናም እኛ ካላቦካነው አይሆንም!

እንደማመጥ!