ታሪክና ፖለቲካ እንደየዘርፉ ይንዘርፈፍ!

0
977

(በሊዲያ ዘ-ጊዮን አማራ)

በአማራ ትግል ውስጥ አንድ ግልፅ መሆን መቻል ያለበት ነገር አለ:: ያው እንደሚታወቀው ሁሉ ብዙዎች ለብሄር ፖለቲካ አዲስ ናቸው:: የአማራ  ብሄርተኝነት ፖለቲካ ስንጀምር በብዙ ጥንናትና ከግራ ቀኝ አከራካሪ ነገሮች ላይ ተወያይተንና አሳማኝ የሆነ እውነታን ተደግፈን ነው:: ነገር ግን አንዳንዶች በጉዞአችን መሀል ከአንድነት ፖለቲካ ወደ አማራ ብሄርተኝነት ሽግግር ሲያደርጉ ብዙ የትግሉን ሂደት ሳያጤኑና ፖለቲካና ከታሪክ መሀል ያለውን ትልቅ ገደል ሳይረዱት ነው:: ታሪክ መፅሀፍትን አገላብጦ ፖለቲካው እግር በእግር በዚያ ይሂድ ማለት አይቻልም:: ሆኖም ብዙዎች በዚህ መረብ ይያዛሉ:: ለምን ስንል ታሪክ የተሰራ ለማመሳከሪያነት የሚረዳ እንጂ ዛሬን እና የነገን እጣ ፈንታ ላይ ፈላጭ ቆራጭ አይደለም:: ፖለቲካና ታሪክ ሁለት ትልቅ የተለያዩ አካል ሆነው ግን ደግሞም የታሳሰሩ ፊልዶች ናቸው:: ትስስራቸው ግን ሲለው ይላላል፣ ይጠብቃል፣ ይበጠሳልም!  ነገር ግን ፖለቲካው ከታሪክ ተሳስሮም፣ ላልቶ፣ ጠብቆም ሆነ ተበጥሶም መጓዝ ይችላል:: ፖለቲካ ዝም ብሎ ታሪክ አንቦ እንደሚተነትን ሰው የሚነባነብ አይደለም:: ታሪክ ታነባለህ ከዛ እንደ እግዝህትነ ማሪያም ትደግመዋለህ::  አለቀ! እውነት ነው ታሪክ ሆኖም ታሪክ ሆኗል:: እውነተኛ ቢሆንም እውነተኛ ተረት ሆኗል:: ብዙ intellectን ማሰራትን አይጠይቅም ታሪክን ቁጭ ብሎ ለማውራት:: የሚጠይቀው የመሸምደድ ችሎታህንና መፅሀፍትን ስራዬ ብሎ ማገላበጥን ነው:: በሌላ አነጋገር አንድ ደብተራ ጥርቅም አድርጎ የሚያውቀውን ነገር መልሶ መላልሶ መናገር ውጭ ሌላ ምንም የለውም::

ይህንን ስል የታሪክን አስፈላጊነትና ዋቢነት እያጣጣልኩኝ አይደለም ነገር ግን ታሪክን እንደ ፖለቲካ የሚይዙ ሀይሎች ከመስመር መውጣትን ለማመላከትና relevance ለመስጠትምና ለማቃናትም ጭምር ነው:: ፖለትካ የእለት ተለት የአንድን ህዝብ ጥቅም  በህልውናው፣ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ወዘተ በተለያየ መልክ የሚሞግት፣ አቅጣጫ የሚቀይስ ብሎም የተሸረቡበትን አደናቃፊ የተቀናቃኝ ብሄር ይሁን ሌላ ህዝብ ሸር የሚገልጥ ለዛም ሸር ሌላ ሸር የሚሸርብ ነው:: የፖለቲካው ሳይንስና የታሪክ ሳይንስ ለየቅል ነው:: እንጂማ ታሪክን ዋቢ በማድረግ ብቻ ቢሆን ኖሮ መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ሀያ ትግሬን ማሳመን ባልቻሉም ነበር:: ነገር ግን ፖለቲካው ለህዝብ እራሱን ሲያቀርብ የዛን ህዝብ ወቅታዊ ተግዳሮቶችንየሚፈታበትን መንገድ ዘይዶ ያዋጣናል ብሎ ማሳመን ነው:: ታሪክንም በፈለገው ትርጓሜ እየሰጡ ማስኬድ ነው::

ፖለቲካ የወደፊት ያልተሰራ ታሪክ ላይ ያነጣጥራል ታሪክ ሊሰራ:: ስለሆነም አንድን ሀይል ወደ ኃላ በታሪክ መውስድና ማስደመም ሳይሆን አንድን ህዝብ ታሪክ ሊያሰራ ያሰልፋል:: ስለሆነም ታሪክን ማጣቀሻነት በላይ እንደ ፖለቲካ ማታገያ መያዝ አይቻልም:: ያለፈ ታሪክ ነውና:: ታሪክ እርግጥ ለአንድ ማህበረሰብ ትልቅ እሴቱ ነው! ግና በዛ እሴት ዛሬን ማንበርከክ አይቻልም:: ዛሬ የዛሬን ታሪክ ሰሪዎች ሰልፈኛን ይሻልና:: እናም ወደፊት መራመድ እንችል ዘንድ በዚህ ሁለት ትልቅ ዘርፎች ላይ ያለውን ልዩነት አጢነን በፖለቲካ እንጎለብት ዘንድ ፖለቲካን እንደ ፖለቲካ እንመርምር ሲያሻ ታሪክ እናጣቅስ:: ነገ የዛሬ ፖለቲከኞች ሰልፈኞች ነችና!

እናም በአማራ ብሄርተኝነት ጎታች የሚሆኑት ብዙውን ግዜ ባለማወቅ እነኝህን ሁከት ዘርፎች እንደየቅላቸው አለመያዝ ነው:: ከብዙ በጢቂት ጠንቅ የሆነብን ፖለቲካውን ከተለያዩ ዘርፎች በማያያዝ በዛ ለመዘውር መሞከር ነው:: ለምሳሌ :-

1) ብሄርተኝነትን ከሀይማኖት ማያያዝ ለምሳሌ አማራን የአንድ ሀይማኖት ክፋይ ብቻ በማድረግ መዘላበድ::

2) ብሄርተኝነትን ከንግስና ስርወ መንግስት አንፃር መዘወር:: የአማራን ብሄርተኝነት ወደፊት እጣ ፈንታውን ንጉስ ለማንገስ ማስመሰል ትልቅ እንቅፋትና በታኝ ነው::… እኔ እራሴ መልሼ ልዋጋው የምችለው ሀሳብ ማለት ነው:: የህልውና ትግልን አንድ ቤተሰብን ስልጣን ላይ የማውጣት ትግል አይደለም:: ይህንን ስል ነገስታቶቻችንን እኮራባቸዋለሁ መላው ግን የነሱን የልጅ ልጆች ማንገስ ነው ብዬ አላምንም:: I mean it’s 2020 already… አማራነትና አማራነት ብቻ!

3) ከዲሞክራሲ አስተዳደር ጋር ማያያዝ ነው:: የአማራ ብሄርተኝነት የዲሞክራሲ ትግል ሳይሆን የህልውና ነው::

4) አማራውን ብሄርተኝነት ከዳር ሆኖ መዘወር መፈለግ ትልቁ ጠንቅ ነው:: ወይ ወደ መሀል መግባት ወይን መውጣት ነው:: መሀሉን ይዞ ወደ በራ መብራት (spotlight) እየተጠጉ እራስን ማሳያ ማድረግ እጅግ የከፋው ጠንቅ ነው::

5) ብሄርተኝነቱን አልደግፍም እያሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ እንደ ገለልተኛ አካል መስሎ የሚዘላብዱት ደግሞ እጅግ የከፉት ናቸው:: እነኝህ ኢትዮጵያ ሀሳዊ አንድነትን በታሪክ ቆማሪነትየተረሳው ጀግና ያስታወስነው ጀግና እያሉ እንደ መዝገብ ቤት ጠባቂ ታሪክን ለግል መታወቂያን የተደበቁበት ሰዎች ሞቅ ሲል አማራ ብሄርንነት ጠጋ እያሉ “እንደምታውቁት እኔ የዘውግ ፖለቲካ አክደግፍል ግን” ግን እያሉ የሚገናገኑ ለኢትዮጵያ መሀል ፖለቲካም ይሁን ለአማራው ፖለቲክ ጠብ የሚል ነገር መስራት የማይችሉ በላይክ የሚሟሟቅ አቋማቸው መልመጥመጥ ለሆዳቸው እንዲያድሩ ያስገደዳቸው ናቸው::

እናም ፖለቲካውን shrewd ሆኖ ስልታዊነትን ተላብሶ፣ ከግራ ቀኝ ተመልክቶ፣ መላ የሚል የሀሳብ ሰዎች ብቻ ሊመሩና ሊያብቡበት ይገባል:: ምክኒያቱም እንደዚህ ያሉቱ ብቻ ናቸው መንገድ ቀይሰው ማህበረሰባቸውን ለድል ማብቃት የሚችሉ::

ያማራው ትግል ያሸንፋል!ነው